top of page

የዱር እንስሳት አደንና ሽያጭ ፣ የፓርኮች መራቆት፣ ግጭት እና የፋይናንስ እጥረት የዱር እንስሳትና የፓርኮች ጥበቃ ስራ ፈተና ሆኗል ተባለ።

  • Mar 12
  • 1 min read

መጋቢት 3/2018


የዱር እንስሳት አደንና ሽያጭ ፣ የፓርኮች መራቆት፣ ግጭት እና የፋይናንስ እጥረት የዱር እንስሳትና የፓርኮች ጥበቃ ስራ ፈተና ሆኗል ተባለ።


ይህ የተባለው የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የተመሰረተበትን 60ኛ ዓመት ዛሬ ሲያከብር ነው።


የቱሪዝም ሚኒስትር ድኤታው አቶ ስለሺ ግርማ የኢኮ ቱሪዝምና የብርቅዬ እንስሳት ቱሪዝም ኢትዮጵያ ውስጥ እየሰፋ መጥቷል ብለዋል።


ላለፉት 60 ዓመታት ህገወጥ የዱር እንስሳት አደንና ሽያጭ፣ የፓርኮች መራቆት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የፋይናንስ እጥረት ዘርፉን ሲገጥሙት የነበሩ ችግሮች ናቸው ተብሏል።

የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ በኢትዮጵያ 30 ፓርኮች፣ ከ90 በላይ ጥብቅ ስፍራዎች ስለመኖራቸው ተናግረዋል።


ከነዚህ ውስጥ የባሌ ብሔርራዊ ፓርክና ሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የአለም ቅርስ ተብለው በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የተመዘገቡ መሆናቸውን አስታውሰዋል።


ፓርኮቹና የዱር እንስሳቱ እየገጠማቸው ስላለው ችግር ያነሱት ሀላፊው የዱር እንስሳቱና ፓርኮቹ የበለጠ እንዲጠበቁ የአካባቢው ማህበረሰብ ከዚያ ተጠቃሚ መሆን አለበት ተብሏል።


በረከት አካሉ

Recent Posts

See All
የሐምሌ 18 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ስፔን በስፔኗ ርዕሰ ከተማ ማድሪድ አቅረቢያ ነዋሪዎች በመዛመት ላይ በሚገኘው ከባድ የሰደድ እሳት ምክንያት ለቅቀው እንደወጡ ታዘዙ፡፡ የማድሪድ ምዕራባዊ ክፍል አቅራቢያ የሰደድ እሳቱ በጣሙን ያየለበት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ እስከ ትናንት ምሽትም ከ19 ሺህ በላይ ሰዎች ለቀው መውጣታቸው ተጠቅሷል፡፡ በስፔን ወቅታ

 
 
 

1 Comment


Daily Harry
Daily Harry
Mar 19

Geometry Dash PC offers colorful visuals, intense music, and addictive gameplay, making each level a thrilling challenge that tests your skill and patience.

Edited
Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page