top of page


ጥቅምት 14 2018 - የባዮቴክኖሎጂ ውጤት የሆነው የዘረመል ምህድስና GMO
ኢትዮጵያ ግብርናን ቀድመው ከጀመሩ የዓለም ሀገራት ስሟ ቀድሞ ይነሳል፡፡ ዛሬም ግን ሀገሪቱ የትናንት የሚባል ታሪክ ካላቸው ሀገራት ተርታ እንኳን በምግብ እራሷን ችላ መሰለፍ ተስኗታል፡፡ በ21ኛው ከፍለ ዘመንም የርሃብ፣ የምግብ እጦት፣ ዜና ከምድሯ አልጠፋም፡፡ ከ1,600 በላይ ዝርያዎችን ባለፉት 70 ዓመታት ለአርሶ አደሮች ማከፋፈሉን የሚናገሩት የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ንጉሴ ደቻሳ (ፕ/ር)፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር በጣም እየጨመረ መሆኑን አስረድተው፤ የሰብል ምርቶች ምርታማነትም በእጥፍ መጨመሩን አብራርተዋል፡፡ ለምሳሌ በአርሶ አደር ማሳ ላይ ጤፍ በሄክታር ከ10 ኩንታል ወደ 20፣ ስንዴ ከ20 ወደ 36፣ ቦሎቄ ከ14 ወደ 28 ከፍ ማለቱን አስረድተዋል፡፡ ንጉሴ ደቻሳ(ፕ/ር) ይህም ሆኖ የምርት እድገቱ ከኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት መ
7 days ago3 min read


ጥቅምት 14 2018 - ሕብረት ባንክ ከሚሰጠው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሰበሰበውን 35 ሚሊየን ብር ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች አበረከተ
35 ሚሊዮን ብሩ የተሰጠው ለ10 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ነው፡፡ ድጋፍ የተርገላቸው አስሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የተመረጡት በሸሪዓው መርህ መሰረት የሚሰሩ መሆናቸው ተመዝኖ፣ ከሚደርሱት የሕብረተሰብ ቁጥር እና የሚሰጠውን ድጋፍ ለምን ተግባር እንደሚያውሉትም ጭምር ታይቶ ነው ተብሏል። ድጋፉ ከተደረገላቸው ድርጅቶች መካከል፤ እማሙ ማሊክ ትምህርት ቤት፣ ወንድም ካሊድ ፋውንዴሽ፣ ባቡል ካኸር፣ ሜቄዶኒያ፣ ቢላሉ ሀበሺ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሙስሊም የጤና ባለሞያዎች ማህበር ይገኙበታል። ሕብረት ባንክ የሸሪዓውን መርህ በተከተለ መልኩ ከወለድ ነፃ የባንክ እገልግሎት መስጠት ከጀመረ 10 ዓመታት እንዳለፈው አስታውሷል። በአሁኑ ሰዓትም ሕብረት ባንክ 23 ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ብቻ የሚሰጡ ቅርንጫፎች ከፍቼ እየሰራሁ ነው ሲል ጠቅሷል። ባንኩ ሸሪዓው
7 days ago1 min read


ጥቅምት 13 2018 - የቴክኒክ ሞያ ዘርፎች ከታችኛው የትምህርት ደረጃ ጀምሮ ትኩረት እያገኘ አይደለም ተባለ፡፡
ለሀገር እድገት መሰረት የሆኑ የቴክኒክ ሞያ ዘርፎች ከታችኛው የትምህርት ደረጃ ጀምሮ ትኩረት እያገኘ አይደለም ፤ ይህም መስተካከል አለበት ተባለ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤና ትምህርት ማዕከል መምህር አቶ ፍስሃ ተክሉ በልጅነት የሚሰራው ስራ ነገ በቴክኒክና ሞያ ትምህርት ቤት ውስጥ እጁ ከታች ጀምሮ የተፍታታ ተማሪ እንድናገኝ ይረዳል ብለዋል፡፡ እነዚህ ተማሪዎች ከሰዎች ጋር አብሮ የመስራትና የፈጠራ አቅማቸውም እጅግ የላቀ እንዲሆን ያደርጋልም ሲሉም ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶክተር ታምሬ አንዷለም በበኩላቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ለቴክኒክና ሞያ ትምህርት የሚሰጠው ትኩረት እጅግ አነስተኛ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ የትኩረት ማነሱ ችግር ዛሬ የመጣ ሳይሆን ቀደም ካለው ጊዜ ጀምሮ የነበረ ነው ያሉ ሲሆን ለሞያ
Oct 231 min read


