አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ በውስጡ ምን ይዟል?
- 12 minutes ago
- 1 min read
የካቲት 25/2018
የሚኒስትሮች ምክር ቤት 53ተኛ ስብሰባውን ባደረገበት ወቅት በቱሪዝም ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ውይይት አድርጎ በምክር ቤቱ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ ወደ ስራ እንዲገባ ፈቃድ ሰጥቷል፡፡
ኢትዮጵያ የቱሪዝም ፖሊሲዋን ለመጨረሻ ጊዜ ያሻሻለችው በ2001 ዓ.ም ነበር፡፡
ታዲያ አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ በውስጡ ምን ይዟል? ስንል በፖሊሲ ማርቀቁ ላይ የተሳተፉትን አቶ ኤንዲ አሰፋን ጠይቀናቸዋል፡፡
የቱሪዝም ባለሙያው አቶ ኤንዲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ወደ ስራ እንዲገባ የተፈቀደው አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ በዘርፉ ከዚህ ቀደም ይነሱ ለነበሩ ችግሮች ምላሽ ይዞ መጥቷል ይላሉ፡፡
ከዚህ ቀደም ቱሪዝም መሰረተ ልማትን በተመለከተ በፖሊሲ ደረጃ የተቀመጠ ነገር አልነበረም አዲሱ ፖሊሲ በዚህ ዙሪያ ምላሽ አለው በዘርፉ የተማሩ ባለሙያዎችም እንዴት መሰማራት እንዳለባቸውም መንገድ አስቀምጧል ብለዋል፡፡
ይህም አሁን የተጀመሩ የቱሪዝም መሰረተ ልማቶች ልማትን የበለጠ እንዲጠነክር እገዛ ያደርጋል ይላሉ፡፡
የቱሪዝም ኢንቨስትመንት እንዴት መጠንከር እንዳለበት ፖሊሲው ምላሽ መያዙን የነገሩን አቶ ኤንዲ አሰፋ ከዚህ ቀደም ለውጪ ሀገር ቱሪስቶች የአደጋ ጊዜ ቅድመ ማስጠንቀቂያ መስጫ አሰራር አልነበረም አሁን ይህ አሰራር እንዲተገበር መንገድ ይከፍታል ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡
የወጣው አዲስ ፖሊሲ በትክክል ከተተገበረ ጥሩ ለውጥ በዘርፉ ያመጣል የሚል እምነት አለኝ የሚሉት ባለሙያው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰላም ሁኔታ ቢመለስና ሀገራት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ዜጎቻቸው እንዳይንቀሳቀሱ የጣሉት የጉዞ ክልከላ ቢያነሱ ከፍተኛ የጎብኚ ቁጥር ኢትዮጵያ የማግኘት እድል አላት ብለዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments