በኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢን መሰረት ያደረገ ገቢ ግብር ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል?
- 1 hour ago
- 2 min read
መጋቢት 2/2018
በኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢን መሰረት ያደረገ ገቢ ግብር ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል?
የአገሪቱ ኢኮኖሚው የሚመነጨውን ያክል ገቢ እየተሰበሰበ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ሲነገር ይሰማል።
በዚህም የተነሳ የታክስ አይነቱ በላይ በላዩ ሆኖ ይታያል።
የገንዘብ ሚኒስቴር በጠራው በገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ ደንብ ወይይት ላይ የተገኙት የተመሰከረለት የሂሳብ ባለሞያው አቶ አወቀ አስፋው ኢኮኖሚያችንን ብናያው ሲሉ ይመክራሉ፡፡
በለሙያው በአገሪቱ ኢኮኖሚው የሚመነጨውን ያክል ገቢ እየተሰበሰበ አይደለም የሚል ሃሳብ ሁሌ እንደሚነሳ አስታውሰው፤ በቅርብ በተሰሩ እና በወጡ መረጃዎች መሰረት ኢትዮጵያ በህዝብ ብዛት 138 ሚሊዮን በመያዝ ከ233 አገራት 10ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ይህም ትልቅ ቁጥር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የጥቅል ዓመታዊ ምርታችን ደግሞ 109 ቢሊዮን ዶላር ነው ፤ ይህ ከአለም ከ 218 አገራት 72 ኛ ደረጃን ይይዛል ፤ በዚህም በጥናቱ ከተካተቱ 218 አገራት 2 መቶኛ ደረጃ ላይ ነው የምንገኘው ሲሉ አክለዋል፡፡
አቶ አወቀ "ብዙ ግዜ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚው የሚመነጨውን ያክል ገቢ እየሰበሰብን አይደለም ብልን ስንነሳ የነፍስ ወከፍ ገቢን አናይም የኢትዮጵያ ከ218 አገር 200ኛ ነው "ብለዋል፡፡
ግብር ለማስከፈል ስንነሳ ይህን ህብረተሰብ ነው የሚለውን ብታይውት ጥሩ ነው ሲሉ ምክራቸው አካፍለዋል፡፡
ለምን ከተባለ ህበረተሰቡ የሚመጣውን ለውጥ ሁሉ በጥሩ እንዲቀበል ለማድረግ እና እናተም በመንግስት ወገን ብቻ ሳይሆን በማህበረሰቡ ወገን ሆናቸው እንድተገነዘቡ ሲሉ አክለዋል፡፡
ለተነሳው ሃሳብ ምላሽ የሰጡት በገንዘብ ሚኒሴርት የታከስ ጉዳዎች አማካሪ አቶ ዋሲሁን አበተ የአሰራሩን መለኪያ ያወጣቸው ኢትዮጵያ እንዳልሆነች እና አሰራሩ በአለም ደርጃ ተቀባይነት አግኝቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ስራ እንዲገባ ያበረከተው አይ ኤም ኤፍ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ሰለዚህም የአንድ አገር የታክስ ውጤት መለኪያው ከአመታዊ ጥቅል ምርት ወይንም GDP ጋር ነው ብለዋል አቶ ዋሲሁን፡፡
ዋናው ነግር መንግስት አጠቃላይ ኢኮኖሚው ከሚመነጨው ሃብት ውስጥ ስንቱን ወሰደ ነው እንጂ እያንዳንዱ ግለሰብ ከተከፈለው የነፍስ ወከፍ ገቢ ይሰብሰብ የሚል መለኪያ የለም፣ ስለዚህ ኢትዮጵያ ላይ የተለየ ተዓምር ልናመጣ እንችልም ሲሉ አማካሪው አስረድተዋል፡፡
በገንዘብ ሚኒሴርት የታከስ ጉዳዎች አማካሪ አቶ ዋሲሁን አበተ አለም የሚሰራበት ተቀባይነት ያገኘው የታወቁ ኢኮኖሚስቶችም ወደ ስራ ያስገቡት ከጥቅል ዓመታዊ ምርትን መሰረት ተደርጎ እንዲሰበሰብ ነው ሲሉ ለቀረበው ሃሳብ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ……





Comments