top of page

በኢትዮጵያ የንግዱን ማህበረሰብ እየገጠሙ ካሉ ችግሮች 40 በመቶ ያህሉ ከገንዘብ አቅርቦት ጋር የተገናኙ ናቸው ተባለ ።

  • 2 hours ago
  • 1 min read

መጋቢት 3/2018


በኢትዮጵያ የንግዱን ማህበረሰብ እየገጠሙ ካሉ ችግሮች 40 በመቶ ያህሉ ከገንዘብ አቅርቦት ጋር የተገናኙ ናቸው ተባለ ።


በአጠቃላይ በኢትዮጵያ 2 ሚሊየን የሚጠጉ ጥቃቅን ፣ አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ኢንዱስትሪ ተቋማት እንዳሉ ተነግሯል።


የእነዚህ ኢንዱስትሪ ባለቤቶችና ኢ-መደበኛ በሆኑ ሌሎች ንግዶች የተሠማሩ ሰዎች በአጠቃላይ የብድር ፍላጎታቸው በአገሪቱ ባሉ ሁሉም ባንኮችና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ተቆጥቦ ከሚገኘው ገንዘብ ግማሽ ያህሉን ይሆናል ተብሏል።


በኢትዮጵያ ባሉ ባንኮችና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ተቆጥቦ ያለ አጠቃላይ ገንዘብ 3.7 ትሪሊዮን ብር እንደሆነ የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በካፒታል ሆቴል እያካሄደው ባለው ውይይት ላይ ሲነገር ሠምተናል።


በውይይቱ ላይ የንግዱ ማህበረሰብ ስለሚገጥመው የመስሪያ ቦታ አቅርቦት ችግርም ተነስቷል።


የመስሪያ ቦታ ማግኘት ብዙ ሂደትን ማለፍ የሚጠይቅ ተግባር እንደሆነ ተነግሯል።


አንድን ቦታ ህጋዊ በሆነ መንገድ በሊዝ የገዛ ግለሰብ በሚቀጥለው ቀን መልሶ መሸጥ ቢፈልግ 24 ሂደቶችን ወይም መስፈርቶችን ማለፍ ይጠበቅበታል ተብሏል።


ምክር ቤቱ "ቀልጣፋና አስተማማኝ የፋይናንስና የመስሪያ ቦታ አቅርቦት ለፈጣን ኢንቨስትመንትና ልማት" በሚል ባዘጋጀው መድረክ ላይ በተለያዩ ባለሞያዎች የመነሻ ፅሁፎች ቀርበዋል።


ታሳታፊዎችም ከብድር እና ከቦታ አቅርቦት ጋር በተገኘ ይታያሉ ያሏቸውን ጥያቄዎችም አንስተዋል።


ንጋቱ ረጋሳ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page