ነሀሴ 16 2017 - የዲጂታል የአድራሻ ሥርዓት በ6 ከተሞች በ4 ወር ውስጥ ስራ እንደሚጀምር የስፔስ ሳይንስና ጂኦ እስፓሻል ኢንስቲትዩት ተናገረ
- sheger1021fm
- 2 days ago
- 1 min read
የዲጂታል የአድራሻ ሥርዓት አዲስ አበባን ጨምሮ በ6 ከተሞች በ4 ወር ውስጥ ስራ እንደሚጀምር የስፔስ ሳይንስና ጂኦ እስፓሻል ኢንስቲትዩት ተናገረ፡፡

ተጨማሪ በ9 ከተሞች ላይ የዲጂታል የአድራሻ ስርዓተ ስራዎች እየተሰራ ሲሆን በ2018 በጀት ዓመት አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡
የስፔስ ሳይንስና ጂኦ እስፓሻል ኢንስቲትዩት የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት ፕሮጀክት ማናጀር አግማሴ ገበየሁ እንደነገሩን በአዲስ አበባ፣ ባህር ዳር ጨምሮ በ6 ከተሞች የዲጂታል የአድራሻ ሥርዓት ተጠናቆ ሙከራ እየተደረገ ነው፡፡
በቢሾፍቱ ከተማ ይህ አገልግሎት ወደ ስራ ገብቷል ያሉት አቶ አግማሴ ገበየሁ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሙከራ ተደርጎ ወደ ስራ መግባቱን ነግረውናል፡፡
የዲጂታል አድራሻ ሥርዓቱ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ወደ አገልግሎት ሲገባ በዲጂታል መንገድ እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶች የበለጠ ታማኝ እንዲሆኑና ስራዎች እንዲቀላጠፉ ያደርጋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
댓글