top of page

በየሳምንቱ 1 ሚሊዮን ሰዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እየተመዘገቡ ነው ተባለ።

  • 2 hours ago
  • 1 min read

መጋቢት 1/2018

በየሳምንቱ 1 ሚሊዮን ሰዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እየተመዘገቡ ነው ተባለ።


በአሁኑ ሰዓት በአጠቃላይ የፋይዳ መታወቂያ የተመዘገቡ ሰዎች ቁጥር 37.5 ሚሊዮን መድረሱን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ፅ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ አርአያስላሴ ተናግረዋል።


ዋና ዳሬክተሩ ይህን ያሉት ፅ/ቤታቸው ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር በመተባበር ለግል መገናኛ ብዙኀን ፋይዳ መታወቂያ በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።


እስከ መጪው ሰኔ ወር ድረስ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝጋቢዎችን ብዛት 90 ሚሊዮን ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነ አቶ ዮዳሄ አስረድተዋል።


የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመልካም አስተዳደር፣ ለማህበራዊ እና ደህንነት ጉዳዮች ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው በፕሮግራሙ ላይ ሲነገር ሰምተናል።



በዚህም በጥቅል ሀገራዊ ምርት ወይንም GDP 6 በመቶ እንደሚያበረክትም ተጠቅሷል።


የባንክ አገልግሎቶችን ለማግኘት አና በመደበኛ አኮኖሚ ውስጥ ለመሳተፍ፣የቴሌኮም አገልግሎቶችን ለማግኘት፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ለማግኘት አንደ ቅድመ ሁኔታ በመሆን የማንነት ማጭበርበርን በመከላከል ዲጂታላይዝድ አግልግሎቶችን ለማቀላጠፍ መታወቂያው እንደሚጠቅም ሲነገር ሰምተናል።


ከዚህ በተጨማሪም በሰነዶች ምዝገባ እና ማረጋገጫ አገልግሎት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማግኘት፣ ተማሪዎች አንድ ዋና የተማሪ መታወቂያ፣ የሀገር አቀፍ ፈተና መለያ አንዲሁም እንደ ቤተ-መጻህፍት አገልግሎት ያሉ የትምህርት አገልግሎቶችን ለማግኘት ያስችላል ተብሏል።


ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ማንኛውም ስደተኞች ፋይዳ መታወቀያን በመጠቀም ሁሉንም በሀገሪቱ የሚገኙ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ሌላኛው የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጠቀሜታ መሆኑ ተጠቅሷል።


ይህ የፋይዳ መታወቂያ እነዚህንና ሌሎች በርካታ ጥቅሞች ቢሰጥም ምዝገባውን በጥርጣሬ የሚያዩት ፣ እንደ CCTV ካሜራ የሚመለከቱ አሉ ተብሏል።


ይህንንን የግንዛቤ ችግር ለመፍታትና በመጪው ሰኔ 90 ሚሊዮን ሰዎች ለመመዝገብ ሚዲያዎች ግንዛቤ በመፍጠር አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ተጠይቋል።


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page