top of page
የሐምሌ 23 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ግብፅ በግብፅ የሜዴትራኒያን የባህር ዳርቻ የነበረ የአሜሪካ የጋዝ ማጠራቀሚያ መርከብ በድሮን ተመታ ተባለ፡፡ ሁለት የደህንነት ምንጮች መርከቡ በድሮን እንደተመታ አረጋግጠውልኛል ሲል ሬውተርስ ፅፏል፡፡ መርከቡ በድሮን እንደተመታ በእሳት መያያዙ ታውቋል፡፡ ቃጠሎው ወደ ሌላ መርከብም ተጋብቶ ነበር ተብሏል፡፡ ኋላ ግን ቃጠሎው በቁጥጥር ስር መዋሉ ተጠቅሷል፡፡ በእሳት ተያይዘው የነበሩት መርከቦች ባህረኞች አንዳችም ጉዳት ሳይገጥማቸው እንዲወጡ ተደርጓል ተብሏል፡፡ ለጥቃቱ ሀላፊው እኔ ነኝ ያለ ወገን እንደሌለ መረጃው አስታውሷል፡፡ #ኢራቅ በኢራቅ ካታኢብ ሔዝቦላህ የተሰኘው ታጣቂ ቡድን መንግስት የአገሪቱን ሉአላዊነት ሊያስከብር ይገባል አለ፡፡ ቡድኑ ለመንግስት ያቀረበው ጥያቄ በማስጠንቀቂያ ጭምር የታጀበ እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡ የቡድኑ ማስጠንቀቂያ የተ
2 hours ago2 min read
የሐምሌ 22 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#አሜሪካ አሜሪካ እና ሳውዲ አረቢያ ኢራቅ ውስጥ በአፍቃሪ ኢራን ታጣቂዎች ይዞታ ላይ ድብደባ ፈፀሙ፡፡ ሰሞኑን ሳውዲ አረቢያ በኢራቅ የሚገኙ አፍቃሪ ኢራን ታጣቂዎች በድሮን ጥቃት አድርሰውብኛል ስትል እንደነበር አልጀዚራ አስታውሷል፡፡ ሳውዲ ጥቃቱን ከማውገዝ በተጨማሪ መበቀሌ አይቀርም በሚል ዝታ ነበር፡፡ በኢራቆቹ አፍቃሪ ኢራን ታጣቂዎች ላይ አሜሪካ እና ሳውዲ በፈፀሙት ጥምር ድብደባ ከ20 የማያንሱት መገደላቸው ተሰምቷል፡፡ በሌላ መረጃ አብዮታዊ ዘብ የተሰኘው የኢራን የጦር ክፍል በዮርዳኖስ በሚገኝ የአሜሪካ የጦር ተቋም ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሰንዝሬያለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡ የዮርዳኖስ ጦር አምስት ሚሳየሎችን መትቼ አሰናክያለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡ ስለ ዮርዳኖሱ ጥቃት ከአሜሪካ በኩል የተሰጠ አስተያየት የለም፡፡ የወደፊቱን የሆርሙዝ የባህር መተላለፊያ ወሽመ
1 day ago2 min read
የሐምሌ 20 የውጭ ሀገር ወሬዎች
#ቀይ_ባህር በቀይ ባህር የባብኤል መንደብ ወሽመጥ የሚተላለፉ መርከቦች ብዛት በእጅጉ እየቀነሰ ነው ተባለ፡፡ በወሽመጡ የሚተላለፉ መርከቦች ብዛት የቀነሰው የየመን ሁቲዎች ባለፈው ሳምንት የሳውዲ አረቢያን ወደቦች እንከቻችምባታለን ብለው ከዛቱ በኋላ እንደሆነ ሬውተርስ ፅፏል፡፡ ለምሳሌም ትናንት በባብኤል መንደብ የባህር ወሽመጥ በኩል ያለፉት የጭነት መርከቦች 11 ብቻ እንደሆኑ የባህር ጉዞ መረጃ አጠናቃሪው የኬፕለር መረጃ ያሳያል፡፡ ይሄም በወሩ በባብኤል መንደብ ወሽመጥ ከተላለፉት መርከቦች ብዛት እጅግ ዝቅተኛው መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ የየመን ሁቲዎች እና ሳውዲ አረቢያ ዳግም ወደ ጦር ፍጥጫቸው ከተመለሱ ሰንብተዋል፡፡ ርዕሰ ከተማዋ ሰንዓን ጨምሮ የየመንን አብዛኛውን ሰሜናዊ ክፍል የሚያስተዳድሩት ሁቲዎቹ የኢራን ሁነኛ የፖለቲካ ሸሪኮች እና የጦር አጋሮች እን
3 days ago2 min read
የሐምሌ 15 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ሞሪታንያ በሞሪታንያ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ በደረሰ የባህር አደጋ 144 ጥገኝነት ፈላጊዎቹ ሳይሞቱ አልቀረም ተባለ፡፡ የአደጋው ሟቾች መነሻዋን ከጋምቢያ በማድረግ ወደ ስፔን በማምራት ላይ በነበረች ጀልባ የተሳፈሩ ጥገኝነት ፈላጊዎች እንደሆኑ አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ በጀልባዋ ተሳፍረው የነበሩት በሙሉ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የመጡ ጥገኝነት ፈላጊዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡ 38 ጥገኝነት ፈላጊዎችን በሕይወት ማትረፍ እንደተቻለ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን /UNHCR/ መረጃ ያሳያል፡፡ አፍሪካውያን ጥገኝነት ፈላጊዎች ወደ ስፔኗ ካናሪ ደሴት በመናኛ ጀልባዎች የሚደርጉት የባህር ጉዞ አደጋ እንደሚደጋገምበት መረጃው አስታውሷል፡፡ አደጋውን ለማስቀረት ገፊ ምክንያቶቹ በወጉ ሊመረመሩ ይገባል መባሉ ተሰምቷል፡፡ #የመን የየመን ሁቲዎች የትኞቹም የመር
Jul 222 min read
ሐምሌ 7/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች
#ኢራን የኢራን አብዮታዊ ዘብ የቀድሞ አዛዥ ሆሴን ካናኒ የአሜሪካውን ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕን ዋይት ሐውስ ድረስ ዘልቀን እንገድለዋን ሲሉ ዛቱ፡፡ ካናኒ ኢራን ደግሞ ለዚህ አቅሙም ችሎታውም አላት ማለታቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡ በቅርቡ ለሟቹ የኢራን የቀድሞ ጠቅላይ መሪ ስንብት እና የቀብር ሥነ ሥርዓት ሲከናወን ትራምፕን የመግደል ዛቻ ሲስተጋባ ነበር ተብሏል፡፡ የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላ ዓሊ ኻሚኒ ከቤተሰብ አባሎቻቸው ጋር የተገደሉት በጦርነቱ መጀመሪያ አሜሪካ እና እስራኤል በፈፀሙት ጣምራ ድብደባ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ዓሊ ኻሚኒን በመተካት ልጃቸው ሞጅታባ ኻሚኒ አዲሱ ጠቅላይ መሪ ሆነው መመረጣቸው ይታወቃል፡፡ ትራምፕ ኢራኖች እሳቸውን ለመግደል ከሞከሩ በአገሪቱ ላይ ሺህ ሚሳየሎችን አዘንብባታለሁ ሲሉ መዛታቸውን መረጃው አስታውሷል
Jul 142 min read
የሰኔ 19 /2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ቬኒዙዌላን የተለያዩ የአለማችን አገሮች በመንታ ርዕደ መሬት የተመታችዋን ቬኒዙዌላን አይዞሽ ፣ ከጎንሽ ነን እንደግፍሻለን አሏት፡፡ ቬኒዙዌላን ለመደገፍ ከጎንሽ ነን ካሏት መካከል አሜሪካ እና ካናዳ ይገኙበታል፡፡ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ አገራቸው ታላቅ ፣ ፈጣን እና ውጤታማ የእርዳታ ምላሽ ትሰጣለች ማለታቸውን አልጀዚራ ፅፏል፡፡ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኔይ አገራቸው በአደጋው ጉዳት ለገጠማቸው ቬኒዙዌላውያን ሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ እየተሰናዳች መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በአደጋው ክፉኛ ማዘናቸውን እወቁልኝ ብለዋል፡፡ ድርጅቱ ለቬኒዙዌላ አለም አቀፍ እርዳታ እንደሚያስተባብር ጉቴሬዝ አረጋግጠዋል። የካራካስ አለም አቀፍ ኤርፖርት በአደጋው ምክንያት መዘጋቱ የሰብአዊ እ
Jun 262 min read


የኢራን ሹሞች አሜሪካን በሚሳየሎቻችን አትምጪብን አሏት፡፡
ሰኔ 12/2018 - #ዓለም_አቀፍ_ወሬዎች #ኢራን የኢራን ሹሞች አሜሪካን በሚሳየሎቻችን አትምጪብን አሏት፡፡ የኢራን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ኢስማየል ባጋይ የኢራን የሚሳየል መርሐ ግብር አሜሪካ እና ኢራን በደረሱት የጦርነት ማቆሚያ የመግባቢያ ስምምነት አንድም ስፍራ አልተጠቀሰም ማለታቸውን ሬውተርስ ፅፏል፡፡ ቃል አቀባዩ ሚሳየላችን ለተኩስ እንጂ ለድርድር አይቀርብም ሲሉ መሳለቃቸውም ተሰምቷል፡፡ ከአሜሪካ ሹሞች በኩል የኢራን የሚሳየል መርሐ ግብር የወደፊቱ ድርድር አካል ነው የሚለው አስተያየት እየተደጋገመ ነው ተብሏል፡፡ የኢራን ሹሞች ደግሞ ምንም ቢፈጠር ሚሳየሎቻችን ለድርድር አይቀርቡም የሚል አቋም ይዘዋል፡፡ በመግባቢያ ስምምነቱ ዝርዝር ጉዳዮች ኢራን እና አሜሪካ በ60 ቀናት ውስጥ ድርድር እንደሚያደርጉ በሰነዱ ላይ መስፈሩን መረጃው አስታውሷል፡፡
Jun 192 min read


