top of page


#ሸገር_ትንታኔ
ሩሲያ የግዛት አካሎቼ ናቸው የምትላቸው የኩሪል ደሴቶች ጉዳይ ጃፓንን ከ80 አመታት በላይ ሲቆጭ ሲያንገበግባት ኖሯል፡፡ ሰሞኑን የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን በኩል ደሴቶች ጉብኝት ማድረጋቸው ጃፓንን ክፉኛ አንጨርጭሯታል፡፡ የኩሪል ውዝግብ ዳግም እየተጋጋለ ነው፡፡ ዝርዝሩን የኔነህ ከበደ አዘጋጅቶታል
2 days ago1 min read


በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሽፋኑ 63 በመቶ ገደማ ደርሷል፡፡
ነሐሴ 9 2018 በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሽፋኑ 63 በመቶ ገደማ ደርሷል፡፡ ይሁን እንጂ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ያላቸው ሰዎች 6 ሚሊዮን ብቻ ናቸው፡፡ ህዝቡ በነፍስ ወከፍ የሚያገኘው ኢነርጂ መጠንም ከሰሀራ በስተደቡብ ካሉት ሀገራት አኳያ ሲታይም ከእጥፍ በላይ ያነሰ ነው፡፡ ይህንን የኤሌክትሪክ ሀይል ችግርን ሙሉ ለሙሉ ለመፍታት ፣ ሁሉንም የሀገሪቱ ህዝብ ከኤሌክትሪክ ጋር ለማገናኘት 30.65 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ ሀብት ከየት ይመጣል ? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ.... ቴዎድሮስ ወርቁ ጠይቋል
2 days ago1 min read


ያልሰራሁትን ፣ ያላተረፍኩትን ግብር ክፈል ተባልኩ የሚሉ ነጋዴዎች መንግስት ይመልከተን ሲሉ ይሰማሉ።
ነሐሴ 9 2018 ያልሰራሁትን ፣ ያላተረፍኩትን ግብር ክፈል ተባልኩ የሚሉ ነጋዴዎች መንግስት ይመልከተን ሲሉ ይሰማሉ። መንግስት በበኩሉ የሚሰበስበው ግብር አሁንም ዝቅተኛ መሆኑን ያስረዳል፡፡ የመንግስትም ገቢ እንዲጨምር ፣ ነጋዴዎችም ያላገኙትን ክፈሉ እንዳይባሉ ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው? ፍቅሩ አምባቸው
2 days ago1 min read


ሌብነት ወይንም ሙስና አገልግሎት ሰጪንና ተቀባይን የሚያግባባ ብቸኛ ቋንቋ የሆነ መስሏል፡፡
ነሐሴ 9 2018 ሌብነት ወይንም ሙስና አገልግሎት ሰጪንና ተቀባይን የሚያግባባ ብቸኛ ቋንቋ የሆነ መስሏል፡፡ ህብረተሰቡም መሬት ፣ ንግድ ፣ ገቢዎች ፣ ጉምሩክ ፣ ግንባታ ሙስና የከፋባቸው ተቋማት ናቸው ብሎ እንደሚያምን ጥናት አሳይቷል፡፡ ሌቦችን ፣ ሙሰኞችን ለመቅጣት ግን ህግ አለ፡፡ ሙስናንን ለመከላከል በሚል የተቋቋሙ ተቋማት አሉ፡፡ መንግስትም ሌቦችን እየቀጣሁ ነው ፣ የምታገሰው ጉዳይ አይደለም ይላል፡፡ ግን ሌብነት ቀጥሏል፡፡ ለምን? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ..... ያሬድ እንዳሻው
2 days ago1 min read
የነሐሴ 9 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ኮንጎ የኮንጎ ኪንሻሣው የኢቦላ ወረርሽኝ አድማሱን እያሰፋ ነው ተባለ፡፡ ወረርሽኙ ወደ ተጨማሪ ግዛትም መዛመቱን የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠሪያ /አፍሪካ CDC/ መረጃ ማሳየቱን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ በኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ ያዳረሳቸው ግዛቶች ብዛት 6 ደርሷል፡፡ ኢቱሪ ወረርሽኙ ከፍተኛ ጫና ያሳደረባት ግዛት ነች፡፡ ወረርሽኙ መቀስቀሱ ከተነገረ 3 ወር ሆኖታል፡፡ እስከ ትናንትም የገደላቸው ሰዎች ብዛት 2 ሺህ 100 ደርሷል፡፡ የኮንጎው ኢቦላ በከፍተኛ የመዛመት ፍጥነት ላይ ነው፡፡ በታሪክም ታላቁ የኢቦላ ወረርሽኝ ሊሆን የሚችልበት እድል የሰፋ ነው ተብሏል፡፡ #ሩሲያ የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭለድሚር ፑቲን በቀጠናዊ የፀጥታ እና ደህንነት ጉዳይ ከሰሜን ኮሪያ ጋር በትብብር እንሰራለን አሉ፡፡ ፑቲን ከሰሜን ኮሪያ ጋር ቀጠናዊ የፀጥታ እና የ
