top of page

ሰኔ 14 2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች

  • Jun 21, 2025
  • 2 min read

 

የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አርጋቺ እስራኤል በአገራችን ላይ የከፈተችውን ጥቃት ካላቆመች በፍጹም ወደ ኒኩሊየር ነኩ ድርድር በጭራሽ አንመለስም አሉ፡፡

 

አባስ አርጋቺ የአገራቸውን አቋም እወቁልን ያሉት በዚሁ ጉዳይ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ከአውሮፓ አገሮች አቻዎቻቸው ጋር በተነጋገሩበት ወቅት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡

 

አውሮፓውያኑ ኢራን ከአሜሪካ ጋር ቀደም ሲል ከአሜሪካ ጋር ኒኩሊየር ነኩን ድርድር እንድትቀጥል አርጋቺን አበክረው ጠይቀዋቸዋል፡፡

 

እስራኤል እና ኢራን ትናንት ሌሊቱንም አንዷ በሌላዋ ላይ ከበድ ከበድ ያሉ ጥቃችን መሰንዘራቸው ተሰምቷል፡፡

የእስራኤል ጦር በኢራን የሚሳየል ማከማቻዎች እና መተኮሻዎችን ዒላማ ያደረጉ ድብደባዎችን ፈፅሜያለሁ ብሏል፡፡

 

በኢራንም የሚሳየል ድብደባ በቴል አቪቭ አቅራቢያ ከፍተኛ ፍንዳታ ተሰምቷል መባሉ ተጠቅሷል፡፡

 

የእስራኤለ ጦር ኤታ ማጆር ሹም ኢያል ዛሚር አገራቸው ከኢራን ጋር በጀመረችው ግጭት ለተራዘመ ዘመቻ ዝግጁ መሆኗን እንደተናገሩ መረጃው አስታውሷል፡፡

 

 

የኒጀር ወታደራዊ መንግስት በፈረንሳዊ ኩባንያ ባለቤትነት ስር የሚገኝን የዩራኒየም ማዕድን ማምረቻ ወደ ብሔራዊ ሐብትነት አዞረዋለሁ አለ፡፡

 

በኒጀር ወታደራዊ መንግስት ተወርሶ ወደ ብሔራዊ ሀብትነት የሚዞረው ሶሚየር በተባለው ፈረንሳዊ ኩባንያ ባለቤትነት ስር ሲተዳደር የቆየ የዩራኒየም ማምረቻ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡

 

መንግስት የማዕድን ኩባንያውን የሚወርሰው ያልተገቡ ተግባራትን እየፈፀመ ነው በሚል ምክንያት መሆኑ ታውቋል፡፡

 

በኒጀር የጦር አለቆች በመንግስት ግልበጣ ስልጣን ከያዙ ወዲህ አገሪቱ ከቀድሞዋ ቅኝ ገዢዋ ጋር ያላትን ግንኙነት በእጅጉ እየደፈረሰ መምጣቱ ይነገራል፡፡

 

ኒጀር በቀጠናው ሰፍረው የነበሩ የፈረንሳይ ወታደሮችን ሙሉ በሙሉ ካስወጡት መካከል አንዷ ነች፡፡

 

ምእራብ አፍሪካዊቱ ኒጀር በአለም ላይ ከከፍተኛ የዩራኒየም ማዕድን መገኛዎች አንዷ እንደሆነች መረጃው አስታውሷል፡፡

 

ዩራኒየም ለኒኩሊየር የኤሌክትሪክ ማመንጫ እና በከፍተኛ ደረጃ የተብላላው ደግሞ ለኒኩሊየር ቦምብ መስሪያነት ይውላል፡፡

 

 

የየመን ሁቲዎች አሜሪካ በእስራኤል ተደራቢነት ኢራን በጦር የምትመታ ከሆነ እኛም ጥቃታችንን እንቀጥላለን ሲሉ ዛቱ፡፡

 

ሁቲዎቹ በቀይ ባህር ተላላፊ መርከቦች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ያቆሙት ከአሜሪካ ጋር በደረሱት የተኩስ አቁም እንደነበር አልጀዚራ አስታውሷል፡፡

 

የየመንን ሰሜናዊ ክፍል የሚያስተዳድሩት ሁቲዎቹ ከኢራን በተጓዳኝ እኛም በእስራኤል ላይ ሮኬቶችን እየተኮስንባት ነው ብለዋል፡፡

 

ሁቲዎቹ ቀደም ሲል የእስራኤል እና የአጋሮቿ ናቸው ባሏቸው የቀይ ባሕር ተላላፊ መርከቦች ላይ ጥቃት ሲሰነዝሩ የቆዩት ለጋዛ ፍልስጤማውያን አጋርነታቸው ለማሳየት አልመው ነው ይባላል፡፡

 

የሁቲ ታጣቂዎች ሁነኞቹ የኢራን የጦር እና የፖለቲካ አጋሮች መሆናቸው ይነገራል፡፡

 

የኔነህ ከበደ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

 

Recent Posts

See All
የሐምሌ 23 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ግብፅ በግብፅ የሜዴትራኒያን የባህር ዳርቻ የነበረ የአሜሪካ የጋዝ ማጠራቀሚያ መርከብ በድሮን ተመታ ተባለ፡፡ ሁለት የደህንነት ምንጮች መርከቡ በድሮን እንደተመታ አረጋግጠውልኛል ሲል ሬውተርስ ፅፏል፡፡ መርከቡ በድሮን እንደተመታ በእሳት መያያዙ ታውቋል፡፡ ቃጠሎው ወደ ሌላ መርከብም ተጋብቶ ነበር ተብሏል፡፡ ኋላ ግን

 
 
 
የሐምሌ 22 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#አሜሪካ አሜሪካ እና ሳውዲ አረቢያ ኢራቅ ውስጥ በአፍቃሪ ኢራን ታጣቂዎች ይዞታ ላይ ድብደባ ፈፀሙ፡፡ ሰሞኑን ሳውዲ አረቢያ በኢራቅ የሚገኙ አፍቃሪ ኢራን ታጣቂዎች በድሮን ጥቃት አድርሰውብኛል ስትል እንደነበር አልጀዚራ አስታውሷል፡፡ ሳውዲ ጥቃቱን ከማውገዝ በተጨማሪ መበቀሌ አይቀርም በሚል ዝታ ነበር፡፡ በኢራቆቹ አ

 
 
 
የሐምሌ 21 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ጃፓን የጃፓን ደቡባዊ ምዕራብ ክፍል በርዕደ መሬት ተመታ፡፡ ርዕደ መሬቱ የደረሰው ኩማማቶ የተባለው የአገሪቱ ክፍል እንደሆነ ኒኪ እስያ ፅፏል፡፡ የመሬት ነውጡ የተቀሰቀሰው ከምድር በ10 ኪሎ ሜትር ጥልቀት መሆኑ ታውቋል፡፡ ነውጡ በርዕደ መሬት መለኪያ /ሬክተር ስኬል/ 7 ነጥብ 1 ሆኖ መመዝገቡ ታውቋል፡፡ ቀደም ሲ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page