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በጦርነት ጉዳይ ''ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ንትርክ ውስጥ መግባት ባልሻም በጦርነት አውጋዥነቴ ግን እገፋበታለሁ'' አሉ፡፡
ሚያዝያ 6/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች #ካቶሊካዊት_ቤተ_ክርስቲያ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በጦርነት ጉዳይ ከአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ንትርክ ውስጥ መግባት ባልሻም በጦርነት አውጋዥነቴ ግን እገፋበታለሁ አሉ፡፡ ቀደም ሲል ትራምፕ የካቶሊኩን ርዕሠ ጳጳስ ደካማ ሲሉ መጥራታቸውን አናዶሉ አስታውሷል፡፡ ሊዮ 14ኛ በአልጀሪ ጉብኝታቸው ወቅት ትራምፕ ያሻቸውን ቢሉም ጦርነትን በብርቱ ማውገዜን እገፋበታለሁ ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ እኔ የወንጌል ሰባኪ ነኝ በአለም ሰላም እንዲሰፍን ከመናገር ወደ ኋላ አልልም ብለዋል፡፡ ትራምፕ ቀደም ሲል ኢራን የኒኩሊር የጦር መሳሪያ ባለቤት መሆኗን የሚደግፍ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አልፈልግም ማለታቸው መረጃው አስታውሷል፡፡ አሜሪካ እና ኢራን በጠላትነት ከተሰ
Apr 142 min read


የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገራቸው ጦር የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት መናኸሪያ የሆነውን የካርግ ደሴት ሊይዝ እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ፡፡
መጋቢት 21/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገራቸው ጦር የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት መናኸሪያ የሆነውን የካርግ ደሴት ሊይዝ እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ፡፡ የካርግ ደሴት የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት ማምረቻ እና ለውጭ ገበያ ከታለመው ነዳጅ 90 በመቶው የሚላከው ከዚሁ ደሴት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ከወር በላይ ባስቆጠረው የኢራን ጦርነት ምክንያት በአለም ዙሪያ የነዳጅ ዘይት ዋጋ በጣሙን እያሻቀበ ነው ተብሏል፡፡ ኢራን በኢስፍሐን ዩኒቨርስቲ ላይ ለተፈፀመባት ጥቃት በእስራኤል እና በባሕረ ሰላጤው አገሮች በሚገኙ የአሜሪካ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የአፀፋ ጥቃት እንደምታደርስ ዝታለች፡፡ ኢራን በእስራኤል ደቡባዊ ክፍል የኢንዱስትሪዎች መገኛ ላይ በፈፀመችው የሚሳየል ድብደባ ከባድ ቃጠሎ መድረሱ ታውቋል፡፡
Mar 302 min read


የታይዋኗ ርዕሠ ከተማ ታይፔ የቀድሞ ከንቲባ በጉቦ ቅሌት የ17 አመታት የእስር ቅጣት ተከናነቡ፡፡
መጋቢት 18/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ታይዋን የታይዋኗ ርዕሠ ከተማ ታይፔ የቀድሞ ከንቲባ በጉቦ ቅሌት የ17 አመታት የእስር ቅጣት ተከናነቡ፡፡ ኮ ዌን ጄ የተባሉት የታይፔ የቀድሞ ከንቲባ ለ17 አመታት እስር ቅጣት የተዳረጉት የ532 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የምንዛሪ ግምት ያለው ገንዘብ በጉቦ መቀበላቸው ተረጋግጦባቸው እንደሆነ AFP ፅፏል፡፡ በተሰጣቸው ጉቦ ለውጥ ለሪል ስቴት አልሚዎች ከተፈቀደላቸው በላይ ሰፊ መሬት መምራታቸው ታውቋል፡፡ ግለሰቡ በጠበቆቻቸው አማካይነት ይግባኝ መጠየቃቸው ተጠቅሷል፡፡ ጉዳያቸው በይግባኝ እስኪታይም በዋስ ሆነው ውጤቱን ይጠባበቃሉ ተብሏል፡፡ #አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በሰላሙ ጉዳይ ያለ አንዳች ማንገራገር ካልተስማማች ከእስካሁኑም የከፋ ከባድ ድብደባ ይጠብቃታል ሲሉ
Mar 273 min read


መጋቢት 16/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ኢራን ለኢራን ጠቅላይ የደህንነት ምክር ቤት አዲስ የበላይ ተሰየሙ፡፡ የምክር ቤቱ የበላይ ሆነው የተሰየሙት ሞሐመድ ባጌር ዘልግ ሐድር እንደሆኑ ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡ የቀድሞው የምክር ቤቱ የበላይ ዓሊ ላርጃኒ ባለፈው ሳምንት በእስራኤል ጥቃት መገደላቸው ሲነገር ሰንብቷል፡፡ ላርጃኒን ተከትሎም የቀድሞው የደህንነት ሚኒስትርም ተገድለዋል፡፡ ከ3 ሳምንታት በላይ ባስቆጠረው ጦርነት የቀድሞው ጠቅላይ መሪ አሙያቶላህ ዓሊ ሐሚኒን ጨምሮ በርካታ ሹሞች መገደላቸው ይነገራል፡፡ በጦርነቱ በአገሪቱ ከ1300 በላይ ሰዎች ተገድለዋል ተብሏል፡፡ ኢራንም በእስራኤል እና የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች በሚገኙባቸው የአረብ አገሮች የአፀፋ የሚሳየል እና የድሮን ጥቃት እየሰነዘረች መሆኑን መረጃው አስታውሷል፡፡ #አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጦርነቱ ማብቂያ
Mar 252 min read


የኢራን አዲሱ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ሞጅታባ ሐሚኒ አሜሪካ እና እስራኤልን ሳናንበረክክ የተኩስ አቁም አናደርግም ማለታቸው ተሰማ፡፡
መጋቢት 10/2018 - አለም ዓቀፍ ወሬዎች #ኢራን የኢራን አዲሱ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ሞጅታባ ሐሚኒ አሜሪካ እና እስራኤልን ሳናንበረክክ የተኩስ አቁም አናደርግም ማለታቸው ተሰማ፡፡ ሞጅታባ ሐሚኒ ምንም ዓይነት የተኩስ አቁም አናደርግም ያሉት የመጀመሪያቸው በሆነ ፖሊሲ ነክ ምክክር በመሩበት አጋጣሚ እንደሆነ በስም ያልተጠቀሱ የኢራን ሹም መናገራቸውን ሬውተርስ ፅፏል፡፡ በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ የኢራን አፀፋ ከባድ እና የከፋ ይሆናል ሲሉ ሞጅታባ ዝተዋል ተብሏል፡፡ አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ አሜሪካ እና እስራኤልን ገና የእምብርክክ እናስኬዳቸዋለን ማለታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሹም ተናግረዋል፡፡ የሞጅታባ ሐሚኒ ጠንከር ያለ አስተያየት የተሰነዘረው በውጥረት ማርገቢያ ጉዳይ ለቀረበላቸው ሀሳብ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ በኢራን የጠቅላይ መሪነቱ ሹመት
Mar 192 min read


በኢራን ወታደራዊ እርምጃ ስለመውሰድ በአሜሪካ በኩል እየተነሳ ያለውን ሀሳብ ኢራን የምር አድርጋ ብትወስደው ይበጃታል ተባለ፡፡
የካቲት 19/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ኢራን በኢራን ወታደራዊ እርምጃ ስለመውሰድ በአሜሪካ በኩል እየተነሳ ያለውን ሀሳብ ኢራን የምር አድርጋ ብትወስደው ይበጃታል ተባለ፡፡ ይህንን ያሉት የአሜሪካው ምክትል ፕሬዘዳንት ጄዲ ቫንስ ናቸው፡፡ ሁለቱ ሀገሮች በኢራን የኒውክሊየር ፕሮግራም ዙሪያ ለሶስተኛ ዙር ንግግር ጄኔቫ የገቡ ሲሆን ምክትል ፕሬዘዳንቱ ግን ኢራን አሁንም ለሰላማዊው መንገድ ዝግጁ አትመስልም እያሉ ነው፡፡ የኒውክሊየር ፕሮግራሟንም እንዳላቆመች መረጃ አለን ያሉት ምክትል ፕሬዘዳንቱ ያ ለአሜሪካ ትልቅ ችግር ነው ብለዋል፡፡ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ደግሞ የዛሬው የጀኔቫ ስብሰባ በኢራን የኒውክሊየር እና የባለስቲክ ሚሳየል ፕሮግራሟ ዙሪያ ድርድር የሚደረግበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በኢራን በኩል
Feb 262 min read


ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን በጊዜያዊነት መዝጋቷ ተሰማ ።
የካቲት 11/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ኢራን ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን በጊዜያዊነት መዝጋቷ ተሰማ ። ሰርጡ የተዘጋው *የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ* በአካባቢው የባህር ሃይል ልምምድ ስለሚያደርግ ነው ተብሏል። ልምምዱ አሜሪካ በአረብ ባህር አካባቢ ወታደራዊ አቅሟን እያደረጀች መምጣቷን ተከትሎ የሚካሄድ እንደሆነ ዘ ቴሌግራፍ ጽፏል። ዋሽንግተን አውሮፕላን ተሸኳሚ የጦር መርከብን ጨምሮ ወታደሮችን ከዘመን አፈራሽ የውጊያ መሳሪያዎች ጋር ወደ አካባቢው መላኳ ተነግሯል። የኢራን እርምጃ ሁለቱ ሀገራት አለመግባባታቸውን ለመፍታት በጄኔቫ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ላይ እያሉ የተሰማም ነው። ኢራን የሆርሙዝ መተላለፊያን ስትዘጋ እንደ ጎርጎርሳውያኑ አቆጣጠር ከ1980ዎቹ ወዲህ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል። #ሩሲያ ሩሲያ በባልቲክ ሀገራት ላይ ወረራ ከፈ
Feb 181 min read


የሶማሊላንድ አስተዳደር በግዛቷ የእስራኤል የጦር ሰፈር እንዲገነባ ተስማምቷል መባሉን ሐሰት ነው አለ፡፡
ታህሳስ 24/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ሶማሊላንድ የሶማሊላንድ አስተዳደር በግዛቷ የእስራኤል የጦር ሰፈር እንዲገነባ ተስማምቷል መባሉን ሐሰት ነው አለ፡፡ እስራኤል ባለፈው ሳምንት አርብ ለሶማሌላንድ የነጻ አገርነት እውቅና ሰጥታለች፡፡ የእስራኤል እርምጃ በሶማሌያ እና በምስራቅ አፍሪካዊቱ አገር አጋሮች ዘንድ ውግዘት አስከትሏል፡፡ የሶማሊያው ፕሬዘዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ሶማሌላንድ ከእስራኤል እውቅና ለማግኘት የጦር ሰፈር እንድትገነባ መፍቀዷን ተናግረዋል፡፡ ይሄም በደህንነት መረጃዎች የተደረሰበት ነው ማለታቸው አልጀዚራ ፅፏል፡፡ ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በተጨማሪም በእስራኤል ከጋዛ ሰርጥ የሚነቀፉ ፍልስጤማውያን በሶማሌላንድ ለማስፈር ስምምነት ተደርሷል ብለዋል፡፡ የሶማሌላንድ አስተዳደር ግን ይሄ በፍፁም ሐሰት ነው ማለቱ ተሰምቷል፡፡ እስራኤልም ለ
Jan 22 min read


ቭላድሚር ፑቲን ዩክሬይን የሰላሙን መንገድ ብትመርጥ ይሻላታል ሲሉ በድጋሚ አስጠነቀቁ፡፡
ታህሳስ 20/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ሩሲያ የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩክሬይን የሰላሙን መንገድ ብትመርጥ ይሻላታል ሲሉ በድጋሚ አስጠነቀቁ፡፡ የሩሲያው ታስ የወሬ ድርጅት የፑቲንን የከትናንት በስቲያ ማስጠንቀቂያ እወቁት ማለቱን የፃፈው ሬውተርስ ነው፡፡ የሩሲያ ጦር ሰሞኑን በዩክሬይን ላይ ሁለንተናዊ ጥቃቱን ማክፈቱ ይነገራል፡፡ ፑቲን የድጋሚ ማስጠንቀቂያቸው የተሰማው የሩሲያ ጦር በቅርቡ በዳኔስክ እና በዛፓሮዢያ ግዛቶች በያዛቸው ከተሞች እና አካባቢዎች ጉብኝት ያደረጉ የጦር አለቆችን ባነጋገሩበት አጋጣሚ ነው ተብሏል፡፡ የሩሲያው ፕሬዘዳንት ዩክሬይን ሰላሙን ካልመረጠች ለጦርነቱ ያስቀመጥነውን ግብ በጦር ሀይል ማሳካታችን አይቀርም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ጦርነቱ ያለ ሁነኛ መፍትሄ ወደ 4ኛ ዓመቱ እየታቀረበ ነው፡
Dec 29, 20252 min read


ጥቅምት 29 2018 - ጥቅምት 29 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የቡድን 20 አባል አገሮች ጉባኤ አይገኝም አሉ፡፡ የአሜሪካውፕሬዘዳንት አፍሪካ ነርስ በተሰኙት ነጭ ደቡብ አፍሪካዊያን ላይ እልቂት እና ማሳደዱ በርትቶባቸዋል የሚል ክሳቸውን እየደጋገሙት መሆኑን አናዶሉ አስታውሷል፡፡ የፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎሳ መንግስት በትራምፕ የሚቀርበውን ውንጀላ በተደጋጋሚ እያስተባበለ ነው፡፡ ትራምፕ ግን የደቡብ አፍሪካን መንግስት ጥምድ አድርገው እንደያዙት ነው፡፡ እንደውም ደቡብ አፍሪካ ከቡድን 20 አባል አገርነቷ ልትባረር ይገባል ያሉት ሰሞኑን ነው፡፡ የቡድን 20 አባል አገሮች ስብሰባ በደቡብ አፍሪካ ቢካሄድም ያለ አሜሪካ ተሳትፎ ይሆናል ተብሏል፡፡ #ማሊ በምዕራብ አፍሪካዊቱ ሀገር ማሊ
Nov 8, 20251 min read


ጥቅምት 27 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ፊሊፒንስ ፊሊፒንስን ሰሞኑን በመታት ከባድ አውሎ ነፋስ የሟቾቹ ብዛት ከ140 በላይ መድረሱ ተሰማ፡፡ አውሎ ነፋሱ በከባድ ጎርፍ እና በመሬት መንሸራተት ጭምር የታገዘ እንደነበር AFP አስታውሷል፡፡ በአደጋው ከሞቱት እና አካላዊ ጉዳት ከገጠማቸው ሌላ 127 ሰዎች ደግሞ እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም ተብሏል፡፡ ይህም የሟቾቹ ብዛት ከተጠቀሰውም በላይ ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት አሳድሯል፡፡ ሴቡ የተባለችዋ ግዛት ዋነኛዋ የአደጋው ሰለባ ነች፡፡ በግዛቲቱ የደረሰው ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ከዚህ ቀደም ከደረሱት ሁሉ በእጅጉ ከባድ ነበር ተብሏል፡፡ ጎርፉ መኪኖችን እና ትልልቅ ኮንቴይነሮችን ጭምር አንከብክቦ መጋለቡ ታውቋል፡፡ ለፊሊፒንሱ አውሎ ነፋስ ፣ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ የአየር ለውጡ በዋና ምክንያትነት እየቀረ
Nov 6, 20252 min read


ጥቅምት 25 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ኢራን የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አርጋቺ አገሬ ከአሜሪካ ጋር ወደ ኒኩሊየር ነኩ ንግግር ለመመለስ የሚያጣድፉት ጉዳይ የለም አሉ፡፡ አርጋቺ ከአሜሪካ ጋር በእኩልነት ደረጃ ካልሆነ በስተቀር አንዳችም ንግግር ማድረግ እንደማትሻ መናገራቸውን አልጀዚራ ፅፏል፡፡ አሜሪካ ኢራን በጭራሽ ዩራኒየም ማብላላት የለባትም የሚል አቋም አላት፡፡ አዲሱ የአሜሪካ የንግግር ሀሳብም በዚሁ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር ነው ይባላል፡፡ ኢራን ደግሞ ይሄን በጭራሽ አልቀበልም ባይ ነች፡፡ ምዕራባዊያኑ ኃያላን ኢራን የኒኩሊየር ቦምብ የመስራት ውጥን አላት ሲሉ ይከሷታል፡፡ ቴሕራን በበኩሏ የኒኩሊዩር መርሐ ግብሬ ለኤሌክትሪክ ማመንጫ እና ለሰላማዊ አገልግሎት የታለመ ነው የሚል መሟገቻ ታቀርባለች፡፡ #ሜክሲኮ ፔሩ ከሜክሲኮ ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጠች፡፡ ፔሩ ዲ
Nov 4, 20252 min read


ጥቅምት 12 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ካሜሩን በካሜሩን ከሳምንት በፊት በተካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ አረጋዊው የአገሪቱ መሪ ፖል ቢያ እንዳሸነፉ የቅድሚያ ውጤቱ አሳየ ተባለ፡፡ የአገሪቱ የምርጫ አከናዋኝ መስሪያ ቤት በቅድሚያ ውጤቱ ፖል ቢያ ለፕሬዘዳንታው ምርጫው ከተሰጠው ድምፅ 53 በመቶውን በማግኘት አሸንፈዋል ማለቱን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ የፖል ቢያ የቅርብ ተፎካካሪ ኢሳ ቺሮማ ባካሪ ያገኙት ድምፅ 35 በመቶ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ባካሪ ከምርጫው በኋላ በተደጋጋሚ አሸንፌያለሁ ሲሉ ሰንብተዋል፡፡ ኢሣ ቺሮማ ባካሪ ውጤቱ በወጉ ይጣራልኝ ማለት መጀመራቸው ተሰምቷል፡፡ የ92 አመቱ አረጋዊ ፖል ቢያ የምርጫ ድላቸው ከፀናላቸው የ42 አመታት መሪነታቸውን በመ5 ዓመታት ይጨምርላቸዋል ተብሏል፡፡ የአገሪቱ ህገ መንግስታዊ ምክር ቤት ይፋዊ ውጤቱን ሰሞኑን እወቁት እንደሚል በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
Oct 22, 20252 min read


መስከረም 26 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ሶማሊያ የሶማሊያው ፅንፈኛ ቡድን /አልሸባብ/ በርዕሰ ከተማዋ ሞቃዲሾ በሚገኝ እስር ቤት ላይ ጥቃት መፈፀሙ ተሰማ፡፡ በአልሸባብ ታጣቂዎች ጥቃት ደርሶበታል የተባለው የእስር ማዕከል በአገሪቱ ቤተ መንግስት አቅራቢያ...
Oct 6, 20252 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page
_edited.jpg)
