top of page

ግንቦት 20/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች

  • May 28
  • 2 min read

የፍልስጤማውያኑ ታጣቂ ቡድን (ሐማስ) የወታደራዊ ክንፉ የበላይ ሞሐመድ አውዳ በእስራኤል ጥቃት መገደሉ እውነት ነው አለ፡፡


ሞሐመድ አውዳ የተገደለው እስራኤል በጋዛ ከተማ በፈፀመችው የአየር ጥቃት እንደሆነ TRT ዎርልድ ጽፏል፡፡



ከሐማሱ የወታደራዊ ክንፍ አዛዥ ጋር በጥቃቱ ባለቤቱ እና ሁለት ልጆቹ መገደላቸው ታውቋል፡፡


አውዳ ከሐማስ መስራቾች አንዱ እንደነበር በቡድኑ መግለጫ ተጠቅሷል፡፡


ሞሐመድ አውዳ በሐማስ ወታደራዊ ክንፍ የበላይነት የተሰየመው በቅርቡ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡


እስራኤል የጋዛ የጦር ዘመቻዋን ከጀመረች ወዲህ በርካታ ስመ ጥር የሐማስ ወታደራዊ አዛዦችን መግደሏን መረጃው አስታውሷል፡፡



ምዕራብ አፍሪካዊቱ ጋና ከደቡብ አፍሪካ ዜጎቿን ማስወጣት ጀመረች፡፡


በደቡብ አፍሪካ በውጭ ተወላጅ አፍሪካውያን ላይ ያነጣጠረው የአገሬው ሰዎች የጥላቻ ጥቃት እየተባባሰ መምጣቱን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡


ጥቃቱን በግላጭ ካወገዙት መካከል የጋና መንግስት አንዱ ነው፡፡


የጋና መንግስት ለጥቃት የተጋለጡ እና ወደ ትውልድ አገራቸው መመለስ የሚሹ ፈቃደኞች እንዲመዘገቡ ከጠየቀ ሰንብቷል፡፡


በጥሪው መሰረት 300 ያህል ጋናውያን ትናንት ከጆሃንስበርግ ኦሊበር ታምቦ ኤርፖርት ወደ አገራቸው እንዳመሩ ታውቋል፡፡


ከ800 በላይ ጋናውያን እና ትውልደ ጋናዎች ወደ አገራቸው ለመመለስ እንደተመዘገቡ መረጃው አስታውሷል፡፡



የአሜሪካ ጦር በኢራን ባንዳር አባስ ወታደራዊ መቆጣጠሪያ ላይ ድብደባ ፈፀምኩ አለ፡፡


የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ እዝ በባንዳር አባስ የፈፀመውን ድብደባ ራስን ለመከላከል የታለመ ነበር ማለቱን ቢቢሲ ፅፏል፡፡


ከድብደባው አስቀድሞ የኢራን ጦር የሰደዳቸውን አራት አጥቂ ሰው አልባ በራሪ አካላት (ድሮኖች) መትቼ ጥያለሁ ብሏል ማዕከላዊ እዙ፡፡


የኢራን መገናኛ ብዙሃን በባንዳር አባስ ከተማ ምስራቃዊ ክፍል ከፍተኛ ፍንዳታ መሰማቱን ዘግበዋል፡፡


የኢራን ሹሞች ጉዳዩን እናጣራለን እንዳሏቸው አውርተዋል፡፡


የአሜሪካ ጦር በኢራን ላይ በ3 ቀናት ውስጥ 2ኛው የሆነውን ድብደባ የፈፀመው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገው ድርድር አላረካንም ማለታቸውን ተከትሎ ነው፡፡


የኢራን የኒኩሊር መርሐ ግብር እና የሆርሙዝ የባህር መተላፊያ ወሽመጥ ጉዳይ የሁለቱ አገሮች ከፍተኛ መወዛገቢያዎች እንደሆኑ ይነገራል፡፡


ለጦርነቱ ማስቆሚያ የሚካሄደው ድርድር ወሰድ መለስ የሚታይበት ሆኗል፡፡


የኢራን ሹሞች ለቀዳሚው ድብደባም ለአሜሪካ የእጇን እንሰጣታለን ብለው ነበር፡፡


አዲሱ ውጥረት የተኩስ አቁሙን ፉርሽ እንዳያደርገው ተሰግቷል ተብሏል፡፡



የአለም የጤና ድርጅት የበላይ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በኮንጎ ኪንሻሣ ምስራቃዊ ክፍል የቀጠለው ጦርነት በአገሪቱ የተከሰተውን የኢቦላ ወረርሽኝ ለመገደብ እና ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ አዳጋች እንዳደረገው ተናገሩ፡፡


በኮንጎ ኪንሻሣ ኢቱሪ ግዛት ኢቦላ በወረርሽኝ ደረጃ ከተቀሰቀሰ መሰንበቱን ቢቢሲ አስታውሷል፡፡


ወረርሽኙ እስከ ትናንት ከ220 ያላነሱ ሰዎችን መግደሉ ተጠቅሷል፡፡


በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ብዛትም እየጨመረ ነው ተብሏል፡፡


ኢቦላ በአማጺያን ተይዘው ወደሚገኙ ስፍራዎችም በመዝለቁ የመከላከሉን ጥረት አዳጋች ማድረጉ ተሰምቷል፡፡


በዚህም ምክንያት የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የወረርሽኙን መዛመት ለመገደብ የሚከናወኑ ተግባራትን ለማገዝ ተፋላሚዎቹ የተሟላ የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ተማፅነዋል፡፡


በኮንጎ ኪንሻሣ በ50 ዓመታት ጊዜ ኢቦላ በወረርሽኝ ደረጃ ሲቀሰቀስ የአሁኑ ለ17ኛ ጊዜ ነው ተብሏል፡፡



የሐንጋሪ ፓርላማ አገሪቱ በአለም አቀፉ የወንጀለች ችሎት አገሪቱ /ICC/ አባልነቷ እንድትፀና የሚያደርግ ሕግ ማፅደቁ ተሰማ፡፡


በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን ይመራ የነበረው መንግስት አገሪቱን ከችሎቱ አባልተነቷ ለማስወጣት ወስኖ እንደነበር አናዶሉ አስታውሷል፡፡


ከጥቂት ወራት በፊት በተካሄደው የሐንጋ የፓርላማ ምርጫ የነቪክቶር ኦርባን የፖለቲካ ወገኖች ሽንፈት ገጥሟቸዋል፡፡


ይህም ኦርባን ለ16 ዓመት ይዘውት የነበረውን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን አሳጥቷቸዋል፡፡


የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፒተር ማግያ አስተዳደር የኦርባን መንግስት ከ ICC አባልነት ለመልቀቅ ደርሶት የነበረውን ውሳኔ መቀልበሱ ታውቋል፡፡


ውሳኔው ባይቀለበስ ኖሮ ሐንጋሪ በመጪው ወር ከአለም አቀፉ ችሎት አባልነቷ ትለቅ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ

2 Comments


top game
top game
Jun 02

The best thing about eggy car is that it doesn't require a long tutorial. You can jump right in and enjoy the challenge from the first minute.

Like

yaqian zhang
yaqian zhang
Jun 02

If you like physics-based driving challenges, Drive Mad is worth checking out. The balance between frustration and achievement feels just right.


Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page