ነሀሴ 30 2017ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደንበኞቼን ሽልማት በሽልማት ላደርጋቸው ነው አለ፡፡
- sheger1021fm
- Sep 5
- 1 min read
ኩባንያው "በሽ" ሲል በጠራው ሎተሪ ሽልማት 57 ሚሊዮን ብር የሚደርሱ ሽልማቶችን ከአጠቃቀም ልማድ ጋር ያጣመረ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ዛሬ የተጀመረው የበሽ ሎተሪ ሽልማት የመጀመሪያዎቹ የሁለት ሳምንታት የ1 ሚሊየን ብር አሸናፊዎች በሥነ ስርዓቱ ላይ የተሸለሙ ሲሆን በየሳምንቱ ሁለት ሰዎችን ሚሊየነር እያደረግ እስከ ሕዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም የሚዘልቅ ይሆናል ተብሏል።

በዚህ የሽልማት መርኅ ግብር ደንበኞች ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ እና የሳምንቱ ትልቁ አሸናፊ የሚሆኑበትና ከእያንዳንዱ ደንበኛ የአጠቃቀም ልምድ ጋር የተሰናሰሉ አዳዲስ የበሽ ጥቅሎች ቀርበዋል ሲል ኩባንያው አስረድቷል።
በዚህ መርኅ ግብር ደንበኞች የድምጽ፣ የዳታ እና የመልዕክት ወይም ሁሉንም ያካተቱ የበሽ ጥቅሎችን ሲገዙ የሽልማት መለያ ቁጥር ከሳፋሪኮም በመልዕክት ይደርሳቸዋል ተብሏል።
በበሽ ሽልማት ዕለታዊ ለ224,000 አሸናፊዎች ለእያንዳንዳቸው 100 ብር፣ ሳምንታዊ ለ25 አሸናፊዎች ለእያንዳንዳቸው 100,000 ብር፣ ሜጋ ሳምንታዊ ለ32 አሸናፊዎች 1,000,000 ብር ለእያንዳንቸው የሚሸለሙ ሆኖ በጠቅላላው 56.9 ሚሊየን ብር ለሽልማት ቀርቧል።
ለዚህ ሽልማት ብቁ የሚሆኑት ተሳታዎች የሳፋሪኮም ደንበኞች ሆነው በስማቸው የተመዘገበ የኤም ፔሳ አካውንትና ሲምካርድ ሊኖራቸው ይገባል ሲሉ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ዋና ኃላፊ አንዱዓለም አድማሴ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞቼ ቁጥር ከ10 ሚሊዮን በላይ ደርሷል፣ ይህም ከፍተኛ ስኬት ነው ማለቱ ይታወሳል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments