top of page

ህገ ወጦች ጤነኛ ህፃናት የአካል ጉዳተኛ እያደረጓቸው ለጎዳና ላይ ልመና እንደሚያሰማሯቸው ጥናት አሳየ።

  • 11 minutes ago
  • 1 min read

መጋቢት 2/2018


ህገ ወጦች ጤነኛ ህፃናት እና አቅመ ደካሞችን የአካል ጉዳተኛ እያደረጓቸው ለጎዳና ላይ ልመና እንደሚያሰማሯቸው ጥናት አሳየ።


የተሻለ ህይወት ትኖራላችሁ እየተባሉ ከክፍለ ሃገር ወደ ከተማ የሚመጡ ጤነኛ ህፃናት ጭምር ሰዎችን ለማራራት በሚል ዓይነ ስውር እየተደረጉ ለልመና መሰማራታቸውን ጥናቱ ጠቅሷል።


ጥናቱን ፖፕሌሽን ካውንስል የተባለና ትኩረቱን በጤና ነክ ምርምሮች ላይ ያደረገ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም የተሰራ ሲሆን በጥናቱ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ እና መቀሌ መካተታቸው ተነግሯል።


ህፃናት እና አቅመ ደካሞችን እየመለመሉ ለልመና የሚያሰማሩ ሰዎች የአካል ጉዳት የሌለባቸውን ጭምር የአካል ጉዳተኛ እንደሚያደርጓቸው የነገሩን የፖፑሌሽን ካውንስል የኢትዮጵያ ተወካይ ጌታቸው ተሾመ(ዶ/ር) ናቸው።


ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው ከትውልድ ስፍራቸው የሚመጡ ህፃናት፣ የአካል ጉዳተኞችና አቅመ ደካሞች ከቤተሰቦቻቸው እንዳይገናኙ እንደሚደረጉ፣ በቂ የልመና ገንዘብ ካልሰበሰቡ አካላዊ ቅጣት እንደሚደርስባቸው፣በቂ ምግብ እንደማይሰጣቸውና ስለ ራሳቸውም ሆነ ስለሚያስለምኗቸው ሰዎች ምንም አይነት መረጃ እንዳይሰጡ ማስፈራሪያ እንደሚደርስባቸው ጌታቸው(ዶ/ር) ነግረውናል።


ይህ አይነቱ ወንጀል በድብቅ የሚሰራ በመሆኑ የተጠርጣሪውን ማንነት ለይቶና በቁጥጥር ሥር አውሎ በህግ ፊት ለማቅረብ ብዙ ሥራ የሚፈልግ ነው ያሉን ኃላፊው ከዚህ ጥናት በኋላ ተቋማቸው ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አስፈላጊውን መረጃ ለመስጠት እየሰራን ነው ብለዋል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ……


ንጋት መኮንን

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page