top of page


አሜሪካ የሆርሙዝን የባህር መተላለፊያ ወሽመጥ እና የኢራንን ወደቦች መዝጋቷን ቻይና በጥብቅ ተቃወመችው፡፡
ሚያዝያ 7/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች #አሜሪካ አሜሪካ የሆርሙዝን የባህር መተላለፊያ ወሽመጥ እና የኢራንን ወደቦች መዝጋቷን ቻይና በጥብቅ ተቃወመችው፡፡ እስያዊቱ አገር የአሜሪካን እርምጃ አደገኛ ነው እንዳለችው አናዶሉ ፅፏል፡፡ ሀላፊነት የጎደለውም ስትል ጠርታዋለች፡፡ የቻይና የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአሜሪካ የባህር ወሽመጡን መዝጋት ውጥረቱን ይበልጥ የሚያባብስ ነው የሚል መግለጫ አውጥቷል፡፡ የቻይናው የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ለችግሩ መቃለል ዘላቂ እና አጠቃላይ የተኩስ አቁም የሚደረግበት መላ ቢፈለግ የተሻለ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ በአለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ አቅርቦቱን ችግር እያባባሰው መምጣቱ ይነገራል፡፡ አሜሪካ የባህር መተላለፊያ ወሽመጡን ከሰኞ ቀን 8 ሰዓት አንስቶ ዘግቼዋለሁ ማለቷን መረጃው አስታውሷል፡፡ #ናይጀር
Apr 151 min read


መጋቢት 28/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች
#ፍልስጤም የፍልስጤማውያኑ የጦር እና የፖለቲካ ድርጅት (ሐማስ) የእስራኤል ጦር በጋዛ የሚፈፀመውን ጥቃት አቁሞ ጠቅልሎ ካልወጣ በስተቀር በጭራሽ ትጥቅ አልፈታም አለ፡፡ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጋዛ ሰርጥ የወደፊት ሰላም ቀደም ሲል ያቀረቡት ባለ 20 ነጥቦች የሰላም እቅድ ሐማስ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንዲፈታ የሚጠይቅ መሆኑን ሬውተርስ አስታውሷል፡፡ የሐማስ የበላዮች በዚህ ጉዳይ ትናንት ከአደራዳሪዎቹ ጋር መመካከራቸው ተሰምቷል፡፡ ይሄን ተከትሎም የሀማስ ወታደራዊ ክንፍ ቃል አቀባይ አቡ ኦባይዳ የእስራኤል ጦር ከመንፈቅ በፊት በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት የጋዛ ሰርጥን ለቅቆ ካልወጣ በስተቀር በጭራሽ ትጥቅ አንፈታም ብለዋል፡፡ በጋዛ የወደፊት ዘላቂ ስለማለቱ የሐማስ ትጥቅ መፍታት ነገር በጣሙን አስቸጋሪው ጉዳይ እንደሆነ ይነገራል
Apr 62 min read


የፔሩ ፓርላማ ጆሴ ማሪያ ባልካዛርን የሀገሪቱ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት አድርጎ ሰየመ።
የካቲት 13/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ፔሩ የፔሩ ፓርላማ ጆሴ ማሪያ ባልካዛርን የሀገሪቱ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት አድርጎ ሰየመ። ፓርላማው ቀደም ብሎ ለአራት ወራት በተጠባባቂ ፕሬዝዳነትነት ያገለገሉትን ጆሴ ጄሪ በሙስና ምክንያት ከስልጣን ማንሳቱ ይታወሳል። አሁን የተመረጡት ፕሬዝዳንት ጆሴ ማሪያ ባልካዛር የፓርላማው አባል እንደሆኑ ተነግሯል በአስር ዓመት ውስጥ በፔሩ ስምንት ፕሬዝዳንቶች መፈራረቃቸውን ሮይተርስ ጽፏል። ሀገሪቱ ሚያዝያ ወር ላይ ፕሬዝደንቷን እና የፓርላማ አባላትን ምርጫ ለማካሄድ ቀጠሮ ይዛለች። #ብሪታንያ የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር በዲኤጎ ጋርሺያ የአየር ሃይል ሰፈር ዙሪያ የደረሱት ስምምነት ትልቅ ስህተት ያለበት ነው ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተቹ። ዲኤጎ ጋርሺያ
Feb 203 min read