ጥቅምት 13 2018 - የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማህበር የኢትዮጵያ ብድር እዳ ጫና ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርቱ 39 በመቶ ደረጃ እንዳለው ተናገረ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማህበር የኢትዮጵያ ብድር እዳ ጫና ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርቱ 39 በመቶ ደረጃ እንዳለው ተናገረ፡፡ የእርዳታና ድጋፍ መቀነስም ከቀጠሉ ግጭቶችና መሰል ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ጋር ተዳምሮ ችግሩን እንዲያከፋው ቅድሚያ የሚያስፈልገውን እየለዩ መፍትሄ ማበጀት ያስችላል ብሏል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ …. ተህቦ ንጉሴ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s 🐦X :...
Oct 231 min read


ኢትዮጵያ ብድሯን በቻይና የመገበያያ ገንዘብ ለመክፈል ጥያቄ ማቅረቧ፣ ምን ያስገኝላታል?
ኢትዮጵያ ዋና አበዳሪዋ ከሆነችው ቻይና ለወሰደችው ብድር 5.3 ቢሊዮን ዶላሩን በዩዋን ለመክፈል ጥያቄ አቅርባለች፡፡ ጥያቄው አዎታዊ ምላሽ ካገኘ የብር የመግዛት አቅም ይበልጥ እንዳይዳከም ያግዛል ተብሏል፡፡ እንዴት ? በአለም ዓቀፉ ደረጃ “ብድሯን ለመክፈል የምትቸገር ሀገር” በሚል የገባችበትን ምድብ በመቀየርስ ስሟን ያድስላት ይሆን? የዘርፉን ባለሞያ አነጋግረናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. ትዕግስት ዘሪሁን የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬Wh
Oct 231 min read


ጥቅምት 13 2018 - በ3 ወራቱ ከውሃ ከመነጨው የኤሌክትሪክ ሃይል ግማሽ የሚሆነው ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተገኘ እንደሆነ ተነገረ።
ባለፉት 3 ወራት ለኬንያ እና ጅቡቲ በሽያጭ ከቀረበ የኤሌክትሪክ ሃይል፤ ከ34 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ መገኘቱ ተነገረ። በሱዳን ያለው ግጭት በመሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት በማስከተሉ በጊዜ ማዕቀፉ የኤሌክትሪክ ሃይል ለሀገሪቱ በሽያጭ አልቀረበም ተብሏል። በሌላ በኩል በሶስት ወራቱ ከውሃ ከመነጨው የኤሌክትሪክ ሃይል ግማሽ የሚሆነው ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተገኘ እንደሆነ ሠምተናል። ከሃምሌ 1 ቀን 2017 እስከ መስከረም 30/2018 ባሉት ሶስት ወራት ኢትዮጵያ 9,208 ጊጋ ዋት ሰአት የኤሌክትሪክ ሃይል አመነጭታለች ተብሏል። ከዚህ የኤሌክትሪክ ሃይል 98 በመቶ ወይም 9,027 ጊጋ ዋት ሰአቱ ከውሃ የሃይል ማመንጫ ገድቦች የተገኘ እንደሆነ ፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ነግረውናል፡፡
Oct 231 min read


