top of page

የመኖሪያ ቤት ችግር በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የብዙዎች ራስ ምታት ሆኖ ቀጥሏል።

  • 1 day ago
  • 2 min read

ሐምሌ 27 2018


የመኖሪያ ቤት ችግር በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የብዙዎች ራስ ምታት ሆኖ ቀጥሏል።


በሪል እስቴት ዘርፍ ከተሰማሩ አልሚዎች መካከል አንዱ የሆነውና የቤት ችግርን ለመፍታት እሰራለሁ የሚለው አባይ ሆምስ ሪል እስቴት፤ ከሰሞኑ በ2 ቢሊዮን ብር የግንባታ ወጪ አዲስ የመኖሪያ ህንፃ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል፡፡


ከቄራ ወደ ጎተራ በሚወስደው መንገድ ፔፕሲ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ (kings residence) ኪንግስ ሬዚደንስ ሲል የሰየመውና 80 የሚሆኑ አፓርትመንት ቤቶች ሚገነቡበት ፕሮጀክት ገዢዎች በተገኙበት ባሳለፍነው ቅዳሜ የመሬት ቁፋሮ ስራውን አስጀምሯል፡፡


የአባይ ሆምስ ሪልእስቴት አማካሪ የሆኑት አቶ ልኡል ደረጀ በሪል እስቴት ዘርፉ ከሚስተዋሉ ችግሮች መካከል የግንባታ ግብአት የዋጋ ግሽበት ዋነኛው ነው፤የግንባታ ወጪ ስለጨመረብኝ ገንዘብ መጨመር አለባችሁ የሚለው ክርክር በዘርፉ የተለመደ ነው ብለውናል፡፡


የግንባታ እቃዎች የዋጋ ግሽበት በየጊዜው እንደሚጨምር ያለፍንበት ልምድ ያሳየናል፤ ስለሆነም ዋጋ ስለጨመረ ጨምሩ ወደሚል ከመሄድ፤ ወይም ውልን ከማቋረጥና፤ ገንዘብን ይዞ ከመጥፋት ከመነሻው የዋጋ ግሽበቱን ታሳቢ ያደረገ ዋጋ ማውጣት ተገቢ መሆኑን የሚናገሩት ባለሙያው አቶ ልኡል ፤እርሳቸው በሚያማክሩትና ወደ ሪልእስቴት ስራ ከገባ ሁለት ዓመቱ በሆነው አባይ ሆምስ ይህንን ችግር ለመፍታት እንዴት እየሰራችሁ ነው ላልናቸው ሲመልሱ፤ደምበኞቻችን ከዋጋ ጭማሪው እንዲያመልጡ ከምንሰጣቸው አማራጮች አንዱ በመደበኛነት ቤቱን ለማግኘት ከተዋዋልንበት የ10 በመቶ ክፍያ በላይ እንዲከፍሉ ማድረግ እንደሆነ ነግረውናል፡፡


ይሁንና በቅርቡ በኢራን ጦርነት ምክንያት የተከሰተው ዓይነት የነዳጅም፤ የግብዓትም እጥረት ሲከሰት ኪሳራውን ለመጋራት በግልጽ መነጋገር ይፈልጋል ይላሉ፡፡


ሌላውና በሪል እስቴት አልሚውና ገዢው መካከል አለመተማመንን የሚፈጥረው ገዢ ቤቱ በትክክል እየተገነባ መሆኑን አይቶ ማረጋገጥ ሲፈልግ፤ በተቃራኒው አልሚው የቤቱን የግንባታ ደረጃ ለማሳየት አለመፈለግ ነው ይላሉ ባለሙያው፤ አባይ ሆምስ ሪል እስቴት ከቄራ ወደ ጎተራ በሚወስደው መንገድ ፔፕሲ አካባቢ ኪንግስ ሬዚደንስ ሲል የሰየመውንና በ2 ቢሊዮን ብር በጀት 80 የሚሆኑ አፓርትመንት ቤቶችን የሚገነባበትን ፕሮጀክቱን የግንባታ ስራ ባስጀመረበት ወቅት እንዲህ ዓይነቱን አለመተማመን ለመቀነስ ነው ገዢዎች ከጅማሮው አንስቶ ሂደቱን እንዲያዩ የጠራናቸው ብለውናል፡፡