2 days ago2 min read
የነሐሴ 8 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#የተባበሩት_አረብ_ኢሚሬትስ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በሆርሙዝ ወሽመጥ በሁለት መርከቦቼ ላይ ጥቃት ሰንዝራለች ያለቻትን ኢራንን በብርቱ ኮነነቻት ተባለ፡፡ ኢራን በነዳጅ ጫኝ መርከቦቻችን ላይ ጥቃት ሰንዝራለች ሲል ከበድ ያለ ተቃውሞውን ያሰማው የኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንደሆነ አልጀዚራ እና AFP ፅፈዋል፡፡ ያም ሆኖ የኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በመርከቦቻችንም ሆነ በባህረኞቻቸው ላይ የደረሰ አንዳችም ጉዳት የለም ማለቱ ተሰምቷል፡፡ ኢሚሬትስ በሆርሙዝ መሰል ጥቃት ተሰንዝሮብኛል ስትል ሳምንት ባልሞላው ጊዜ የአሁኑ 2ኛዋ ነው ተብሏል፡፡ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜም ኢሚሬትስ በሆርሙዝ ወሽመጥ በሌላ ነዳጅ ጫኝ መርከቤ ላይ ጥቃት ተሰንዝሮባታል ብላ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡ ኢራን ትዕዛዜን በሚተላለፉ መርከቦች ላይ እርምጃ እወስዳለሁ
3 days ago2 min read
የቱሪዝም ተጓዥችና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሀገርን ገፅታ በመገንባትና ቱሪዝምን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳላቸው ይነገራል፡፡
ነሐሴ 8 2018 የቱሪዝም ተጓዥችና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሀገርን ገፅታ በመገንባትና ቱሪዝምን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳላቸው ይነገራል፡፡ ኢትዮጵያም ይህንን መልካም አጋጣሚ በአግባቡ ለመጠቀም እነዚህ የዘርፉ ባለሙያዎች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ አስፈላጊውን መረጃና ጥበቃ ማድረግ እንደሚገባ ባለሙያዎች አሳስበዋል። የቱሪዝም ተጓዥ ብሎገሮች ወይም ፀሀፊዎች በየሄዱበት የተመለከቱትን በጎም ይሁን መጥፎ ኩነቶች ቀጥታ ለተከታዮቻቸው ያሳውቃሉ፡፡ ይሄ ስራቸው ደግሞ በአለም አቀፍ አስጎብኚ ድርጅቶች ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጠው ያነጋገርናቸው የቱሪዝም ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ገንዘብ ከፍሎ በአለም አቀፍ የቱሪዝም ማስታወቂያ መስክ ላይ ማስተዋወቅ ለማይችሉ ሀገራት እነዚህ የቱሪዝም ፀሀፊዎች ፣ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ተፅ
3 days ago1 min read


ገዳ ባንክ አዲስ የሚያስገነባውን የህንፃ ዲዛይን ይፋ አደረገ፡፡
ነሐሴ 8 2018 ገዳ ባንክ አዲስ የሚያስገነባውን የህንፃ ዲዛይን ይፋ አደረገ፡፡ ባንኩ አስገነባዋለሁ ያለው ዋና መስሪያ ቤት ሜክሲኮ አካባቢ በ6 ሺህ 579 ካሬ ሜትር ላይ እንደሚያርፍም ተናግሯል፡፡ ገዳ ባንኩ ይፋ ያደረገው የህንፃው ዲዛይን የኪነ-ሕንፃ ጥበብን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር ያቀናጀ መሆኑን የተናገሩት የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ቡልቶ የዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ ለማካሄድ የዲዛይን ውድድር ሲያካሂድ ቆይቷል ብለዋል። ውድድሩ በዘርፉ በታወቁ ገለልተኛ ዳኞች ጥብቅ ምዘና ሲደረግበት የቆየ መሆኑ የተነገረ ሲሆን መስፈርቱን አሟልተው ለውድድር ከቀረቡ 18 ተወዳዳሪዎች አንድ ድርጅት አሸንፏል ተብሏል። ወደ ስራ ከገባ ሶስት አመታትን ያስቆጠረው ገዳ ባንክ ከ32 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች እንዳሉት ያነሳ ሲሆን ጠቅላላ ሀብቴ 12.6 ቢሊየን ብ
3 days ago1 min read
በአዲስ አበባ አጀንዳ ላይ የመከረውን ተመካካሪ ቡድን ጨምሮ ስምንቱም በአምስት መቶ ተሳታፊዎች የተቋቋሙ ቡድኖች በየቡድናቸው ሲመካከሩ ቆይተው በምክረ ሐሳቦች ላይ መስማማታቸውን ኮሚሽኑ ተናገረ።
ነሐሴ 7 2018 በአዲስ አበባ አጀንዳ ላይ የመከረውን ተመካካሪ ቡድን ጨምሮ ስምንቱም በአምስት መቶ ተሳታፊዎች የተቋቋሙ ቡድኖች በየቡድናቸው ሲመካከሩ ቆይተው በምክረ ሐሳቦች ላይ መስማማታቸውን ኮሚሽኑ ተናገረ። የምክክር ሂደቱን አስመልክተው ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ምክትል ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ፣ ሁሉም ተመካካሪ ቡድኖች በቀረቡ ምክረ ሐሳቦች ላይ ተስማምተው መፈረማቸውን አስረድተዋል። አከራካሪ ሆኖ የሰነበተው ቡድን 7 ወይም በአዲስ አበባ ላይ የሠራው ቡድን በምክረ ሐሳቡ ላይ መግባባት ላይ ደርሷል ተብሏል። "በዚህ ሂደት ውስጥ አለመግባባቶች፣ ግጭቶች አልነበሩም አይባልም። በመኖራቸው ምክንያት ግን ይህ ምክክር አስፈላጊ መሆኑን የበለጠ አረጋግጦልናል። እነዚያ ግጭቶች ተፈተው፣ ተደማምጠው፣ ወደ አንድ የጋራ ሐሳብ፣ አማካይ ሐሳብ ላይ ደርሰው
4 days ago1 min read


በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዓይን ሐኪምና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የዓይን ህክምና ትምህርት ክፍል መስራች የነበሩት የዶ/ር ጳውሎስ ቀንአ የቀብር ሥነ -ሥርዓት ዛሬ ከሰዓት በኋላ በጴጥሮስ ወ/ጳውሎስ ተፈፀመ፡፡
ነሐሴ 7 2018 በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዓይን ሐኪምና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የዓይን ህክምና ትምህርት ክፍል መስራች የነበሩት የዶ/ር ጳውሎስ ቀንአ የቀብር ሥነ -ሥርዓት ዛሬ ከሰዓት በኋላ በጴጥሮስ ወ/ጳውሎስ ተፈፀመ፡፡ የዓይን ህክምናን በቤሩት ሊባኖስ በሚገኘው የአሜሪካ ዩኒቨርስቲ ተምረው የተመረቁት ዶ/ር ጳውሎስ ቀንአ ከኢትዮጵያ ውጪ በርካታ የስራ እድሎች ቀርበውላቸው የነበረ ቢሆንም በሀገር ቤት በቂ የህክምና ዶክተሮች የሉንም በማለት አገርቸውን በትጋት ማገልገላቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ ዶክተር ጳውሎስ፣ በ1964 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ለአጭር ጊዜ የውጭ ሀገር ባለሙያ ጋር አብረው መስራት ጀምረው እንደነበር የሕይወት ታሪካቸው ይናገራል፡፡ በ1980 ዓ.ም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የመጀመሪያውን የሶ