ጥቅምት 12 2018 ለሰላም፣ ለእድገት ሲባል መንግስት፣ የተፎካካሪ ፓርቲ ፖለቲከኞች እና ነፍጥ ያነሱ ታጣቂዎች ወደ መግባባት እንዲመጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ፓርትርያርኩ ይህንን የሰላም ጥሪ ያቀረቡት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በተጀመረበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ነው፡፡ በሀገሪቱ ያለው አለመረጋጋት በህዝብ አጠቃላይ ስነ ልቦና፣ በሀገሪቱ አንድነትና እድገት ላይ የሚያስከትለው ጫና በቀላሉ የሚታይ አይደለም ያሉት አባ ማቲያስ ፣ የህዝቡ ስነ ልቦና ከተጎዳ የነገው እድል ጤናማ ይሆናል ተብሎ አይታሰብም ብለዋል፡፡ ችግሩ እየታየ ያለው በዋናነት በሀገራችን ፖለቲከኞች በመሆኑ ነገሩ የተወሳሰበና የተራዘመ እንዲሆን አድርጎታል ሲልም አክለዋል፡፡ በመሆኑም ይህ የርስ በርስ ግጭት ቆሞ ችግሮች በውይይትና በድርድር በመፍታት የወንድማማች እልቂት የሚያስቆም የሰላምና የዕርቅ ዕድል ቅድሚያ እንዲሰጠው ጉባኤው የበኩሉን ጥረት ማድረግ ይገባዋል ሲል አባ ማቲያስ ጠይቀዋል፡፡ የነገው ትውልድ ልማታዊ ተስፋ እውን ሊሆን የሚ
Oct 221 min read


ጥቅምት 12 2018 - አሲዳማ መሬትን ለማከም የሚረዳ የኖራ ወፍጮ በተለያዩ ክልሎች ሊያቋቁም መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ተናገረ
በአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ እርዳታ አሲዳማ መሬትን ለማከም የሚረዳ የኖራ ወፍጮ በተለያዩ ክልሎች ሊያቋቁም መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ተናገረ፡፡ ለዚህ ተግባር የሚውል የ20 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ከአለም ባንክ መገኘቱም ተሰምቷል፡፡ ኢትዮጵያ ከምታርሰው መሬት ውስጥ 43 ከመቶ ወይም 7 ሚሊዮን ሄክታር የሚሆነው መሬቷ በአሲድ እንደተጠቃ የግብርና ሚኒስቴር ከአንድ ዓመት በፊት መናገሩ ይታወሳል፡፡ 3.1 ሚሊዮን ሄክታር የሚሆነው ደግሞ በጠንካራ አሲድ የተጠቃ አፈር ነው ተብሏል፡፡ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እያሱ ኤሊያስ (ፕ/ር) በአሲድ የተጠቃው መሬት ምርትን ከ70 እስከ 100 በመቶ ምርት እንደሚቀንስ ተናግረው ይህም የሀገሪቱን የግብርና ስራ ፈታኝ አድርጎታል ሲሉ አስረድተዋል፡፡ በኢሲድ የተጠቃው መሬት ከፍተኛ ዝናብ እና እርጥበት ያለበት አ
Oct 221 min read


ጥቅምት 12 2018 - "በአደጋው የሞቱና አድራሻቸው ያልታወቀ ሰዎች ስርዓተ ቀብር፣ በከተማ አስተዳደሩ ተፈፅሟል" የድሬዳዋ ደወሌ ምድር ባቡር ድርጅት
"በአደጋው የሞቱና አድራሻቸው ያልታወቀ ሰዎች ስርዓተ ቀብር፣ በከተማ አስተዳደሩ ተፈፅሟል" የድሬዳዋ ደወሌ ምድር ባቡር ድርጅት ሥራ አስኪያጅ። የባቡር ሾፌሩን ጨምር ለ15 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው የድሬዳዋ ደወሌ የባቡር አደጋ እንዴት ሊከሰት ቻለ? ከባቡሩ እድሜ ጋር ተገናኝቶ እየተነሳ ያለው ጥያቄስ ለአደጋው መከሰት ምክንያት ነው ወይ? የድሬዳዋ ደወሌ ምድር ባቡር ድርጅት ስራ አስኪያጅ እና ምክትል ስራ አስኪያጅን ጠይቀናል። ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ቴዎድሮስ ወርቁ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://ti
Oct 221 min read


