top of page

በበጀት ዓመቱ በመንፈቅ ዓመት በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ 8,183 ሊትር ነዳጅ መወረሱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ተናገረ፡፡

  • 2 hours ago
  • 1 min read

የካቲት 25/2018


በበጀት ዓመቱ በመንፈቅ ዓመት በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ 8,183 ሊትር ነዳጅ መወረሱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ተናገረ፡፡


ህገወጥ የነዳጅ ዝውውሩ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ሲፈፀም የተገኘ ነው፡፡


ቢሮው በውሃ ኮዳ እና በሌሎች ያልተፈቀዱ እቃዎች ሲጓጓዙ ተገኝተዋል ካለው 8,183 ሊትር ነዳጅ ውስጥ ናፍጣ 5,900 ሊትር ከ2,000 ሊትር በላይ ቤንዚን እና ነጭ ጋዝን እንደሆነ ተሰምቷል፡፡



በከተማዋ ባሉት ሁሉም ማዲያዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ነው ያለው ቢሮው በህገ-ወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩትን ፣ ነዳጅ እያላቸው የለንም የሚሉትን እርምጃ እየወሰድንባቸው ነው ብሏል ቢሮው፡፡


በዚህም ባለፉት 6 ወራት ነዳጅ እያላቸው ጨርሰናል በማለት አገልግሎት ያቆሙ ሶስት ማደያዎችን ክስ ተመስርቶባቸው እንዲታሸጉ ተደርጎ እንደገና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ተደርጓል ተብሏል፡፡


የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ነዳጅ እያላቸው የለንም፣ ጨርሰናል ጀነሬተር የለንም ፣ መቅጃ ተበላሸብኝ በሚል አገልግሎት ማቆም አይቻልም ፣ በከተማዋ ባሉ ሁሉም ማዲያዎች ላይም ቁጥጥር አደርጋለሁ ብሏል፡፡


ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page