ነሀሴ 15 2017 በአዲስ አበባ በመጪው ዓመት ቢያንስ 500,000 ነባር የኤሌክትሪክ ቆጣሪዎች በዘመናዊ ቆጣሪዎች ይቀየራሉ ተባለ።
- sheger1021fm
- Aug 21
- 1 min read
ነባሮቹ ቆጣሪዎች በሂደት ሙሉ ለሙሉ በዘመናዊ ቆጣሪዎች እንደሚተኩም ተነግሯል።
እስከ አሁን በሙከራ ደረጃ የቆየው አዲሱ ቆጣሪ ደንበኞች ካሉበት ሆነው የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን የሚያውቁበት እንደሆነ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመለክታል።
ዘመናዊዎቹ ቆጣሪዎች ደንበኞች ወደ ተቋማት መሄድ ሳያስፈልጋቸው በስልካቸው ካርድ እየሞሉየሚጠቀሙበትን ሥርዓትም የያዙ እንደሆኑ በአገልግሎቱ የኤሌክትሪክ ኔትወርክ ቁጥጥር ሀላፊ አቶ ዘሪሁን አበበ ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ካሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ደንበኞች 400,000 ያህሉ የቅድመ ክፍያ ካርድን በመጠቀም አገልግሎት የሚያገኙ ናቸው ተብሏል።
በዚህ የቅድመ ክፍያ ካርድ አገልግሎት ላይ በየጊዜው የተለያዩ ቅሬታዎች እንደሚነሱ አቶ ዘሪሁን ተናግረዋል።
ዘመናዊዎቹ ቆጣሪዎች እነዚህን ቅሬታዎች ያስቀራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አክለዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ቴዎድሮስ ወርቁ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments