top of page
በሽብር ወንጀል በተጠረጠሩት የኢሕአፓ አመራሮች እና አባላት ላይ ተጨማሪ 10 ቀን የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ፡፡
ነሐሴ 11 2018 በሽብር ወንጀል በተጠረጠሩት የኢሕአፓ አመራሮች እና አባላት ላይ ተጨማሪ 10 ቀን የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ፡፡ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) አመራሮችና አባላት ላይ መርማሪ ፖሊስ ያቀረበውን ጥያቄ በመቀበል፣ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ የ10 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቀደ። በዛሬው ዕለት ረፋድ 4:00 ሰዓት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የቀረቡት የኢሕአፓ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይስሐቅ ወልዳይ፣ የፓርቲው አባል አቶ አበበ አካሉ እና ጠበቃ አበራ ንጉሥ ናቸው። ቀደም ሲል በነበረው ችሎት ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ያደረጉትን ንግግር የድምፅ ቅጂ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱም ቅጂውን ካዳመጠ በኋላ «ለጥርጣሬ መነሻ የሚሆን
8 minutes ago
ስርዓተ ምግብ ላይ በመስራት መቀንጨርን ለመቀነስ፤ ከተቻለ ወደ ዜሮ ለማውረድ እየተሰራ ቢሆንም አፈጻጸሙ ግን ጥያቄ የሚያስነሳ ነው ይላሉ የስነምግብ ባለሙያዎች፡፡
ነሐሴ 11 2018 ስርዓተ ምግብ ላይ በመስራት መቀንጨርን ለመቀነስ፤ ከተቻለ ወደ ዜሮ ለማውረድ እየተሰራ ቢሆንም አፈጻጸሙ ግን ጥያቄ የሚያስነሳ ነው ይላሉ የስነምግብ ባለሙያዎች፡፡ በቀበሌ ደረጃ መቀንጨርን ለመከላከል የሚመደቡ ባለሙያዎች የስነ ምግብ ዕውቀት የሌላቸው መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ ደግሞ በሚፈለገዉልክ ለዉጥ ሊያመጣ አይችልም ሲሉ ያነጋገርናቸዉ ባለሞያዎች ያስረዳሉ:: ዶ/ር ታደሰ ዘርፉ በአለማቀፉ የምግብ ምርምር ፖሊሲ ተመራማሪ ሳይንቲስት ናቸው ፡፡ የሚደረጉ የጥናትና ምርምር ውጤቶችንም ሆነ የሚታቀዱ እቅዶችን ተግባራዊ ለማድረግ በቂ እውቀት ያላቸውና የስነ ምግብ ባለሙያዎችን መመደብ አልተቻለም ሲሉ ነግረውናል፡፡ አሁን በኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ባለሙያዎች ቁጥር አነስተኛ ነው ወይ ስንል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምግብና ስነ -ምግብ
13 minutes ago


በ769 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ አራት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ተመረቁ።
ነሐሴ 11 2018 በ769 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ አራት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ተመረቁ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ ርቀው ለሚገኙ የገጠር አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋፋት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሐዌ ጉዲና ወረዳ የተገነቡ አራት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን አስመርቋል። ፕሮጀክቶቹ የተገነቡት በቶርበን፣ ባቴ፣ ሐሎ ጎባ እና ሐሮ ኦባ ቀበሌዎች ሲሆን፣ በአጠቃላይ 769 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው ናቸው፡፡ አራቱ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች በድምሩ 900 ኪሎ ዋት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አላቸው ተብሏል። በፕሮጀክቱ 7.74 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር፣ 30.29 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም 10 የማከፋፈያ ትራንስፎርመሮች ተተክለው ሥራ ጀምረዋል። ማህበ
2 hours ago
በመጪው ረቡዕ ለስምንቱም አጀንዳዎች የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች በ4 ሺህ ጉባዔተኞች እንደሚጸድቁ የምክክር ኮሚሽን ተናገረ፡፡
ነሐሴ 11 2018 በመጪው ረቡዕ ለስምንቱም አጀንዳዎች የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች በ4 ሺህ ጉባዔተኞች እንደሚጸድቁ የምክክር ኮሚሽን ተናገረ፡፡ በአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ውይይት ሲካሄድባቸው ለቆዩ አጀንዳዎች የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች በመጪው ረቡዕ እንደሚጸድቁ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ ተናግረዋል፡፡ ምክትል ኮሚሽነሯ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተመካካሪዎች ከዛሬ ከሰዓት ጀምሮ በራሳቸው እና በሌሎች ቡድኖች ምክረ ሀሳብ ላይ መወያየት እንደሚጀምሩ ተናግረዋል፡፡ እንደ ኮሚሽነሯ ማብራሪያ ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ ተመካካሪ ቡድኖች የመረጧቸው ተወካዮች በቀረቡ ምክረ ሀሳቦች ላይ ድግግሞሽ እና ተቃርኖ እንዳይኖር የማጠናከር እና የማጣጣም ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ ያጣጣሟቸውን ስራዎች ደግሞ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለ
2 hours ago
ክረምት በመጣ ቁጥር የአዲስ አበባ የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች በዝናብ ተሞልተው በመገንፈላቸው ለእግረኞችም ይሁን ለተሸከርካሪዎች ወዲህ ወዲያ ሲያስቸግሩ ይታያል፡፡
ነሐሴ 11 2018 ክረምት በመጣ ቁጥር የአዲስ አበባ የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች በዝናብ ተሞልተው በመገንፈላቸው ለእግረኞችም ይሁን ለተሸከርካሪዎች ወዲህ ወዲያ ሲያስቸግሩ ይታያል፡፡ በተለይም እነዚህ መስመሮች በቆሻሻና ሌሎች ቁሶች በመደፈናቸው ውሃውን በአግባቡ ማስወጣት አቅቷቸው በመንገዶች ላይ የሚፈጠረው የውሃ መተኛትና ጎርፍ የሰዎችን እንቅስቃሴ ከማወኩ ባለፈ ለአደጋ ተጋላጭነትንም እየጨመረ መምጣቱ በከተማዋ የሚታይ ችግር ሆኗል፡፡ ለመሆኑ በተመሳሳይ ጊዜ አመት እየጠበቁ የሚገነፍሉት የከተማ የፍሳሽ ማስተላለፊያዎች ጥገናና ጥንቃቄ በሌላ በኩል ክረምቱን ተከትሎ የሚበዛውን የጎርፍ አደጋ ለመቀነስ ምን ተሰርቷል? ችግሩስ ለምን ከዓመት አመት ዘለቀ ስንል የሚመለከታቸውን ጠይቀናል፡፡ የከተማዋን መንገዶች ከጎርፍ ስጋት ለመቀነስ ሲሰራ ቢቆይም በተለያዩ ሰ
3 hours ago












bottom of page
_edited.jpg)