ጥቅምት 12 2018 -ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚያገኘው ኢትዮጵያዊ ከ40 በመቶ በማይበልጥባት አትዮጰያ የውሃ ሀብት አያያዟን ዲጂታል በማድረግ በኩል ምን እየሰራች ነው?
አፍሪካ ውሃ ሀብቷን የምትረዳበት እና የምታስተዳድርበትን መንገድ ለመቀየር የሚያስችሉ የዲጂታል ፈጠራዎች፣ ቴክኖሎጂ እና መረጃ ላይ የሚመክር ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ ከትናንት ጀምሮ እየተካሄደ ነው፡፡ በመድረኩ የመንግስት ተወካዮች፣ ሳይንቲስቶች እና የፈጠራ ባለሞያዎች ተገኝተዋል፡፡ ሲምፖዚየሙን ያዘጋጀው ዓለም አቀፉ የውሃ አስተዳደር፣ ከዲጂታል አፍሪካ እና ከሄልምስሌይ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተበባር መሆኑን ሰምተናል፡፡ ዘመናዊ የውሃ አስተደደር ላይ መምከር ከውሃ ጋር በተያያዘ ያለውን የመረጃ ክፍት ለመሙላት፣ በዚህም የምግብ ስርዓትን የተመለከቱ ውሳኔዎችና ኢንቨስትመንቶችን ለመደገፍ በማሰብ ነው ተብሏል፡፡ የ3 ቀናት ስብሰባው የሳተላይት መረጃ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ዲጂታል መድረኮች ከውሃ ጋር በተያያዘ ሀገሮች ዕቅድ እንዲያሻሽሉ፣ የው
Oct 221 min read


ጥቅምት 11 2018 - ባህርዳር እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በኒኩለር ሳይንስ የሁለተኛ ዲግሪ ት/ት መስጠት መጀመራቸውን ተናገሩ
በኒኩለር ሳይንስ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት መስጠት መጀመራቸውን ሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ተናገሩ፡፡ ትምህርቱን እየሰጡ ያሉት ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ናቸው፡፡ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በተያዘው ዓመት ለመጀመርያ ጊዜ በ2ተኛ ዲግሪ ሲያስተምራቸው የነበሩ ተማሪዎች እንደሚያስመርቅ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ(ዶ/ር) ነግረውናል፡፡ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደረጀ እንግዳ(ዶ/ር) በበኩላቸው ከሁለተኛ ዲግሪ ባለፈ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ለመስጠት ዝግጅት እያጠናቀቁ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ በቅርቡ መንግስትበ ኢትዮጵያ የኒኩለር ፕላንት ለሰላማዊ መንገድ እንደሚገነባ የተናገረ ሲሆን ሁለቱ ተቋማት ለዚህ የሚሆን ባለሞያ ለማፍራት ማቀዳቸውንም ጠቅሰዋል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. በረከት
Oct 211 min read


ጥቅምት 11 2018 የኢትዮዽያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት በማድረግ አለም አቀፍ ኩባንያ ለመሆን ጉዞ ጀምሬያለሁ አለ።
ኮርፖሬሽኑ በበፊቱ አዋጅ መሰረት ሶስት የተሰጡትን ግዙፍ የኢንቨስትመንት ክንውኖችን ለመፈፀም ወደ ስራ መግባቱን ተናግሯል። ኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እፈፅማቸዋለው ካላቸው ግዙፍ ስራዎች፤ አንደኛው የምድር ባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ፤ ሁለተኛ የተገነባውን የባቡር ልማት ማከናወን እና ሶስተኛው የመሰረተ ልማት አካል አስተዳደርና ተዛማጅ ስራዎች ናቸው። ኮርፖሬሽኑ ከዚህ በተጨማሪም በአዋጅ በተሰጠው በደረጃ አንድ ኮንትራክተር ፤ በደረጃ አንድ መልቲሞዳል አገልግሎት እንዲሁም በደረጃ አንድ የባቡር አካላት ማምረቻ እና ሌሎች ፈቃዶች ወደ ስራ ለመግባት ማሰቡን ሲናገር ሰምተናል። የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሸን ዛሬም የመንግስትና የግል ሽርክና በማስማማት ፋይናንስ ለማሰብሰብ ሲመክር ውሏል። ኮርፖሬሽኑ እነዚህን ግዙፍ ፕሮጀክቶች ለማልማት በሽርክና ማህ
Oct 212 min read


