በኤሌክትሪክ እጦት ምክንያት የእለት ተእለት ተግባራቸውን መከወን ዳገት እንደሆነባቸው የምዕራብ ጎጃም ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
- 1 day ago
- 1 min read
ሐምሌ 27 2018
በኤሌክትሪክ እጦት ምክንያት የእለት ተእለት ተግባራቸውን መከወን ዳገት እንደሆነባቸው የምዕራብ ጎጃም ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትክ አገልግሎት በበኩሉ ማህበረሰቡ የሚያነሳው ችግር ተገቢ ነው እሱን ለማስተካከልም እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡
ከ1.3 ሚሊየን በላይ ህዝብ ያለበት የምዕራብ ጎጃም ዞን ኤሌክትሪክ እያገኘን ያለነው በሳምንት አንዴ ነው፤ 6ቱን ቀናት ደግሞ በጨለማ ማሳለፍ ከጀመርን ከራርመናል ሲሉ ቅሬታቸውን ነግረውናል፡፡
ለረጅም ጊዜ ስንፈተንበት ለቆየነው ችግርም መፍትሄ ለማግኘት የአማራ ሪጅን ማስተባበሪያ ቢሮን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአካል በመቅረብ ጥያቄያችንን አቅርበናል ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ የፍኖተ ሰላም ሰብስቴሽን ሥራውን በአግባቡ ለማከናወን በአስቸኳይ አዲስ ትራንስፎርመር የሚያፈልግ በመሆኑ ይህ እንዲስተካከል የሚለው ቅሬታ ከጥያቄዎቻችን መካከል ናቸው ብለውናል፡፡
የምዕራብ ጎጃም ዞን ነዋሪ በኤሌክትሪክ እጦት ምክንያት አሁን ላይ እየገጠመው ስላለው ችግር የጠየቅነው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚነሳው ቅሬታ ትክክል መሆኑን ያምናል፡፡
ችግሩ በሁለቱም የሀይል አቅራቢ ተቋማት የሚታወቅ መሆኑን የተናገረው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአማራ ሪጅን ማስተባበሪያ ቢሮ የሚነሳውን ቅሬታ ለመፍታት የአጭር ጊዜ የረጅም ጊዜ እቅድ ወጥቶ እየተሰራ ነው ብሏል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ...
ፋሲካ ሙሉወርቅ
_edited.jpg)

Comments