top of page

ጥቅምት  3 2018  - የባህር ማዶ ወሬዎች

  • Oct 13, 2025
  • 2 min read


ምዕራብ አፍሪካዊቱ አገር ማሊ አሜሪካውያንም ወደኛ ለመምጣት ለቪዛ ሲያመለክቱ እስከ 10 ሺህ ዶላር የሚደርስ የዋስትና ገንዘብ እንዲያሲዙ ልጠይቅ ነው አለች፡፡


ቀደም ሲል አሜሪካ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ቪዛ የሚጠይቁ ከ5 እስከ 10 ሺህ ዶላር የዋስትና ገንዘብ እንዲያሲዙ የሚጠይቅ አሰራር ተግባራዊ እንደምታደርግ እወቁልኝ ካለች መሰንበቷን አናዶሉ አስታውሳል፡፡


አዲሱ አሰራሯን ከ10 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ተግባራዊ ማድረግ እንደምትጀምር ታውቋል፡፡


የማሊ መንግስት መግለጫም ለአዲሱ የአሜሪካ የቪዛ መመሪያ ምላሽ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡


የማላዊ እና የዛምቢያ መንገደኞች የአሜሪካ ቪዛ ለማግኘት ለቃለ መጠይቅ ከመቅረባቸው አስቀድሞ ከ5 እስከ 15 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በዋስትና ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸው መረጃው አስታውሷል፡፡



ካሜሩናውያን ቀጣይ ፕሬዘዳንታቸው ለመምረጥ ትናንት ድምፅ ሲሰጡ ዋሉ፡፡


አገሪቱን ላለፉት 43 ዓመታት የመሯት ፕሬዘዳንት ፖል ቢያ የአሁኑም ምርጫ እጩ ተፎካካሪ እንደሆኑ አልጀዚራ ፅፏል፡፡


የ92 አመቱ ፖል ቢያ ለፕሬዘዳንትንት ሲፎካከሩ የአሁኑ 8ኛቸው እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡

ፖል ቢያ በአለማችንም በአሁኑ ወቅት በእድሜ አረጋዊው መሪ ናቸው ይባላል፡፡


በአገሪቱ የአሁኑ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ የተካሄደው ለብዙዎቹ ካሜሩናውያን የኑሮ ውድነቱ ፈተናው እየከበደ በመጣበት ወቅት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡


ውጤቱን የአገሪቱ ህገ መንግስታዊ ምክር ቤት ከ2 ሳምንታት ባልበለጠ ጊዜ እወቁልኝ እንደሚል ታውቋል፡፡



በማዳጋስካር ከዋናው ጦር ሀይል ያፈነገጠ ነው የተባለ የጦር ክፍል የአገሪቱ ወታደሮች አጠቃላይ ትዕዛዝ መቀበል ያለባቸው ከእኔ ብቻ መሆን ይገባዋል ማለቱ ተሰማ፡፡


ህዝባዊ ተቃውሞ በርትቶበት የሰነበተው የፕሬዘዳንት አንድሬይ ራጆሊና አስተዳደር ህገወጥ እና በሀይል የታጀበ የስልጣን ቅሚያ እየተደረገብኝ ነው የሚል መግለጫ ማውጣቱን አልጀዚራ ፅፏል፡፡


ይሁንና የስልጣን ንጥቂያውን ሁኔታ በመግለጫው በዝርዝር አላብራራውም ተብሏል፡፡


ካፕሳት የተሰኘው አፈንጋጩ የጦር ክፍል አዛዦቹ የመንግስትን ትዕዛዝ እንዳያከብሩ ማስጠንቀቁ ተሰምቷል፡፡


የጦር ክፍሉ በፕሬዘዳንት አንድሬይ ራጆሊና አስተዳደር ላይ ተቃውሟቸውን ያበረቱትን ወጣቶች እጠብቃቸዋሁ ማለቱ ተጠቅሷል፡፡


የማዳጋስካሩ ፖለቲካዊ ቀውስ ከእለት ወደ እለት እየተባባሰ ነው፡፡


በኤሌክትሪክ እና በውሃ አገልግሎቶች መቆራረጥ ምክንያት የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከ3 ሳምንታት በላይ ማስቆጠሩን መረጃው አስታውሷል፡፡



የፍልስጤማውያኑ ታጣቂ ቡድን ሐማስ 7 እስራኤላዊያን ታጋቾችን ለአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ማስረከቡ ተሰማ፡፡


እስራኤል እና ሐማስ ቀደም ሲል በፈረሙት የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት ሐማስ በእጁ የሚገኙ 48 እስራኤላዊያን ታጋቾችን በሙሉ ማስረከብ እንደሚጠበቅበት አልጀዚራ ፅፏል፡፡


ከእስራኤላዊያኑ ታጋቾች መካከል 20ዎቹ በሕይወት እንዳሉ ይገመታል፡፡


ሐማስ በተለያዩ ምክንያቶች የሞቱ ታጋቾችን አስከሬንም እንደሚያስረክብ ይጠበቃል፡፡


እስራኤልም ከባድ ፍርደኞችን ጨምሮ 2 ሺህ ያህል ፍልስጤማውያን እስረኞችን ትፈታለች ተብሏል፡፡


ቀደም ሲል የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛው ጦርነት አብቅቷል ማለታቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Recent Posts

See All
የሐምሌ 23 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ግብፅ በግብፅ የሜዴትራኒያን የባህር ዳርቻ የነበረ የአሜሪካ የጋዝ ማጠራቀሚያ መርከብ በድሮን ተመታ ተባለ፡፡ ሁለት የደህንነት ምንጮች መርከቡ በድሮን እንደተመታ አረጋግጠውልኛል ሲል ሬውተርስ ፅፏል፡፡ መርከቡ በድሮን እንደተመታ በእሳት መያያዙ ታውቋል፡፡ ቃጠሎው ወደ ሌላ መርከብም ተጋብቶ ነበር ተብሏል፡፡ ኋላ ግን

 
 
 
የሐምሌ 22 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#አሜሪካ አሜሪካ እና ሳውዲ አረቢያ ኢራቅ ውስጥ በአፍቃሪ ኢራን ታጣቂዎች ይዞታ ላይ ድብደባ ፈፀሙ፡፡ ሰሞኑን ሳውዲ አረቢያ በኢራቅ የሚገኙ አፍቃሪ ኢራን ታጣቂዎች በድሮን ጥቃት አድርሰውብኛል ስትል እንደነበር አልጀዚራ አስታውሷል፡፡ ሳውዲ ጥቃቱን ከማውገዝ በተጨማሪ መበቀሌ አይቀርም በሚል ዝታ ነበር፡፡ በኢራቆቹ አ

 
 
 
የሐምሌ 21 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ጃፓን የጃፓን ደቡባዊ ምዕራብ ክፍል በርዕደ መሬት ተመታ፡፡ ርዕደ መሬቱ የደረሰው ኩማማቶ የተባለው የአገሪቱ ክፍል እንደሆነ ኒኪ እስያ ፅፏል፡፡ የመሬት ነውጡ የተቀሰቀሰው ከምድር በ10 ኪሎ ሜትር ጥልቀት መሆኑ ታውቋል፡፡ ነውጡ በርዕደ መሬት መለኪያ /ሬክተር ስኬል/ 7 ነጥብ 1 ሆኖ መመዝገቡ ታውቋል፡፡ ቀደም ሲ

 
 
 

1 Comment


Fara Pioky
Fara Pioky
Apr 29

 the satisfaction of making Geometry Dash a highly accurate guess is incredibly rewarding. It creates a sense of achievement that encourages players to keep improving their skills.

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page