top of page

አዋሽ ባንክ ለ7 ግብረ ሰናይ ድርጅቶች 25 ሚሊዮን ብር ሰጠ።

  • 1 hour ago
  • 1 min read

የካቲት 26/2018

አዋሽ ባንክ ለ7 ግብረ ሰናይ ድርጅቶች 25 ሚሊዮን ብር ሰጠ።


ባንኩ ለግብረ ሰናይ ድርጅቶቹ ድጋፉን ያደረገው ያለንበትን የረመዳን ወርን ምክንት በማድረግ ነው።


25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የተደረገላቸው ድርጅቶችም ህጻናትን፣ በአረጋዊያንን እና አካል ጉዳተኞችን በመደገፍና በመንከባከብ ላይ የተሰማሩ መሆናቸው ተጠቅሷል።


ወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን፣ የስራ ለና የበጎ አድርጎ ድርጅት፣ ተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድሁድ ሰፖርት ኦረጋናይዜሽን፣ ዘ ችልድረንስ ኸርት ፈንድ ኦፍ ኢትዮጵ፣ እዝነት አካል ጉዳተኛ ህፃናትና ወላጆች መርጃ ድርጅት እና አብደላ ኢብኑ ኡሚ መክቱም ቁራን ማህበር ናቸው ድጋፉ የተደረገላቸው።



አዋሽ ባንክ የ1447ኛውን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ ትናንት ምሽት በሸራተን አዲስ ሆቴል ባዘጋጀው የኢፍጣር መርሃ-ግብር ላይ ነው ድጋፉን የሰጠው።


ባንኩ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ በ52 ከተሞች ለ2600 አባወራዎች፣ አረጋዊያን እና በአነስተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ሰዎች የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ተናግሯል።


በተጨማሪም በአዲስ አበባ እና በ14 ተለያዩ የክልል ከተሞች ከደንበኞቹ ጋር የኢፍጣር መርሃ-ግብር ማካሄዱን ተናግሯል።


ባንክ ባሉት ከ1,005 በላይ ቅርንጫፎቹ አማካይነት ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞችን ማፍራቱን ጠቁመዋል።


በወለድ ነፃ የፋይናንስ ዘርፍ ብቻ ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ የሃላል ፋይናንስ አገልግሎት ማቅረቡም ተነግሯል።


የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው ባንኩ ላለፉት 31 ዓመታት በተለይም በማዕድ ማጋራት፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በስራ ፈጠራ እንዲሁም ለአቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ ከፍተኛ በጀት በመመደብ በርካታ ስራዎችን ማከናወኑን ተናግረዋል።


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page