top of page

ነሀሴ 28 2017 - መንግስት ሰላም ማስፈን ላይ እንዲሰራ ተጠየቀ

  • sheger1021fm
  • 44 minutes ago
  • 1 min read

በኢትዮጵያ እንደልብ ተንቀሳቅሶ መነገድ፣ ማረስም ሆነ ሌላ ሌላውን ለመስራት የሰላም እጦት እንቅፋት ስለሆነ መንግስት ሰላም ማስፈን ላይ እንዲሰራ ተጠየቀ፡፡


የሰላም እጦቱ ካለው የኑሮ ውድነት ጋር ተዳምሮ የነዋሪውን ኑሮ በእጅጉ እየፈተነው እንደሆነ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የአግሮ የኢኮኖሚ መምህር እና የምክር ቤት አባሉ መብራቱ ዓለሙ(ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡


ሰላም ከሌለ የቱንም ያህል ታርሶ ቢመረት ህዝቡ ጋር ስለማይደርስ እድገትን ማሳካት እንደማይቻል ባለሞያው ጠቁመዋል፡፡


መንግስት በበኩሉ የሚባለውን ያህል የተጋነነ የሰላም እጦት ባይኖርም ችግሩን ግን እረዳለሁ ብሏል፡፡


በገንዘብ ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) በአንድ አንድ አካባቢዎች በፊት የነበረው የሰላም እጦት እየቀነሰ እንዳለም አስረድተዋል።


በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል መሄድ እንደማይቻል ተደርጎ የሚቀርበው ሀሳብ ተገቢ እንዳልሆነ ተናግረዋል።


ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ሰላም መሰረት ስለሆነ ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ እንዳለ መንግስት ሲናገር ይሰማል።




ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page