ቤት ገንቢውና ቤት ገዢው በሚያስሩት ውል የሚስማሙት ሌላው ጉዳይ የግዢውን ሁኔታ ነው፤ይህንን ያህል ትከፍላለህ፤ ይህንን ይህል ደግሞ ከባንክ ጋር አስተሳስርሃለሁ የሚለው ስምምነት የተለመደ ነው፤

በዚህ በኩል ድርጅታችሁ ምን ልምድ አለው፤ ያልናቸው አማካሪው ገና ግንባታ መጀመራችን ስለሆነ ከባንክ ጋር አላስተሳሰርንም፤ የቤቱን 10 በመቶ የከፈለ ደምበኛ ይገነባለታል፤ መተማመኛችን የገባነው ውል ነው፤ ባልነው ጊዜ ካላስረከብናቸው ቅጣቱን በውሉ ላይ አስፍረናል ብለዋል አቶ ልዑል፡፡


ወደ ሪል እስቴት ዘርፍ ከገባ 2 ዓመት ሽያጭ ከጀመረ ደግሞ 7 ወራት ገደማ የሆነው አባይ ሆምስ ሪል እስቴት ከሰሞኑ ካስጀመረው ኪንግስ ሬዚደንስ ፕሮጀክት በተጨማሪ ሜክሲኮ ጠማማ ፎቅ አካባቢ ያለው ዳውን ታውን ፕሮጀክቱ 228 አፓርትመንትና 220 ሱቆች ያሉት ሲሆን ከ60 በመቶ በላዩን በሽያጭ ማስተላለፉን ከአማካሪው ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ...




ምንታምር ጸጋው

Recent Posts

See All
በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅነትና በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ከ40 አመታት በላይ በሀላፊነት ሲሰሩ የነበሩት ወይዘሮ መዓዛ ቅጣው አረፉ፡፡

ሐምሌ 28 2018 በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅነትና በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ከ40 አመታት በላይ በሀላፊነት ሲሰሩ የነበሩት ወይዘሮ መዓዛ ቅጣው አረፉ፡፡ ሙሉውን ለማድመጥ.... እሸቴ አሰፋ

 
 
 
በኢትዮጵያ ተላላፊ ባለሆኑ እንደ ልብ ያሉ ሕመሞች ምክንያት የሚመጣ የጤና ችግር ለሀገሪቱ የጤና ሥርዓት ተጨማሪ ሥጋት ሆኗል ተባለ።

ሐምሌ 28 2018 በኢትዮጵያ ተላላፊ ባለሆኑ እንደ ልብ ያሉ ሕመሞች ምክንያት የሚመጣ የጤና ችግር ለሀገሪቱ የጤና ሥርዓት ተጨማሪ ሥጋት ሆኗል ተባለ። ከልብ ሕመም ጋር በተያያዘ የሚደርስ የጤና ቀውስን ለመቀነስ ሕክምናው እንዲሁም ቅድመ - መከላከሉ ላይ በስፋት መሠራት አለበት ተብሏል። ከልብ ሕክምና ተደራሽነት፣ የ

 
 
 
ባለፉት 10 ዓመታት ኤል ኒኖ በኢትዮጵያ ሁለት ጊዜ ተከሰቷል።

ሐምሌ 28 2018 ባለፉት 10 ዓመታት ኤል ኒኖ በኢትዮጵያ ሁለት ጊዜ ተከሰቷል። በ2007/08 እና ከሦስት ዓመታት በፊት በተወሰኑ ቦታዎች ላይ አጋጥሟል። በእነዚህ ጊዜያት እንስሳት ሞተዋል፤ የግብርና ምርት መጠን አሽቆልቁሏል፤ ገበሬውም ለገበያ እና ለቤቱ የሚያቀርበውን ምርት ለማግኘት መቸገሩን የግብርና ምርምር ኢ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page