ነሀሴ 16 2017 - የቴምር ፌስቲቫል ከነሃሴ 20 እስከ 22 ድረስ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እንደሚካሄድ የግብርና ሚኒስቴር ተናገረ
- sheger1021fm
- Aug 22
- 1 min read
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል ከነሃሴ 20 እስከ 22 ድረስ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እንደሚካሄድ የግብርና ሚኒስቴር ተናገረ።
ፌስቲቫሉ የግብርና ሚኒስቴር፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስና ከከሊፋ አለማቀፍ አዋርድ ለቴምርና ለግብርና ፈጠራ በጋራ ያሰናዱት ነው።
የግብርና ሚስትር ዴዔታ መለስ መኮንን(ዶ/ር) የመጀመርያው #የቴምር_ፌስቲቫል መካሄዱ ኢትዮጵያ በዘርፉ ጠንክራ እንድትሰራ ያደርጋታል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የቴምር ምርት ከውጪ ታስገባለች፣ ይህንን በሃገር ውስጥ ለመተካት መንግስት እቅድ አለው ፌስቲቫሉም መነቃቃትን ይፈጥራልም ሲሉ ጠቅሰዋል።
የከሊፋ አለማቀፍ አዋርድ ለቴምርና ለህብርና ፈጠራ ዋና ፀሀፊ አብዱልዋሃብ አልቡሃሪ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ በዘርፉ ለምታደርገው ጥረት ድጋፍ እንደሚያደርጉና አብረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
40 አለማቀፍና ሀገር አቀፍ ተቋማት በፌስቲቫሉ ይሳተፋሉ ተብሏል።
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments