በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ዓመታት በነበሩ ግጭቶች ከ300 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው እንደነበር ተነግሯል።
- 1 hour ago
- 1 min read
የካቲት 26/2018
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ዓመታት በነበሩ ግጭቶች ከ300 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው እንደነበር ተነግሯል።
ይህም የክልሉን አጠቃላይ 20 በመቶ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ማራቁን የክልሉ ምክትል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በሽር አብዱረሂም ተናግረዋል።
አሁን ላይ ግን በክልሉ በተሰሩ ስራዎች በአብዛኛው በሚባል ደረጃ ትምህርት ቤቶች ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደታቸው መመለሳቸውን ኃላፊው አንስተዋል።
ኃላፊው ይህንን ያሉት ኩሶ ኢንተርናሽናል የተባለ የተራድኦ ተቋም በክልሉ ባለፉት 6 ዓመታት ሴት ተማሪዎችን ለዩንቨርሲቲ የማብቃት ፕሮጀክት (U_Girls project) የማጠቃለያ መድረክ ላይ ነው።
የትምህርት ቢሮ ኃላፊው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመማር ማስተማር ችግሮችን በመፍታት ሂደት ውስጥ የኩሶ ኢንተርናሽናልን አስተዋፅኦ አንስተዋል።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኩሶ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ ወንድወሰን ከበደ በክልሉ በ4 ወረዳዎች በሚገኙ 7 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሰራነው ሥራ ከ1000 ሴት ተማሪዎች 84 በመቶዎችን ለዩንቨርሲቲ አድርሰናል ብለዋል።
በቤንሻንጉል ጉሙዝ በተሰራው ሥራ ኩሶ ኢንተርናሽናል ሴት ተማሪዎች ላይ አተኩሮ በሚሰራው ሥራ በአጠቃላይ 28 600 በላይ ሰዎችን ተደራሽ መደረጉን አቶ ወንድ ወሰን አንስተዋል።
ከ1886በላይ ሴት ተማሪዎች የህይወት ክህሎት ስልጠና መውሰዳቸውን የጠቀሱት ኃላፊው መምህራንና የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች የፆታ ተኮር ስርዓት ትምህርት ስልጠና መውሰዳቸውን ተናግረዋል።
ኃላፊ በክልሉ በተደጋጋሚ የሚታዩ ግጭቶች፣የማህበረሰብ የግንዛቤ ዕጥረት እና ኢኮኖማያዊ ችግሮች ሴቶች በትምህርታቸው እንዳይገፉበት እያደረጓቸው ነው ያሉ ሲሆን ችግሩን ለመቀነስ ከዚህ በበለጠ ብዙ መሰራት እንዳለበት አንስተዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7

