top of page

ሚያዝያ  1፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች

  • Apr 9, 2024
  • 2 min read

 

የኒጀር ወታደራዊ መንግስት አሜሪካን በቃ ወታደሮችሽን ከሀገሬ አስወጪልኝ አለ፡፡

 

የኒጀር ወታደራዊ መንግስት ለአሜሪካ መሰል ጥያቄ ሲያቀርብ ወር ባልሞላ ጊዜ  የትናንቱ 2ኛው እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡

 

የምዕራብ አፍሪካዊቱ አገር መንግስት ቀደም ሲል የሁለቱን አገሮች የመከላከያ ትብብር ስምምነት አያሻኝም ማለቱን ዘገባው አስታውሷል፡፡

 

በጊዜውም የወታደራዊ መንግስት መሪው የአሜሪካ ወታደሮች ኒጀርን ለቅቀው እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

 

በአሁኑ ወቅት አሜሪካ በኒጀር ከ600 በላይ ወታደሮች እንዳሏት ይነገራል፡፡

 

የኒጀር ወታደራዊ መንግስት ቀደምሲል በዚያ የነበሩ የፈረንሳይ ወታደሮችን በሙሉ አስወጥቷል፡፡

 



 

የሩሲያ ወታደሮች ከአቭዲቭካ በስተምዕራብ ይዞታቸውን እያስፋፉ ነው ተባለ፡፡

 

ሩሲያውኑ በዳኔስክ ግዛት የምትገነውን አብዲቭካን የያዟት ከወር ተኩል በፊት እንደሆነ ኒውስ ዊክ አስታውሷል፡፡

 

በአሁኑ ወቅትም የሩሲያ ወታደሮች ከአብዲቭካ በስተምዕራብ ያሉ ስፍራዎችን እየተቆጣጠሩ መሆኑ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

 

የሩሲያ ጦር ከወር ተኩል በፊት አቭዲቭካን እንደተቆጣጠረ በስተምዕራብ አቅጣጫ ለመግፋት በጥሩ የጦር ቁመና ላይ እገኛለሁ ብሎ ነበር፡፡

 

የዩክሬይን ወታደራዊ ሹሞችም የሩሲያ ጦር አዲስ ጥቃት ሊከፍትብን ነው ብለው እንደነበር በዘገባው ለትውስታ ሰፍሯል፡፡

 

ስለ አዲሱ የሩሲያ ጦር የተስፋፋ ይዞታ ከዩክሬይን ሹሞች በኩል የተሰማ አስተያየት የለም፡፡

 

 

የብሪታንያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን እና የፈረንሳይ አቻቸው ስቴፋን ሴዢርኒ ለዩክሬይን ያልተቆጠበ ድጋፍ እናደርግላታለን አሉ፡፡

 

ዩክሬይን ከሩሲያ ጋር ስትዋጋ ከ2 አመታት በላይ ሆኗታል፡፡

 

ምዕራባዊያን እና አጋሮቻቸው ዩክሬይንን በጦር መሳሪያ እና በወታደራዊ መረጃ እየደገፏት እንደሆነ አናዶሉ ፅፏል፡፡

 

የፈረንሳይ እና የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዩክሬይን የሁለቱ አገሮች ድጋፍ እንደማይቋረጥባት በጋራ መግለጫቸው እወቁልን ብለዋል፡፡

 

ዩክሬይን በጦርነቱ የግዴታ ማሸነፍ አለባት ብለዋል፡፡

 

ዩክሬይን በጦርነቱ ከተሸነፈች አገሮቻቸው እንደተሸነፉ እንደሚቆጥሩት እወቁልን ብለዋል፡፡

 

ሩሲያ በፊናዋ በጦርነቱ እያሸነፍኩ ነው ባይ እንደሆነች በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

 

 

በቻዷ ርዕሰ ከተማ እንጃሚና የአገሪቱ ወታደራዊ መሪ ጄኔራል ማኅማት ኢድሪስ ዴቢ የምረጡኝ ቅስቀሳ ሰሌዳ እየተሰቀለ ነው ተባለ፡፡

 

የማኅማት ኢድሪስ ዴቢ ሰሌዳ መሰቀል የያዘው የምረጡን ዘመቻው ሊጀመር ከሳምንት በላይ እየቀረው መሆኑን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡

 

ተቃዋሚ የፖለቲካ ማህበራት የወታደራዊ መሪው ምስል እና ፖለቲካዊ መልዕክት ከጊዜው አስቀድሞ መለጠፍ እና መሰቀሉን የህግ ጥሰት ነው ብለውታል፡፡

 

ዴቢ ከጊዜው የቀደመ ቅስቀሳቸውን እንዲያቆሙ ተቃዋሚዎቹ ጠይቀዋል፡፡

 

ቻድ በምርጫ ጥሩ ስም እንደሌላት በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

 

ማሐማት ኢድሪስ ዴቢ በአማጺያን ጥቃት ከ3 አመታት በፊት በተገደሉት አባታቸው ወንበር ህገ መንግስታዊ ባልሆነ መንገድ ስልጣን እንደጨበጡ ዘገባው አስታውሷል፡፡

 

 

የኔነህ ከበደ

 

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

Telegram:  @ShegerFMRadio102_1

 

 

 

Recent Posts

See All
የሐምሌ 17 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ብሪታንያ የብሪታንያ መንግስት በኬንያ ላካሂድ የነበረውን አመታዊ የጦር ልምምድን ትቼዋለሁ አለ፡፡ የብሪታንያ ሰራዊት አመታዊ የኬንያ የጦር ልምምዱን የተወው ከምስራቅ አፍሪካዊቱ አገር መንግስት ፈቃድ ባለማግኘቱ ነው መባሉን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ የብሪታንያ ጦር ከዚህ ቀደም በኬንያ በየአመቱ በመደበኛነት የጦር ልም

 
 
 
የሐምሌ 16 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ሊቢያ በሊቢያ የተለያዩ የፖለቲካ ማህበራት አገሪቱ ወደ አንድነቷ እንድትመለስ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የፖለቲካ ማህበራቱ በጋራ የህውደት ጥሪውን ያቀረቡት የሊቢያን የወደፊት እጣ ፈንታ በተመለከተ ምክክር ባደረጉበት ወቅት እንደሆነ TRT አፍሪካ ፅፏል፡፡ በሊቢያ የቀድሞው መሪ የኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ አስተዳደር ከ15 አመታት

 
 
 
የሐምሌ 15 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ሞሪታንያ በሞሪታንያ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ በደረሰ የባህር አደጋ 144 ጥገኝነት ፈላጊዎቹ ሳይሞቱ አልቀረም ተባለ፡፡ የአደጋው ሟቾች መነሻዋን ከጋምቢያ በማድረግ ወደ ስፔን በማምራት ላይ በነበረች ጀልባ የተሳፈሩ ጥገኝነት ፈላጊዎች እንደሆኑ አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ በጀልባዋ ተሳፍረው የነበሩት በሙሉ ከተለያዩ የአፍ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page