የቤት ሰራተኞችን በተመለከተ ግልፅ የሆነ ህግ ባለመበጀቱ የሚደርስባቸዉን ጥቃት ለመከላከልና መብታቸዉን ለማስከበር አስቸጋሪ እንዳደረገዉም አንድ ጥናት አመላከተ።
- Feb 26
- 1 min read
የካቲት 19/2018
የቤት ሰራተኞችን በተመለከተ ግልፅ የሆነ ህግ ባለመበጀቱ የሚደርስባቸዉን ጥቃት ለመከላከልና መብታቸዉን ለማስከበር አስቸጋሪ እንዳደረገዉም አንድ ጥናት አመላከተ።
ዕድሜያቸው ከ10 ዓመት በታችየሆኑ ህፃናት በቤት ሰራተኝነትተሰማርተው እንደሚገኙ በጥናቱ ተጠቁሟል።
አባዛኛዉን “ከገጠሪቱየሀገራችን ክፍሎችየተሻለ ህይወትን ፍለጋ ወደከተማ በመሰደድ በሰውቤት ተቀጥረው የቤቱን ስራ የሚከዉኑ፣ ልጆችን የሚሳድጉ፣ማዕድ የሚያዘጋጁ የቤት ሴት ሰራተኞች የተለያየጥቃት እንደሚደርስባቸዉም በጥናቱ ተጠቁሟል።

ፎረም ፎርሶሻል ስተዲስ (FSS)የተባለው መንግስታዊ ልሆነ የጥናትተቋም ከ2015 እስከ 2016 ዓ.ም አካሄደኩት ባለዉና ሰሞኑን ይፋ ባደረገዉ ጥናት፣ በሴት የቤትሰራተኞች ላይ ስነ ልቦናዊ እና ቃላዊ ጥቃት እንደሚደርስባቸዉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶሽዮሎጅና የሶሻል አንትሮፖሎጅ መምህር የሆኑት ሰላም ኢሳያስ( ዶ/ር ) ነግረውናል።
በጥናቱ ከተካተቱት ሰራተኞች መካከል አብዛኛዎቹ ከገጠር አካባቢ የመጡ ሲሆኑ፣ ተቀጥረዉ በሚሰሩባቸዉ ቤቶች አስከ 18 ሰዓት በስራ እንደማሳልፉም ተጠቁሟል።
እነዚህ ህፃናት ለትምህረትና የተሻለ ህይወት እንዲኖሩ በሚል ሰበብ በቅርብ ዘመድ ፣በአክስት፣ በአጎት፣ በወዳጅና በጓደኛ ወደ ከተማ ከተወሰዱ በኋላ የቤት ሰራተኛ ሆነዉ ከባባድ ስራዎችን እንደሚያከናዉኑ በጥናቱ መገኘቱ ተመላክቷል።
አብዛኛዉ የቤት ሰራተኞች ያለ እድሚያቸዉ የተወለዱበትን ቀዬ ለቀዉ፣ ከቤተሰብ ተነጥለዉ በዚህ የስራ ዘርፍ እንዲገቡ ከሚያደርጓቸዉ ዉስጥ ድህነት፣ ያለ እድሜ መዉለድ፣ ያለድሜ ጋብቻንን ሽሽትና ሌሎችም እንደሚገኙበት ጥናቱ ተጠቁሟል።
ይህንን ችግር ለማስቆም በአስቸኳይ ህግ ተበጅቶለት ደንብ ወጥቶለት ህግ አስፈፃሚዎች ሌሎች ይመለከተኛል የሚሉ ሁሉ በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ተመላክቷል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ገዛ ጌታሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments