top of page

ነሀሴ 30 2017 - በኢትዮጵያ የአመራር ክህሎት ላይ በርትተን ከሰራን እንደሀገር የሚስተዋሉ ችግሮቻችንን መፍታት እንችላለን ተባለ

  • sheger1021fm
  • 2 hours ago
  • 1 min read

ለዚህ መፍትሄ የሆነውን የአመራር ብቃት ማዳበር ላይ ትኩረት አድርጌ እየሰራሁ ነው ሲል The power of international education የተሰኘ አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ተናግሯል።


ድርጅቱ ከ15 አመታት በፊት በኢትዮጵያ ስራዎችን መከወን የጀመረ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ሴት ተማሪዎችን መደገፍ እና የአመራር ክህሎትን ማስፋት ላይ በትኩረት እንደሚሰራበት ተነግሮለታል።

ree

ተቋሙ ዛሬ ያሰናዳው መርሀ ግብሩም ከአምስት ዓመታት በፊት የጀመረው እና የስነ ተዋልዶ ጤና ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎችን የአመራር ክህሎት እንዲኖራቸው ያደረገበት መሆኑን ተናግሯል።


በዚህም መሰረት በጤናው ዘርፍ ላይ የሚሰሩ 148 ተማሪዎችን እያሰለጠነ መሆኑን የተናገረ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ዛሬ 48 ተማሪዎቹን ብቁ ማድረጉን ተናግሯል።


የአመራር ብቃት እንዲኖራቸው በስልጠና የታገዙት ከኦሮሚያ ክልል እና ከአዲስ አበባ የተውጣጡ ባለሙያዎች ናቸው ሲሉ The power of international education የሰሀራ በስተደቡብ እና የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኢትዮጵያ ጥላሁን ተናግረዋል።


እነዚህ ተማሪዎች ካሁን በኋላ ወደሚሰሩባቸው ተቋም ሲገቡ ከዚህ ቀደም ይሰሩበት በነበረው የአመራር ሥርዓት፣ ችግሮችን የመፍታት አቅም እና ሌሎች ሂደቶችን በተሻለ መንገድ ተግባራዊ ያደርጋሉ ተብሎ ተስፋ እንደተጣለባች ተናግረዋል።


እንደ ሀገር የአመራር ብቃት እና ክህሎት ላይ እየሰራ ነው ያለው ስራ ጥሩ ቢሆንም የተበጣጠሰ እና በቂ ያልሆነ ነው ተብሏል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page