top of page

አሁን ላይ ሁሉም ክልሎች ከፌዴራሉ ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ አዘጋጅተው ጨርሰዋል ተባለ

  • 57 minutes ago
  • 2 min read

የካቲት 25/2018

 

አሁን ላይ ሁሉም ክልሎች ከፌዴራሉ ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ አዘጋጅተው ጨርሰዋል ተባለ።

 

በተለያየ ምክንያት አዋጁን የማዘጋጀቱ ስራ በክልሎች ተጓቶ እንደቆየ የፌዴራል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ተናግሯል።

 

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ በፌዴራል ደረጃ መሻሻሉን ተከትሎ ክልሎችም ተመሳሳይ ማዕቀፍ ያለው  ህግ ማዘጋጀት እንዳለባቸው ተጠቅሶ በዚሁ ላይ ሲሰራ መቆየቱ ተነግሯል።

 

ክልሎች ተመሳሳይ ይዘት ያለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ማውጣት አለባቸው የተባለው የፌዴራሉ አዋጅ ተፈጻሚነት በፌዴራል በሚመዘገቡት ላይ ብቻ ስለሆነ ነው ተብሏል።

 

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል  ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንዳሉት የውጪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ወይም ፤ ከሁለት ክልል በላይ በሆኑ አካባቢዎች የሚሰሩ ሀገር በቀል ድርጅቶች የሚመዘገቡት በፌዴራል ደረጃ ሲሆን የሚተዳደሩትም በፌዴራሉ አዋጅ ነው።

 

የሃይማኖት ተቋማት የመሰረቷቸው የልማት የበጎ ድርጅቶችም በፌዴራል ደረጃ እንደሚመዘገቡ እና በፌዴራሉ አዋጅ እንደሚተዳደሩ ጠቅሰዋል።

 

በአንድ ክልል ብቻ የሚሰራ አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ግን የሚተዳደረው ክልሉ በሚያወጣው የሲቪል ማህበረሰብ ደርጅቶች አዋጅ እንደሆነ አቶ ፋሲካ ተናግረዋል።

 

አሁን ላይ ሁሉም ክልሎች  የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በመመዝገብ ለማስተዳደር አዋጁን  አዘጋጅተዋል ብለዋል።

 

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና የመንግስት ተቋማት የትብብር መድረክ በየደረጃው መቋቋሙንም ነግረውናል።

 

አንዳንዶቹ ክልሎች አዋጁን ለማዘጋጀት እስከ ሁለት ዓመት እንደፈጀባቸው የተናገሩት አቶ ፋሲካው ሰፋ ያለ ውይይት ሲያደርጉበት ስለነበር ጊዜ ጠይቋል ብለዋል።

 

ህጉን የማውጣት ስራ ዘግይተው የጀመሩ ክልሎችም እንዳሉ ተናግረዋል።

 

በክልሎች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶችን ጉዳይ በዋናነት የሚከታተሉት የገንዘብ እና የፍትህ ቢሮዎች እንደሆኑ አቶ ፋሲካ ጨመረው ተናግረዋል።

 

የፍትህ ቢሮዎች ድርጅቶቹን የመመዝገብ ስራ ይሰራሉ ብለዋል።

 

ከገንዘብ ቢሮዎች ጋር ደግሞ ፕሮጀክት ተፈራርመው ወደ ስራ እንደሚገቡ ጠቅሰዋል።

 

አሁን ላይ በፌዴራል ደረጃ የተመዘገቡ ከ5700 በላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንዳሉ ሠምተናል።

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…

ንጋቱ ረጋሣ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

YouTube : https://shorturl.at/18TS1                   

 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page