top of page

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ "ጉዞ ወደ FIFA የዓለም ዋንጫ 2026"በሚል ሲያካሂድ በነበረው የሽልማት መርሐ ግብር አሸናፊ የሆኑትን ሁለት እድለኞች ይፋ አደረገ።

  • 8 hours ago
  • 1 min read

ሚያዝያ 17/2018


የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ "ጉዞ ወደ FIFA የዓለም ዋንጫ 2026"በሚል ሲያካሂድ በነበረው የሽልማት መርሐ ግብር አሸናፊ የሆኑትን ሁለት እድለኞች ይፋ አደረገ።


ባንኩ ከቪዛ ካርድ ጋር በመሆን የቪዛ ካርዶቹን ለሚጠቀሙ ደንበኞቹ በሰሜን አሜሪካ ለሚካሄደው የዘንድሮ የአለም ዋንጫ ሁለት ባለዕድለኞች ጉዞ ሙሉ ወጪያቸውን እንደሚሸፍን መናገሩ ይታወሳል።



ሁለቱ አሸናፊዎችን ለማወቅ መርሃግብሩ ሲካሄድ የቆየው ከመጋቢት 12 እስከ ሚያዚያ 16/2018 ድረስ ነው።


ዛሬ በወጣው ሽልማት ተሳታፊ ለመሆን ባንኩ በቅርቡ ወደ ሥራ ያስገባቸው ሶስት የካርድ አገልግሎቶች፣ በሀገር ውስጥ POS ማሽኖች ላይ ከብር 200 ባላይ ከፍያዎች የፈጸሙ፣ በባንኩ ATM ብር 1000 እና ከዛ በላይ ገንዘብ ያስገቡ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከ20 ዶላር በላይ ክፍያ የፈጸሙ ደንበኞችን በዕጩነት አቅርቦ በዋናው መሥሪያ ቤት ባካሄደው የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት ሁለት ዕድለኞችን ለይቷል።


በዚህም ነፃነት አሰፋ እና አልዓዛር ንጉሱ የተባሉ ደንበኞች እጣው ወጥቶላቸዋል።


በተለያየ ምክንያት እጣ የወጣላቸው ሰዎች ጉዟቸው ባይሳካ በሚል ሌሎች ሁለት እጣ ወጥቶላቸዋል።


የዚህ ሽልማት ባለ እድለኞች ተጨማሪ አንድ አንድ ሰው ይዘው ወደ አለም ዋንጫው ይጓዛሉ፣የቪዛ ጉዳያቸውን፣ሙሉ ወጪያቸውን የሚጨርስላቸውም ባንኩ መሆኑ ተጠቅሷል።


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page