ነሀሴ 16 2017 - ኦፌኮ በ2018 ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ምርጫ አስቻይ ሁኔታ ከሌለ ላይሳተፍ እንደሚችሉ ተናገረ
- sheger1021fm
- 1 day ago
- 1 min read
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ፓርቲ ( #ኦፌኮ ) በ2018 ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ምርጫ አስቻይ ሁኔታ ከሌለ ላይሳተፍ እንደሚችሉ ተናገረ፡፡
ፓርቲው ይህን ካደረገ ለሁለት ተከታታይ ምርጫ ራሱን ያገልላል ማለት ነው፡፡
የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ከወራት በኋላ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ምርጫ ላይ ለመሳታፍ ተንቀሳቅሶ የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ እና በነጻነት ለመምረጥ አስቻይ ሁኔታ ያስፈልጋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ፓርቲው ከ4 ዓመት በፊት ተደርጎ በነበረው ሀገራዊ ምርጫም አልተሳተፈም፡፡
በቀጣይ በሚካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የማይሳተፍ ከሆነ ደግሞ በምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ መሰረት ህጋዊ እውቅናው ይሰረዛል፡፡
ይህን በተመለከተ የጠየቅናቸው የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ብንሰረዝም እንሰረዝ እንጂ አስቻይ ሁኔታ ከሌለ መስፈርት ለማሟላት ኦፌኮ በምርጫው አይሳተፍም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ተጠይቀው ምላሽ የሰጡት የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሀይሉ ምርጫ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ መኖሩን ጠቁመው አንዳንድ ሰላም የሌለባቸው አካባቢዎችም ምርጫው እስኪደርስ ሰላም ይሆናሉ የሚል እምነት እንዳላቸው መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
Comments