top of page

መጋቢት 2/2018 - ከፍተኛ ትችት የቀረበባቸው እና የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ ደንብ ላይ የተካተቱ የህግ ክፍሎች እንዲሻሻሉ ቢጠየቅም አዋጁ ስለጸደቀ ድንጋጌዎችን ማሻሻል አይቻልም ተባለ።

  • 24 minutes ago
  • 3 min read

መጋቢት 2/2018


ከፍተኛ ትችት የቀረበባቸው እና የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ ደንብ ላይ የተካተቱ የህግ ክፍሎች እንዲሻሻሉ ቢጠየቅም አዋጁ ስለጸደቀ ድንጋጌዎችን ማሻሻል አይቻልም ተባለ።


ይህን ያለው የገንዘብ ሚኒስቴር ነው።


የገንዘብ ሚኒስቴር መጋቢት ትላንት፤ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ለጸደቅው የግቢ ግብር ማስፈጸሚ ረቂቅ ደንብ ላይ በመስሪያ ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሞያ፣የስራ እና የድርጅት ተወካይዎች ጋር ከ5 ሰዓት በላይ የፈጀ ወይይት አካሂዷል ።


በወይይቱ ላይ ጥያቄ ካቀረቡት ከ20 በላይ ተሳታፊዎች ውስጥ የሚበዙት ተመሳሳይ ጥያቄ እና ሀሳብ ስጥተዋል ።


የተጣለው የ2.5 በመቶ የአማራጭ አነስተኛ ግብር እንዲነሳ፣ድርጅቶች ወይንም ተቋማት የሂሳብ መዝገብ እንዲይዙ ያሚያስገድድው የህግ ከፍል እና በየሩብ ዓመት ግብር እንዲሰበሰብ የሚያዘው የህግ ከፍል ይሻሻል የሚለው ጉዳይ ተደጋግሞ ተነስቷል ።


ይህን ጥያቄ ካነሱት ወይንም ከተቹት ወስጥ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ፣የስጋ ላኪዎች እና አምራቾች ፣የኮንስትራክሽን ዘርፍ ፣ የፋይናንስና ኢንሹራንስ ፣የዲቄት አምራች ማህበራት ፣ የህግ እና የሂሳብ በለሙያዎች ይገኙበታል።


ከኢትዮጵያ የዱቄት እና የዱቄት ውጤቶች ማህበር ተወክለው በወይይቱ ላይ መሳተፋቸውን የተናገሩት አቶ አብዱልሃኪም ፤ ልክ ውሃ እና ኤሌክትሪክ የሚያቀርቡ ተቋማት ከአነስተኛ አማራጭ ግብር ነጻ እንደተረጉት ሁሉ የዱቄቱም ነጻ መደረግ አለበት ምክንያቱም መሰረታዊ ፍጆታ ስለሆነ ብለዋል።


ዘርፉ በበርካታ ችግሮች ውስጥ መኖሩን የጠቀሱት ተሳታፊው ይህ ካልተስተካከለና 2.5 በመቶ አማራጭ አነስተኛ ግብር የሚጣል ከሆነ ካሉት ችግሮች ጋር ተዳምሮ በርካታ ፍብሪካዎች ከስራ የሚወጡበት ሁኔታ ሊፈጥር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ተናግረዋል ።


ከደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ዘርፍ ተወክለው በውይይቱ ላይ መታደማቸው የተናገሩት ወ/ሮ እንቁጣጣሽ ፍቃዱ በማሻሻያ ደንቡ ላይ የተደነገገውን የአማራጭ አነስተኛ ታከስ እና በረቂቁ የሂሳብ መዝገብ መያዝ ግዴታ የሚደርገውን የህግ ክፍል ተቃውመዋል።



በረቂቁ ደንቡ አንቀጽ 36 ላይ ሃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር እና የጋራ ኢንቨስትመንት ፈንድ የድርጅት ደረጃ ግብር የመክፈል ግዴታ የሌለባቸው ቢሆንም ከአባሎቻቸው ስብስበው ገቢ ለሚያደርጉት ግብር አፈጻጸም የሂሳብ መዝገብ የመያዝ እና ይህንንም መዝገብ በግብር ዓመቱ መጨረሻ ለታክሱ ባለስልጣን ማቅረብ እንዳለባቸው ግዴታ ይጥላል።


ለደረቅ ጭነት ዘርፍ የሂሳብ መዝግብ መያዝ "በፍጹም የማይቻል ነው"ያሚሉት ወ/ሮ እንቁጣጣሽ ይህን ስንል በማስረጃ በማቅረብ ነው ሲሉ አክለዋል።


ዘርፉ ክፍለ አገራትን እና ድንበሮችን አቋርጦ የሚሰራ ቢሆንም በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ እንኳን ምንም አይነት ስርዓት እንዳልተዘረጋለት አስረድተዋል።


በዚህም ምክንያት ከአንድ ምልልስ ከሚገኘው ገቢ ከ80 እስከ85 በመቶ በአማከኝ ቀጥተኛ ወጪ ነው ፤ለዚህ ደግሞ ምንም አይነት ሰንድ ወይም ደረሰኝ ማቅረብ የሚቻልበት አውድ አንደሌለ ይታወቃል ሲሉ ተሳታፊዋ አክለዋል።


በተጨማሪም በጂቡቱ መኪኖች በቀላል አደጋዎች ይወድቃሉ ከኢትዮጵያ ክሬን ወስዶ ማንሳት ስለማይቻል በጂቡቲ ለሚገኙ አንሺዎች ባንክ ስለሌለ በጥቁር ገብያ ምንዛሬ ተሰልቶ ለአንድ መኪና እስከ 1 ሚሊዮን ብር ድረስ እየተከፈለ ይነሳል ይህም ሲሆን ደረሰኝ የለም፤ ታዲያ በዚህ ሁኔታ ወስጥ እንዴት ነው የሂሳብ መዝገብ መያዝ የሚቻለው ሲሉ ጠይቀዋል ።


ከኮንስትራክሽን ዘርፍ ተወክለው መሳተፋቸውን የተናገሩ ሌላ ተሳታፊ በበኩላቸው የአማራጭ የአነሰተኛ ግብር የቤት ዋጋ እንዳይቀመስ ከማድረጉም በላይ የአገር ውስጥ ተቋረጮችን ከገብያ የሚያርቅ ነው ሲሉ ተችተዋል ።


በተለያዩ ግዚያት ክፍያዎች እያደጉ መምጣታቸውን ያስታወሱት ተሳተፊው አሁን ደግሞ አማራጭ አነስተኛ ግብር 2.5 በመቶ ሲታሰብ የግብታ ዋጋ እንዳይቀመስ ያደርጋል ሲሉ አስረድተዋል ።


ለምሳሌ በመቶ ብር የተወሰደ እንድ ፕሮጀክት 7 በመቶ ሪቴንሽን ይይዝበታል፣ 7.5 በመቶ የቫት ዊዝሆልዲግ ይያዝበታል፣3 በመቶ ደግሞ ዊዝ ሆልዲንግ ይያዝበታል በዚህ ላይ የዋጋ ንርት 9 በመቶ አለ ይህ ሲደማር 30 ይሆናል ብለዋል።


በዚህም የ100 ብር ስራ አንድ ተቋራጭ በ10 ብር ትርፍ ቢወስደ 140 ነው የሚሆነው ይህም የቤትንም ፣የመሰረተ ልማትንም ዋጋ ተመጣጣኝ አያደርገውም ፤አለሚዎችም ኢትዮጵያን እንዳይመርጡ ያደርጋቸዋል ሲሉ አክለዋል።


የገንዘብ ሚኒስቴር በበኩሉ እንዚህን የተነሱት ሃሳቦች በገቢ ግብሩ አዋጁ ላይ የተደነጉ እና በደንብ ሊሻሩ የማይቻሉ ናቸው ብሏል።


ይሁንና የተሰጡ ምክር ሃሳቦችም እንደ ግብዓት እወስዳለሁ ብሏል።


በሚኒስቴሩ የታክስ አማካሪ አቶ ዋሲሁን አባተ ከዚህ በፊት ከነበሩ ወይይቶች የተሻለ የሰው ቁጥር መገኘቱን ተናግረው በአዋጅ ላይ በግልጽ የተደነገን ነገር በደንብ ሊያሻሽለው እንደማይችል መታወቅ ሲሉ አለበት ሲሉ አስረድተዋል ።


ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የተሰጡ የተወሰኑ ኃላፊነቶች አሉ በእነዚህ እና አዋጁን ግልጽ ማድረግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ እንጂ አዋጁን መጋጨት አንችልም ብለዋል አማካሪው።


ከአማራጭ አነስተኛ ግብር ነጻ የሆኑትን በደንቡ መዘርዘር ነው እንጂ ሌሎች ይህኛውም መስክ ይዘለል የሚለውን መወሰን የእኛ ሃላፊነት አይደለም ብለዋል።


ስለዚህም በመሰል ጥያቄዎች ጋር ልንሄድባቸው አንችልም ምክንያቱም ከአዋጁ ጋር ይቃረናሉ ወደፊት ለሚደጉ ወይይቶች ግን ግብዓት ይሆናል፣ ያኔ ሊታይ ይችላላ ብለዋል አቶ ዋሲሁን።


ከአዋጁ ጋር የሚቀረኑ ምክረ ሃሳቦችም አንቀበልም እኛ ብንቀበልም የፍትህ ሚኒስቴር ይጥለዋል ብለዋል አቶ ዋሲሁን።


የሂሳብ መዘግብ በተመለከተ ለቀረበው ጥያቄ" አከሌ"የሂሳብ መዝገብ አያዝ የሚለውን ለመወሰን የሚንስትሮች ምክር ቤት ስልጣን እንደሌለው የጠቆሙት አቶ ዋሲሁን ልናደርግ የምንችለው መዝገብ አያያዙን ምቹ እንዲሆን ማድርግ ፣ዝርዝር መመሪያዎችም በሚዘጋጁበት ወቅት ደረሰኝ በማያገኙበት ወቅት የሚያስረዱበትን ሁኔታ መፍቀድ እንጂ ይህ ዘርፍ የተለየ ስለሆነ ብቻ አንዱ የሂሳብ መዝግብ አይዝም ፣ያኛው ደግሞ ይይዛል ማልት አይቻልም ብለዋል።


ያሬድ እንዳሻው

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page