ጥቅምት 11 2018 - በኢትዮጵያ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮችን እና አርብቶ አደሮችን በተለያየ መልኩ እየረዳ መሆኑን የአለም ምግብ ድርጅት ተናገረ።
የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተወካይ ሙቲንታ አምባይ(ዶ/ር) ይህንን ያሉት ዛሬ በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በተከበረው የአለም የምግብ ቀን ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡ ምርጥ ዘር እና ግብዓት በማቅረብ፣ የማጨጃ እና መውቂያ መሳሪያዎችን በመለገስ፣ በገንዘብ ድጋፍ፣ የገበያ ትስስር በመፍጠር እና በሰብል እና እንስሳት ኢንሹራንስ በሀገሪቱ ከ1.5 ሚሊየን በላይ አርሶ፣ አርብቶ እና ከፊል አርሶ አደሮችን እየደገፈ ነው ሲሉ አስረድተዋል። ካለፈው ጥር ጀምሮ ወደ 47,000 አርሶ አደሮች 35,000 ሄክታር በ5 ክልሎች እየለማ መሆኑን የተናገሩት የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተወካይ ከዚህ ውስጥ ከ10,000 በላይ የሚሆነው በመስኖ እየለማ ነው ብለዋል። ምርታማነትን ማሳደግ፣ ገቢን በመጨመር ማህበረሰቡን ከጥገኝነት የማውጣት ስራ ከመንግስት እና ከሌሎች መንግስታዊ ካልሆኑ
Oct 211 min read


ጥቅምት 11 2018 - ክፍት የተተዉ ጉድጓዶች
በአዲስ አበባ በየጎዳናው ክዳናቸው ተሰርቆ ወይም ተሰብሮ ክፍት የተተዉ ጉድጓዶች ለተለያየ አደጋ ምክንያት መሆናቸውን ቀጥለዋል፡፡ በየዓመቱ 6,000 ክዳኖች እየተዘጋጁ ለአደጋ የሚያጋልጡ ጉድጓዶች እየተከደኑ ቢሆንም አሁንም ስርቆቱ የቀጠለ በመሆኑ ችግሩን መቅረፍ አዳጋች ሆኗል ተብሏል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. ገዛ ጌታሁን የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s 🐦X : https://x.com/sheg
Oct 211 min read


ጥቅምት 11 2018 - የማሻሻያ እርምጃ ተከትሎ የኢትዮጵያ ጥቅል ሀገራዊ ምርት በ90 ቢሊዮን ዶላር ቀንሷል
ከዓመት በፊት የተወሰደውን የውጪ ምንዛሪ አስተዳደር የማሻሻያ እርምጃ ተከትሎ የኢትዮጵያ ጥቅል ሀገራዊ ምርት (GDP) በ90 ቢሊዮን ዶላር ቀንሷል፡፡ እንዲያም ሆኖ የተሻለ የ GDP እድገት ካላቸው ሀገራት መካከል ነች የተባለችው ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት አንዱ ትኩረቴም ጥቅል ሀገራዊ ምርቱን ይበልጥ ማሳደግ ላይ ይሆናል ብላለች፡፡ ለመሆኑ የትኞቹ ዘርፎች ላይ ትኩረት ብታደርግ ይሻላታል? የምጣኔ ሐብት ባለሞያን ጠይቀናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ ንጋቱ ረጋሣ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com
Oct 211 min read


ጥቅምት 10 2018 - ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብት እና ዓለም አቀፍ ህጎች (ክፍል 1)
#ጉዳያችን - ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብት እና ዓለም አቀፍ ህጎች ኢትዮጵያ ካሏት ተፋሰሶች 90 በመቶ የሚሆነው ድንበር ተሻጋሪ ነው። ለመሆኑ ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብት መካከል አለመግባባት ሲፈጠር በዓለም አቀፍ ህግ እንዴት ይዳኛል? በጉዳዩ ላይ፣ የአለም አቀፍ የውሃ ህግ ባለሞያ የሆኑት ከበደ ገርባ(ዶ/ር) የሰጡንን ማብራሪያ ያድምጡ…. ቴዎድሮስ ወርቁ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s 🐦X : https:
Oct 211 min read


ጥቅምት 11 2018 - ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብት እና ዓለም አቀፍ ህጎች (ክፍል 2)
#ጉዳያችን - ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብት እና ዓለም አቀፍ ህጎች (ክፍል 2) ኢትዮጵያ ካሏት ተፋሰሶች 90 በመቶ የሚሆነው ድንበር ተሻጋሪ ነው። ለመሆኑ ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብት መካከል አለመግባባት ሲፈጠር በዓለም አቀፍ ህግ እንዴት ይዳኛል? በጉዳዩ ላይ፣ የአለም አቀፍ የውሃ ህግ ባለሞያ የሆኑት ከበደ ገርባ(ዶ/ር) የሰጡንን ማብራሪያ ያድምጡ…. ቴዎድሮስ ወርቁ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/y
Oct 211 min read


ጥቅምት 11 2018 - በዓለም ዙሪያ በየቀኑ ከ100,000 በላይ የአየር በረራ እንደሚደረግ ይነገራል።
በኢትዮጵያም በቀን የሚነሳና የሚያርፈው እንዲሁም በኢትዮጵያ የአየር ክልል የሚተላለፈው በረራ ከ600 በላይ ደርሷል። ከዚህ ሁሉ የአየር በረራ ጀርባ ሆነው፣ የበረራውን ደህንነት፣ አዋጭነትና ቅልጥፍና የሚቆጣጠሩት #የአየር_ትራፊክ_ተቆጣጣሪዎች ናቸው። ያለነሱ ከአደጋ ነፃ የሆነ እና የሰመረ የአየር በረራን ማሰብ ከባድ እንደሚሆን ይነገራል። በዚህም ምክንያት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ሚናን፣የአቪኤሽን ዘርፍ የልብ ምት ነው እንዲባል ያደርገዋል። በሌላ በኩል ስራው ባለው ውጥረትና ጭንቀት ምክንያት በዓለም ዙሪያ ከባድ ከሆኑ የሙያ አይነቶች አንዱ ያደርገዋል። ጥቅምት 10 በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ስራ የሚታሰብበት፣ተገቢው ክብር የሚሰጥበት ዕለት ነው። የኢትዮጵያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ማህበርም ቀኑን አስቦት ውሏል። በዓለም ዙ
Oct 211 min read


ጥቅምት 10 2018 - የሀገር ቤት መድሃኒት አቅራቢዎች
በኢትዮጵያ ለጤና ተቋማት ተገዝቶ ከሚከፋፈለው መድሃኒት የሀገር ቤት አቅራቢዎች መጠን እጅግ ቀንሶ እንደነበር ይነገራል፡፡ በቅርቡ በተደረጉ አንዳንድ ማሻሻያዎች ይህንን በመጠኑ ቢስተካከልም አምራቾቹ አሁንም አብዛኛውን ግብዓታቸው ከውጪ ሸማች መሆናቸው የሚጣለውም ቀረጥ ከፍተኛ መሆኑ ከዚህ በላይ እንዳይሰሩ እያደረገ ነው ተባለ፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. ምህረት ስዩም የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s 🐦X
Oct 201 min read


ጥቅምት 10 2018 - ህገወጥ አዘዋዋሪዎቹን ለመቆጣጠርና ገንዘቡን ለመያዝ ምን እየተሰራ ነው?
የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና በሰዎች የመነገድ ወንጀል አሁንም ቀጥሏል፡፡ በዚያ ተግባር የሚገለበጠው ገንዘቡም ከፍተኛ ነው፡፡ ህገወጥ አዘዋዋሪዎቹን ለመቆጣጠርና ገንዘቡን ለመያዝ ምን እየተሰራ ነው? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. የኔነህ ሲሳይ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s 🐦X : https://x.com/shegerfm?s=2
Oct 201 min read


ጥቅምት 10 2018 - የመንቀሳቀስ መብት አሳሳቢ ሆኖ የቀጠለው ማን ምን ባለመስራቱ ነው?
በየአካባቢው ተንቀሳቅሶ ለመስራት አሁንም ፈተና ሆኖ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት አስረድቷል፡፡ ይህ የመንቀሳቀስ መብት አሳሳቢ ሆኖ የቀጠለው ምን ባለመደረጉ፣ ማን ምን ባለመስራቱ ነው? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. ማርታ በቀለ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s 🐦X : https://x.com/shegerfm?s=2
Oct 201 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page








