top of page


ግንቦት 20/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች
#ፍልስጤም የፍልስጤማውያኑ ታጣቂ ቡድን (ሐማስ) የወታደራዊ ክንፉ የበላይ ሞሐመድ አውዳ በእስራኤል ጥቃት መገደሉ እውነት ነው አለ፡፡ ሞሐመድ አውዳ የተገደለው እስራኤል በጋዛ ከተማ በፈፀመችው የአየር ጥቃት እንደሆነ TRT ዎርልድ ጽፏል፡፡ ከሐማሱ የወታደራዊ ክንፍ አዛዥ ጋር በጥቃቱ ባለቤቱ እና ሁለት ልጆቹ መገደላቸው ታውቋል፡፡ አውዳ ከሐማስ መስራቾች አንዱ እንደነበር በቡድኑ መግለጫ ተጠቅሷል፡፡ ሞሐመድ አውዳ በሐማስ ወታደራዊ ክንፍ የበላይነት የተሰየመው በቅርቡ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡ እስራኤል የጋዛ የጦር ዘመቻዋን ከጀመረች ወዲህ በርካታ ስመ ጥር የሐማስ ወታደራዊ አዛዦችን መግደሏን መረጃው አስታውሷል፡፡ #ጋና ምዕራብ አፍሪካዊቱ ጋና ከደቡብ አፍሪካ ዜጎቿን ማስወጣት ጀመረች፡፡ በደቡብ አፍሪካ በውጭ ተወላጅ አፍሪካውያን ላይ ያነጣጠረው
May 282 min read


ህዳር 9 2018 -የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አገራቸው ለሳውዲ አረቢያ ዘመን አፈራሾቹን F 35 የጦር ጄቶች እንደምትሸጥ ፍንጭ ሰጡ፡፡ ቀደም ሲል አሜሪካ F 35 የጦር ጄቶች በአረብ አገሮች እጅ እንዲገቡ ፍላጎት እንዳልነበራት አልጀዚራ ፅፏል፡፡ አሁን ግን ትራምፕ ለሳውዲ F 35 የጦር ጄቶችን እንሸጥላታለን ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ሳውዲዎች ታላቅ አጋሮቻችን ናቸው ይሄንንም እናደርገዋለን ብለዋል ትራምፕ፡፡ ትራምፕ የአብርሃም ስምምነቶች በሚሰኘው ማዕቀፍ ሳውዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንድትመሰርትላቸው ይሻሉ ተብሏል፡፡ ሳውዲ አረቢያ ግን ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከመመስረቴ አስቀድሞ የፍልስጤማውያን ነፃ መንግስት በሚቋቋምበት መላ አስተማማኝ ዋስትና ማግኘት እሻለሁ እያለች ነው፡፡ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሳውዲው
Nov 18, 20252 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page

