ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ በ16 ጉዳዮች ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረክ ማካሄድ እንደሚጀምር ምርጫ ቦርድ ተናገረ።
- 12 minutes ago
- 1 min read
የካቲት 30/2018
ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ በ16 ጉዳዮች ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረክ ማካሄድ እንደሚጀምር ምርጫ ቦርድ ተናገረ።
ቦርዱ ይህን ያለው ባለፈው ቅዳሜ በኢዲስ ኢንትርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር የሲቪል ማህበረሰብ ደርጅቶች ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያላቸው ድርሻ በሚል ርዕስ በተሰናዳ የወይይት መድረክ ላይ ነው።
ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ አካታች እና ታዓማኒ ምርጫ ለማካሄድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምን እያሰራ ነው? የሚል ጥያቄ በወይይቱ ላይ ለምርጫ ቦርድ ቀርቧል።
ቦርዱን ወክለው በውይይቱ ላይ የታደሙት የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ነዋይ የመራጮች ምዝገባ በአንዳንድ ክልሎች መጀምሩን እና የዕጩዎች መዝገባ መጠናቀቁን ተናግረዋል።
አቶ ተስፋዬ ነዋይ ዘንድሮ ቦርዱ እሰራለሁ ያለው ትልቁ ስራ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚከራከሩት መድረክ ማዘጋጀት እንደሆነ ጠቁመዋል።

አሁን በቴሌቪዥኖች የሚተላለፍ የተለያዩ የክርክር መድረኮች መኖራቸውን ያስታወሱት ምክትል ሰብሳቢው እነዚህ መድረኮች ሚዲያዎቹ በራሳቸው ተነሳሽነት የሚያደርጓቸው ክርክሮች ናቸው፤ የራሳቸው ደካማ እና ጠንካራ ጎን አላቸው ሲሉ አስረድተዋል።
በዚህም ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደሩ 47 የሚሆኑ ፓርቲዎች የሚከራከሩበት "በጣም የተደራጃ መድረክ" ለህዝቡም በቂ መረጃ የሚሰጥ "ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዳቀረቡትም እጩ ብዛት የክርክር የሚያደርጉበት መድረክ እያዘጋጀን ነው ሲሉ አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል።
ቦርዱ ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ በ16 ርዕስ ጉዳዬች ላይ የሚዘጋጁ የክርክር መድረኮችን ለህዝቡ መገናኛ ብዙሃን ጨምሮ በተለያዩ ቋንቋዎች እና ዘዴዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ ይደረጋል ብሏል።
ይህም መራጩ ስለ ፓርቲዎቹ "በቂ ግንዛቤ" ኖሮት እንዲመርጥ ለማድረግ ያግዛል ሲል ምርጫ ቦርድ አክሏል።
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments