top of page

ኢትዮጵያ በ2030 የሚደረገውን የዓለም ቱሪስት አስጎብኚ ባለሞያዎች ማህበራት ፌዴሬሽን ጉባኤ የማስተናገድ ፍላጎት አላት ተባለ።

  • 21 hours ago
  • 1 min read

የካቲት 18/2018  

 

ኢትዮጵያ በ2030 የሚደረገውን የዓለም ቱሪስት አስጎብኚ ባለሞያዎች ማህበራት ፌዴሬሽን ጉባኤ የማስተናገድ ፍላጎት አላት ተባለ።

 

ጉባኤውን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ማህበር ተናግሯል።

 

ፌዴሬሽኑ በቅርቡ በተደረገው የጃፓኑ ጉባኤ ላይ ከ2 ዓመት በኋላ የሚደረገውን ጉባኤ ለማዘጋጀት ጠይቆ በመጨረሻው ዙር ፔይሩ መመረጧን ተናግሯል።

 

ማህበሩ ይህንን ጥረት እያደረኩ ያለሁት ብቻዬን ነው ከመንግስት በኩል ድጋፍ ያስፈልገኛል ሲልም ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስረድቷል።

 

ማህበሩ የዓለም አቀፍ የቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ማህበራት ፌዴሬሽን አባል መሆኑ ባለሙያዎች የተሻለ ስልጠና እንዲያገኙ ይረዳል፤ ኢትዮጵያም ከአለም አቀፍ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ለመስራት እንድትችል ያግዛታል ብለዋል የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ማህበር ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ዮናስ ምትኩ።

 

የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ማህበር 350 አባላት እንዳሉት ተነግሯል።

 

አባል የሆነበት የአለም የቱሪዝም አስጎብኚ ባለሙያዎች ማህበራት ፌዴሬሽን ደግሞ 70 ሀገራትን በአባልነት የያዘና 200ሺህ አባላት ያሉት ነው ተብሏል።

 

በረከት አካሉ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

YouTube : https://shorturl.at/18TS1                   

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page