ታሪክን_የኋሊት
- 1 day ago
- 1 min read
ባለ ብዙ ገድሉ አፍሪካ አሜሪካዊ ስፖርተኛ ጄሲ ኦውንስ በዘመኑ ድንቅነቱን አስመስክሯል፡፡
በተለይም ከ90 አመታት በፊት በጀርመን በተካሄደው የበርሊን ኦሎምፒክ ታላቁን ታሪክ የሰራበት ነበር፡፡
በዚያ ኦሎምፒክ ኦውንስ በተለያዩ ስፖርታዊ ክንውኖች አራት የወርቅ ሜሊያዎችን አጥልቋል፡፡
በዚህ ኦሎምፒክ በመቶ ሜትር ሩጫ የመጀመሪያዋን የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘው ከ90 አመታት በፊት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡
ሁለገቡ ኦውንስ በበርሊን ኦሎምፒክ ከመቶ ሜትር ሩጫ በተጨማሪ በአግድመት ዝላይ ፣ በ200 ሜትር እንዲሁም 4 በ 4 መቶ ሜትር የዱላ ቅብብል 3 የወርቅ ሜዳሊያዎችም አሸንፏል፡፡
ጄ ሲ ኦውንስ ከ90 አመታት በፊት በበርሊን ኦሎምፒክ ከየትኞቹም ተፎካካሪ ስፖርተኞች በበለጠ በድል ያሸበረቀ ሆኖ አጠናቋል፡፡
ዘመኑ ናዚ ጀርመን አለምን በጦር አስገበራለሁ በሚል እብሪት ጡንቻዋን የምታፍታታባት ነበር፡፡
በዘረኛ አስተሳሰብ የሰከሩት መሪያቸው አዶልፍ ሒትለር እና ተከታዮቹ የነጭ ዘር ከነጮችም የአርያን ዝርያዎች የምርጦች ሁሉ ምርጥ ናቸው የሚል የታላቅነት ሰበካ የተያያዙበት ነበር ጊዜው፡፡
አፍሪካ አሜሪካዊው ኦውንስ በበርሊን ኦሎምፒክ ከየትኞቹም ተፎካካሪ ስፖርተኞች በላቀ የ4 የወርቅ ሜዳሊያዎች ባለቤት መሆኑ የናዚዎቹን የታላቅነት ሰበካ እርቃኑን ያስቀረ እንደሆነ አስመስክሯል፡፡
አሶሼትድ ፕሬስ ባሰባሰበው የህዝብ አስተያየት መለኪያ ኦውንስን የ20ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ ታላቅ ስፖርተኛ እንዳለው በግለ ታሪኩ ሰፍሮ ይገኛል፡፡
የኔነህ ከበደ
_edited.jpg)

Comments