top of page

በስራቸው ውጤታማ የሆኑ የአዲስ አበባ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የቆይታ ጊዜያቸው

  • 10 hours ago
  • 1 min read

መጋቢት 7/2018


በስራቸው ውጤታማ የሆኑ የአዲስ አበባ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የቆይታ ጊዜያቸው ቢያበቃም በተሰጣቸው የማምረቻ ቦታ ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲሰሩ በከተማዋ ካቢኔ ከሠሞኑ እንደተፈቀደላቸው ተነገረ።


የከተማ አስተዳደሩ በ43 ሄክታር መሬት ላይ ያስገነባቸባቸውን የማምረቻ ሼዶች በቅርቡ ለመካከለኛ እና አነስተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ሊያስረክብ እንደሆነም ሠምተናል።


በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የተሰማሩ አንቀሳቃሾች በተሰጣችሁ የማምረቻ ቦታ ላይ ለአምስት ዓመት ከሰራችሁ በኋላ ፤ ለሌሎች መልቀቅ አለባቸው የሚለው መመሪያ ስጋት ላይ እንደጣላቸው ተናግረዋል፡፡


በአንዳንድ አካባቢዎች የተፈቀደላችሁ ጊዜ አብቅቷል በሚል ሼዶች እየታሸጉ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ከሠሞኑ ባዘጋጀው አንድ መድረክ ላይ የተገኙ የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተናግረዋል፡፡


የከተማዋ ኢንዱስትሪ ቢሮ በበኩሉ ከ1997 ጀምሮ ሼድ ይዘው እየሰሩ የሉ አንቀሳቃሾች መኖራቸውን በጥናት አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡


የተሻለ የስራ ዕድል የፈጠሩ እና ለውጪ ገበያ ምርቶቻቸውን የሚያቀርቡ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ለተጨማሪ አንድ አመት በያዙት ቦታ እየሰሩ እንዲቀጥሉ በከተማዋ ካቢኔ ከቀናት በፊት መወሰኑንም በቢሮ ሃላፊ ደረጃ የአምራች ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት አቶ ጳውሎስ ሢሣይ ተናግረዋል፡፡


ኢንዱስትሪዎቹ የማምረት አቅማቸው እየታየ የተሻለ የማምረቻ ቦታ እንደሚሰጣቸውም አቶ ጳውሎስ ተናግረዋል፡፡


የከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ ለሚደራጁ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪ አንቀሳቃሾች በ43 ሄክታር መሬት ላይ ያስገነባቸባቸውን ፤የማምረቻ ሼዶች በቅርቡ እንደሚያስረክብም አቶ ጳውሎስ ተናግረዋል፡፡


የከተማ አስተዳደሩ አሁን ላይ ከአራት ሺህ በላይ ሼዶችን በሁሉም ክፍለ ከተሞች ገንብቶ አንቀሳቃሾች እንዲሰሩበት እያደረገ ይገኛል ተብሏል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ንጋቱ ረጋሣ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page