top of page

''ደንብ አስከባሪ ባለሞያዎች በሞያ ስነ ምግባር ታንፀው እንዲሰሩ እያደረግሁ ነው'' የደንብ ማስከበር ባለስልጣን

  • 18 hours ago
  • 1 min read

Updated: 2 minutes ago

የካቲት 20/2018


ደንብ አስከባሪዎች ህግን በተከተለ መልኩ እና ሞያዊ ስነ ምግባርን ጠብቀው የተሰጣቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ እያደረግሁ ነው ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ በማስከበር ባለስልጣን ተናገረ።


ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከዚህ ቀደም አልፎ አልፎ በደንብ አስከባሪዎች የሚፈጸሙ የሥነ ምግባር ጥሰቶች አሁን እየቀነሱ ነው ብሏል።


ከዚህ ቀደም ህግን ለማስከበር አልፎ አልፎ በደንብ አስከባሪዎች በኩል ይስተዋሉ የነበሩ የስነ ምግባር ግድፈቶች እንዳይኖሩ እየሰራ መሆኑንም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ተናግሯል።


ደንብ አስከባሪዎች ህግን በተከተለ መልኩ እና ሙያዊ ስነ-ምግባርን ጠብቀው የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ፣ ማህበረሰቡን ስነ-ምግባር በተሞላበት መልኩ እንዲያገለግሉ ለማስቻል የስነ ምግባር ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑን ሰምተናል።


ከዚህ ቀደም አንዳንድ ደንብ አስከባሪዎች በጎዳና ንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎችን ሲያንገላቱ፣ ሲደበድቡ፣ ብሎም የያዙትን እቃ ጭምር ሲበታትኑ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በባለሥልጣኑም የደንብ አስከባሪዎች ላይ በህገ-ወጦች ድብደባ እየተፈጸመባቸው ስለመሆኑ ሲናገር ነበር።


ይህው ጉዳይ በተንቀሳቃሽ ምስሎች ጭምር በስፋት በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወር እንደነበር ይታወሳል።


ይህንን የስነ ምግባር ግድፈት ለመፍታትም የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አባላቶቹን በስነ ምግባር የታነፁ ለማድረግ እያሰለጠንኩ ነው ብሏል።


ይህም ስልጠና በአንዳንድ ደንብ አስከባሪዎች የሚፈፀሙ የስነ ምግባር ጥሰቶች እንዲቀንሱ ማድረጉ ተነግሯል።



የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ እና የስልጠናና ቅድመ መከላከል ሀላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ጥቂት በማይባሉ ደንብ አስከባሪዎች ላይ የሚስተዋለውን የስነ ምግባር ጥሰት መከላከልና መቀነስ የሚቻለው የእርምት እርምጃ በመውሰድ ብቻ ባለመሆኑ አባላቶችን በስነ-ምግባር ለማነፅ የስነ ምግባር ስልጠናው እንዲጀምር ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።


ስልጠናውም ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር ውል በመግባት መሰጠት እንደጀመረ ነግረውናል።


በከተማው የሚፈፀም የደንብ ጥሰት 87 በመቶ መቀነሱንም ባለስልጣኑ ነግሮናል።


ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ  የስነ ምግባር ጥሰት ፈጽመዋል ባላቸው 18 ደንብ አስከባሪዎች ላይ ከደመወዝ ቅጣት እስከ ስራ ማገድ እርምጃ  መውሰዱንም ተናግሯል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….

ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page