ነሀሴ 30 2017 - ሁለተኛው የአፍሪካ የወጣቶች የአየር ንብረት ጉባኤ በአድዋ ሙዝየም እየተካሄደ ነው።
- sheger1021fm
- 3 days ago
- 1 min read
አፍሪካዊያን ወጣቶች በአየር ንብረት ለውጥና በሌሎች ምክንያቶች ለስደት እየተዳረጉባት መሆኑን በጉባኤው ተነስቷል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አፍሪካ ወደ ከባቢ አየር የምትለቅቀው በካይ ጋዝ ከአጠቃላዩ ድርሻው ከ4 በመቶ ዝቅ ያለ መሆኑን ተናግረዋል።
ነገር ግን አፍሪካ በድርቅ፣ ጎርፍ፣ በምግብ ዋስትና አለመረጋገጥ፣ በዝናብ እጦት እና ሌሎችም ችግሮች ወጣቶቿ የስደትና ሌሎችም ችግሮች ተጋፋጭ እየሆኑ ነው ተብሏል።

አፍሪካውያን ወጣቶች ላይ በስራ ፈጠራ በወጣቶች የነገ መሪነት ላይ በስፋት መስራት ይገባል ያሉት አቶ ተመስገን የአዲስ አበባ የአፍሪካ ወጣቶች ዲክላሬሽን ይዘጋጃልም ብለዋል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ አፍሪካውያን ወጣቶች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለስደትና ለሌሎች ችግሮች እየተጋለጡ ቢሆንም የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን እየሰሩ የሚገኙ ወጣቶችም አሉን በማለት ተናግረዋል።
በውይይቱ እየተሳተፉ ያሉ ወጣቶች በአየር ንብረት ለውጥ ፍትህ እንፈልጋለን ፍትህም ዛሬ ይሰጥ ሲሉ በተደጋጋሚ ሲናገሩ አድምጠናል።
ኢትዮጵያ በአድዋ ጦርነት የውጪ ወራሪን ተባብራ ድል እንዳደረገች አፍሪካውያንም በህብረት የአየር ንብረት ለውጥን በመተባበር ክንድ መፋለም አለባት ፣ የአየር ንብረት ለውጥ በዚሁ ከቀጠለ ከአሁኑ በባሰ መንገድ አፍሪካውያን ለስደት ይዳረጋሉ ተብሏል።
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
Comments