4 days ago1 min read


ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት አመት 23 አነስተኛ የፀሀይ ሀይል ማመንጫዎችን ሰርታ ወደ አገልግሎት አስገብታለች ተባለ፡፡
ነሐሴ 7 2018 ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት አመት 23 አነስተኛ የፀሀይ ሀይል ማመንጫዎችን ሰርታ ወደ አገልግሎት አስገብታለች ተባለ፡፡ በዓለም ገበያ ዋጋው በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ መሆኑ እና የሚያመርተው ሀይልም እያደገ በመሆኑ ኢትዮጵያ በስፋት የፀሐይ ሀይል ማመንጫዎችን ትገነባለች ተብሏል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ... ቴዎድሮስ ወርቁ
4 days ago1 min read
በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ሃዲዶች ላይ ለአካል ጉዳተኞች የተሰራው መወጣጫ(ራምፕ) ለዓመታት በመዘጋቱ አካል ጉዳተኞች ባቡር መጠቀም ለማቆም ተገደናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ነሐሴ 7 2018 በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ሃዲዶች ላይ ለአካል ጉዳተኞች የተሰራው መወጣጫ(ራምፕ) ለዓመታት በመዘጋቱ አካል ጉዳተኞች ባቡር መጠቀም ለማቆም ተገደናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። የሃዲዱ ጠባቂ የፀጥታ አካላት የተዘጋውን መወጣጫ(ራምፕ) እንዲከፍቱላቸው ቢጠይቁም የተሰጣቸው ምላሽ እስከ ድብደባ የደረሰ መሆኑንም ቅሬታቸውን ያቀረቡ አካል ጉዳተኞች ነግረውናል፡፡ በከተማዋ ያሉ የቀላል ባቡር ሃዲዶች ለጉዳት አልባው የደረጃ መወጣጫ፤ለአካል ጉዳተኞች ደግሞ ለዊልቸርና ክራንች ተጠቃሚዎች የተመቸ የመወጣጫ (ራምፕ) እንዳለው የነገሩን ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ ለአካል ጉዳተኛው የተሻለው የትራንስፖርት አማራጭ ባቡር ቢሆንም በዚህ ምክንያት መጠቀም ለማቆም ተገደናል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ብሄራዊ ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተሰማ ሰብስቤ
4 days ago1 min read
የነሐሴ 7 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ዩጋንዳ ዩጋንዳ ከአውሮፓ የሚባረሩ የ3ኛ አገር ስደተኞችን ልትቀበል ነው ተባለ፡፡ ዩጋንዳ ከአውሮፓ ተባራሪዎቹን ተቀብላ ለማስተናገድ መዘጋጀቷን ካቲሜሪኒ የተሰኘ የግሪክ ጋዜጣ መዘገቡን አናዶሉ ፅፏል፡፡ ጋዜጣው ዘገባውን ያሰራጨው ዲፕሎማሲያዊ ምንጮችን በዋቢነት በመጥቀስ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የሐሳቡ ቀዳሚ አፍላቂዎች ጀርመን ፣ ኦስትሪያ ፣ ዘ ኔዘርላንድስ እና እና ግሪክ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡ ዩጋንዳ በውጥኑ ቀዳሚ ስራ ላይ ማዋያ 10 ሺህ የ3ኛ አገር ከአውሮፓ ተባራሪ ጥገኝነት ፈላጊዎችን ተቀብላ ታስተናግዳለች ተብሏል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ሰነድ አልባዎች ናቸው የተባሉ የ3ኛ አገራት ጥገኝነት ፈላጊዎችን ወደተለያዩ የአፍሪካ አገሮች እያባረረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ዩጋንዳ ከአውሮፓ ተባራሪዎቹን ጥገኝት ፈላጊዎች ልትቀበል ነው
4 days ago2 min read
በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ሊከሰት የሚችለው ኤልኒኖ በግብርና እንዲሁም አምራች እና የአገልግሎት ዘርፎች ላይም ተፅዕኖ ይኖረዋል ተባለ።
ነሐሴ 7 2018 በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ሊከሰት የሚችለው ኤልኒኖ በግብርና እንዲሁም አምራች እና የአገልግሎት ዘርፎች ላይም ተፅዕኖ ይኖረዋል ተባለ። ከአስር ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የታየው የኤልኒኖ ተፅዕኖ የእህል ምርት ውጤትን ከ15 እስከ 20 በመቶ እንዲቀንስ አድርጎ እንደነበር አንድ የዘርፉ ተመራማሪ ነግረውናል። ክስተቱ ከፍቶ በታየባቸው የኢትዮጵያ ምስራቃዊ አካባቢዎች የእህል ምርት ቅናሹ ከ40 በመቶ በላይ እንደነበር በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰርና በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ተባባሪ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ሠለሞን ዜና ያስታወሱት። ተፅዕኖው ምግብ እና ለስላሳ መጠጥ አምራች ፋብሪካዎች ላይም መታየቱን ዶክተር ሠለሞን ተናግረዋል። የእነዚህ ፋብሪካዎች ምርታማነት በ25 በመቶ ቀንሷል ያሉ ሲሆን ሽያጫቸውም በ39 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቅ
4 days ago1 min read


በኢትዮጵያ እየተመረተ ካለው የኤሌክትሪክ ኃይል ግማሽ ያህሉ ከህዳሴ ግድብ መሆኑ ተነገረ።
ነሐሴ 7 2018 በኢትዮጵያ እየተመረተ ካለው የኤሌክትሪክ ኃይል ግማሽ ያህሉ ከህዳሴ ግድብ መሆኑ ተነገረ። በአሁኑ ወቅት የታላቁ ህዳሴ ግድብ በሙሉ አቅሙ ማለትም 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እያመረተ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ነግሮናል፡፡ እየተጠናቀቀ ባለው የ2018 ዓመት እንደ ሀገር 38 ሺህ ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ለማምረት ውጥን ተይዞ 35 ሺህ 671 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል መመረቱንና፤ከተመረተው ግማሽ ያህሉ ማለትም 18 ሺህ 360 ጊጋ ዋት ሰዓት የተመረተው ከህዳሴ ግድብ መሆኑን የተቋሙ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ነግረውናል፡፡ ከአፍሪካ ግዙፉ የሀይል ማመንጫ የሆነው ግድቡ ኢትዮጵያ የምታመርተውን የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን የመጨመሩን ያክል ሃገሪቱ ለሽያጭ የምታቀርበውን የኃይል መጠንም ጨምሮታል የሚሉት አቶ ሞገ
4 days ago1 min read
የኤሌክትሪክ ታሪፍ በየጊዜው ሲጨምር ይታያል፡፡
ነሐሴ 7 2018 የኤሌክትሪክ ታሪፍ በየጊዜው ሲጨምር ይታያል፡፡ በዚህም ደንበኞች ቅሬታ ያቀርባሉ ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ አዲስ የታሪፍ ጭማሪ አለማድረጉን፤ የአሁኑ የዋጋ ለውጥ ከ2017 ጀምሮ በ16 ዙር ለማስፈጸም የታቀደው አሰራር አካል ነው ብሏል፡፡ እንደውም ከሁለት አመት በፊት ተግባራዊ ያደረኩት የታሪፍ ማሻሻያ የኑሮ ውድነትን እና የዋጋ ግሽበትን እንዳያባብስ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ደንበኞች የመክፈል አቅም ያገናዘበ እና ድጎማ የሚያርግም ነው ብሏል። በ2017 ዓ.ም ያደረኩት የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማስተካከያ በአንድ ጊዜ ተጠቃሚው ላይ ጫና እንዳያሳድር በማሰብ በ4 ዓመታት ውስጥ በየሶስት ወር ተከፋፍሎ በ16 ጊዜ ተግባራዊ እንዲሆን ብቻ ነው ያደረኩት ሲል ያስረዳል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ... ፋሲካ ሙሉወርቅ
4 days ago1 min read
ዛሬ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ በ161 ብር ከ79 ሳንቲም መሸጡ ተነገረ፡፡
ነሐሴ 6 2018 ዛሬ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ በ161 ብር ከ79 ሳንቲም መሸጡ ተነገረ፡፡ ዛሬ ይፋ በሆነው ጨረታ 125 ሚሊዮን ዶላር ለጨረታ ቀርቧል ተብሏል፡፡ በጨረታው 28 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን በጨረታው የድርሻቸውን ተጫርተው የወሰዱ ባንኮች ቁጥር 9 መሆናቸው ተነግሯል፡፡ ለጨረታው የቀረበው ከፍተኛው ገንዘብ 163 ብር ከ98 ሳንቲም ሲሆን ዝቅተኛው 159 ብር ከ98 ሳንቲም ሆኗል፡፡ ዛሬ ይፋ በሆነው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 125 ሚሊዮን ዶላር መቅረቡን ይፋ ያደረገው ብሔራዊ ባንክ ቀጣዩን የጨረታ ጊዜም በፕሮግራሙ መሰረት ይፋ አደርጋለው ብሏል፡፡ ዛሬ ይፋ በሆነው ጨረታ ላይ የቀረበው የውጭ ምንዛሬ መጠን 125 ሚሊየን ዶላር ቢሆንም በባንኮቹ በኩል የቀረበው ፍላጎት ግን 470.17 ሚሊየን ዶላር
5 days ago1 min read
ብሔርን መሰረት ያደረገው የክልሎች አወቃቀር ይቀጥል በሚለው የ500 ቡድን የሀገራዊ ምክክር ተመካካሪዎች ተስማምተዋል፡፡
ነሐሴ 6 2018 ብሔርን መሰረት ያደረገው የክልሎች አወቃቀር ይቀጥል በሚለው የ500 ቡድን የሀገራዊ ምክክር ተመካካሪዎች ተስማምተዋል፡፡ አገሪቱ የምትከተለው የመንግስት ሥርዓት ምን ይሁን? ለሚለው ተመካካሪዎቹ ኢትዮጵያ በፕሬዚዳንት ትመራ በሚለው ላይ ሙሉ ለሙሉ ተስማምተዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ከየት ይመረጥ? ሥርዓቱ ፓርላምታዊ ሆኖ ከፓርላማ ይመረጥ? ወይስ ሙሉ በሙሉ ሥርዓቱ ፕሬዚዳንታዊ ሆኖ በህዝብ ቀጥታ ይመረጥ የሚለው ግን ሁሉምን አስማሚ አልሆነም ፡፡ በዚህም በመንግሥት አደረጃጀት እና ቅርፅ በፖለቲካ ሥርዓት፣ ውክልና የምርጫ ሥርዓት ስር ሲመከር የሰነበተው ተመካካሪ ቡድን እነዚህ አጀንዳዎች በልዩነት ወደ ቀጣይ ምዕራፍ እንዲተላለፉ ወስኗል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ውክልና ምን ይምሰል? የሚለውም ሌላው በልዩነት ያለፈ ንዑስ አጀንዳ ነው ፡፡ ሙ
5 days ago1 min read
የነሐሴ 6 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ደቡብ_አፍሪካ በደቡብ አፍሪካ በአንድ የማዕድን ዝቃጭ ማስወገጃ ስፍራ መደርመስ 14 ሰዎች የሞቱበት አደጋ እየተመረመረ ነው ተባለ፡፡ ሌሎች 8 ሰዎች ደግሞ አካላዊ ጉዳት እንደገጠማቸው ቢቢሲ ፅፏል፡፡፡ በዝቃጩ ውስጥ የተቀበሩ ሌሎች ሰዎች ሳይኖሩ አይቀሩም ተብሏል፡፡ በአደጋው የሞቱት እና አካላዊ ጉዳት የገጠማቸው ሕገ-ወጥ የማዕድን ሰራተኞች መሆናቸው ታውቋል፡፡ አደጋው የደረሰበት ከተዘጋ የቆየ የማዕድን ስፍራ እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡ ስፍራው ቀደም ሲል ፕላቲኒየም እና ሌሎችም ማዕድናት ሲመረቱበት የቆየ ነው ተብሏል፡፡ #ሊባኖስ የሊባኖስ ፓርላማ የሞት ቅጣትን የሚያስቀር ህግ አፀደቀ፡፡ የፓርላማው አባላት የሞት ቅጣትን የሚያስቀረውን ህግ ያፀደቁት በአብላጫ ድምፅ እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡ የሊባኖሱ የፍትህ ሚኒስትር የህጉን መፅደቅ ታሪካዊ ሲሉ
5 days ago2 min read
በመንግሥት አደረጃጀት እና ቅርፅ አጀንዳ ሥር ሲመክሩ የቆዩ የሥራ ቡድኖች ከ53 ንዑሳን ጉዳዮች ውስጥ በ50ው ላይ ተስማምተው ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ተሻግረዋል።
በመንግሥት አደረጃጀት እና ቅርፅ አጀንዳ ሥር ሲመክሩ የቆዩ የሥራ ቡድኖች ከ53 ንዑሳን ጉዳዮች ውስጥ በ50ው ላይ ተስማምተው ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ተሻግረዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ ተመካካሪ፤ ሦስት ንዑሳን አጀንዳዎች ግን ለአስማሚ ግብረ ኃይል ይላካሉ መባሉን ነግረውናል። ወደ አስማሚ ግብረ ኃይል ይላካሉ ከተባሉት ንዑሳን አጀንዳዎች ውስጥ የመንግሥት ሥርዓቱ ፓርላሜንታዊ ሆኖ ከፓርላማ የሚመረጥ ፕሬዝዳንት ርዕሰ ብሔርም ርዕሰ መንግሥትም ሆኖ አገሪቱን ይመራት፤ ይህም በየስድስት ዓመቱ የሚካሄድ ሁለት የምርጫ ዘመን ይኑረው የሚለው አንዱ ነው። ሙሉ ሥርዓቱ ፕሬዚዳንታዊ ይሁን እና ፕሬዚዳንቱ በቀጥታ ከሕዝብ ይመረጥ የሚለውም በዚህ ሥር የቀረበው ነው። «የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ውክልና እንዴት ይሁን? ብሔሮች በምክር ቤቱ በአንድ ሚሊዮን አን
5 days ago2 min read


የሃይማኖት ጉዳዮች እና የሰላም ግንባታ አጀንዳ ተመካካሪዎች ባቀረቧቸው ምክረ ሀሳቦቻቸው ላይ መግባባታቸውን የምክክር ኮሚሽን ይፋ አደረገ፡፡
ነሐሴ 5 2018 የሃይማኖት ጉዳዮች እና የሰላም ግንባታ አጀንዳ ተመካካሪዎች ባቀረቧቸው ምክረ ሀሳቦቻቸው ላይ መግባባታቸውን የምክክር ኮሚሽን ይፋ አደረገ፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እያካሄደ ባለው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በኮሚሽኑ ምክር ቤት በተለዩ ስምንት አጀንዳዎች ላይ ምክክር እየተደረገ ነው፡፡ አጀንዳዎቹ 500 አባላት ባሏቸው ስምንት የስራ ቡድኖች ምክክር እየተደረገባቸው ይገኛሉ፡፡ በኮሚሽኑ የአሰራር ሥነ-ዘዴ መሰረት 500 አባላት ያሉት አንድ ቡድን በአንድ አጀንዳ ላይ እየተመካከረ ነው፡፡ በዚህም በሃይማኖት ጉዳዮች እና በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ለይ ሲመካከሩ የቆዩት ሁለት ቡድኖች ዛሬ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጠናቀሩ ምክረ ሀሳቦቻቸው ላይ ተስማማተው በተዘጋጀው ቃለ ጉባኤ ላይ ተፈራርመዋል
6 days ago1 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page
_edited.jpg)