ጥቅምት 27 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ፊሊፒንስ ፊሊፒንስን ሰሞኑን በመታት ከባድ አውሎ ነፋስ የሟቾቹ ብዛት ከ140 በላይ መድረሱ ተሰማ፡፡ አውሎ ነፋሱ በከባድ ጎርፍ እና በመሬት መንሸራተት ጭምር የታገዘ እንደነበር AFP አስታውሷል፡፡ በአደጋው ከሞቱት እና አካላዊ ጉዳት ከገጠማቸው ሌላ 127 ሰዎች ደግሞ እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም ተብሏል፡፡ ይህም የሟቾቹ ብዛት ከተጠቀሰውም በላይ ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት አሳድሯል፡፡ ሴቡ የተባለችዋ ግዛት ዋነኛዋ የአደጋው ሰለባ ነች፡፡ በግዛቲቱ የደረሰው ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ከዚህ ቀደም ከደረሱት ሁሉ በእጅጉ ከባድ ነበር ተብሏል፡፡ ጎርፉ መኪኖችን እና ትልልቅ ኮንቴይነሮችን ጭምር አንከብክቦ መጋለቡ ታውቋል፡፡ ለፊሊፒንሱ አውሎ ነፋስ ፣ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ የአየር ለውጡ በዋና ምክንያትነት እየቀረ
Nov 6, 20252 min read


ጥቅምት 3 2018 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ማሊ ምዕራብ አፍሪካዊቱ አገር ማሊ አሜሪካውያንም ወደኛ ለመምጣት ለቪዛ ሲያመለክቱ እስከ 10 ሺህ ዶላር የሚደርስ የዋስትና ገንዘብ እንዲያሲዙ ልጠይቅ ነው አለች፡፡ ቀደም ሲል አሜሪካ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ቪዛ የሚጠይቁ ከ5 እስከ 10 ሺህ ዶላር የዋስትና ገንዘብ እንዲያሲዙ የሚጠይቅ አሰራር ተግባራዊ እንደምታደርግ እወቁልኝ ካለች መሰንበቷን አናዶሉ አስታውሳል፡፡ አዲሱ አሰራሯን ከ10 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ተግባራዊ ማድረግ እንደምትጀምር ታውቋል፡፡ የማሊ መንግስት መግለጫም ለአዲሱ የአሜሪካ የቪዛ መመሪያ ምላሽ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ የማላዊ እና የዛምቢያ መንገደኞች የአሜሪካ ቪዛ ለማግኘት ለቃለ መጠይቅ ከመቅረባቸው አስቀድሞ ከ5 እስከ 15 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በዋስትና ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸው መረጃው አስታውሷል፡፡ #ካሜሮን ካሜሩናውያን ቀጣይ ፕሬዘ
Oct 13, 20252 min read


መስከረም 22 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ኒጀር_እና_ማሊ የኒጀር እና የማሊ ወታደራዊ መንግስታት በምክክር ላይ ናቸው ተባለ፡፡ የሁለቱ አገሮች ምክክር አስተናጋጅ ማሊ እንደሆነች አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ የኒጀሩ ወታደራዊ መንግስት መሪ ጄኔራል አብዱራሂማኔ...
Oct 2, 20252 min read


ታህሳስ 25፣2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ጋና የጋና መንግስት የሁሉም የአፍሪካ አገሮች ዜጎች ወደ አገሪቱ ያለ ቪዛ እንዲገቡ ፈቀደ፡፡ የአፍሪካ ሀገሮች ዜጎች ወደ ጋና ያለ ቪዛ እንዲገቡ መፈቀዱ የሀገሪቱን የንግድ እና የቱሪዝም ዘርፎች በእጅጉ...
Jan 3, 20252 min read


ነሐሴ 8፣2016 - ነሐሴ 8፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#አፍሪካ ኤም ፖክስ(Mpox) የተሰኘው የፈንጣጣ በሽታ በአፍሪካ አህጉር የህዝብ የጤና ስጋት መሆኑ ታወጀ፡፡ ወረርሽኙ አህጉራዊ የጤና ስጋት ነው ሲል ያወጀው የአፍሪካ የበሽታዎች ቁጥጥር እና መከላከል አካል...
Aug 14, 20242 min read


ሐምሌ 26፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ቶጎ በቶጎ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ተሾሙ፡፡ በፕሬዘዳንት ፋውሬ ንያሲምቤ በጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሾሙት ቪክቶሪ ቶሜጋ ዶግቢ እንደሆኑ አናዶሉ ፅፏል፡፡ በአዲሱ የአገሪቱ ህገ መንግስት መሰረት አገሪቱ ባለ ጠቅላይ...
Aug 2, 20242 min read


ሐምሌ 23፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ፍልስጤም የፍልስጤማውያኑ የጦር ድርጅት(ሐማስ) በጋዛ የተኩስ አቁም ለማድረግ የሚካሄደውን ድርድር በማወላከፍ የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁን ከሰሰ፡፡ ድርድሩ የሚካሄደው በአሜሪካ ተደግፎ በቀረበው...
Jul 30, 20241 min read


ሚያዝያ 21፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#የአለም_የምግብ_ፕሮግራም በተለያዩ የአለም ክፍሎች የተለያዩ ቀውሶች መነባበር የሰብአዊ የምግብ እርዳታ አቅርቦቱን በእጅጉ ፈታኝ እያደረገው ነው ተባለ፡፡ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት በመካከለኛው ምስራቅ...
Apr 29, 20242 min read


ሚያዝያ 11፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ፍልስጤም የፍልስጤም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሙሉ አባል አገር የመሆን ሕልም ተጨናገፈ፡፡ ፍልስጤምን የተባበሩት መንግስታት ሙሉ አባል ማድረጊያ የውሳኔ ሀሳብ ትናንት ለፀጥታው ምክር ቤት ቀርቦ እንደነበር አናዶሉ...
Apr 19, 20242 min read


ጥር 24፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#አሜሪካ የአሜሪካ መንግስት በሱዳን ከቀጠለው ጦርነት ጋር ግንኙነት አላቸው ባላቸው ሶስት የሱዳን ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ መጣሉ ተሰማ፡፡ ማዕቀቡ ከተጣለባቸው ኩባንያዎች ሁለቱ RSF ከተሰኘው ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ጋር...
Feb 2, 20242 min read


ጥር 7፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#እስራኤል እስራኤል ውስጥ በተሰረቀ መኪና በርካታ ሰዎችን ሆን ብለው በመግጨት ጉዳት አድርሰዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች መያዛቸው ተሰማ፡፡ በተጠርጣሪነት የተያዙት ግለሰቦች ፍልስጤማውያን እንደሆኑ አረብ ኒው...
Jan 16, 20241 min read


ታህሳስ 1፣2016 – የባህር ማዶ ወሬዎች
#ግብፅ ግብፃውያን ቀጣይ ፕሬዘዳንታቸውን ለመምረጥ ከትናንት አንስቶ ድምፅ እየሰጡ ነው፡፡ ድምፅ አሰጣጡ እስከ ነገ ድረስ እንደሚከናወን ኒው ዴይሊ ፅፏል፡፡ ፕሬዘዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲን ለመፎካከር ሶስት እጩዎች...
Dec 11, 20232 min read


ጥቅምት 13፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ፍልስጤም የፍልስጤማዊያኑ የጦር ድርጅት /ሐማስ/ ተጨማሪ 2 ሴት ታጋቾችን መልቀቁ ተሰማ፡፡ ሐማስ ቀደም ሲል አግቷቸው ከነበሩት መካከል አንዲትን አሜሪካዊት ከነሁለት ልጆቿ የለቀቀው ሰሞኑን ነው፡፡ ሐማስ ተጨማሪዎቹን...
Oct 24, 20232 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page

