top of page

ከወረቀት አሰራር፤ ከፊት ለፊት ተገናኝቶ ከመስራት ያልተላቀቀው የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ዘርፍ

  • 10 hours ago
  • 1 min read

ሚያዝያ 17/2018


ከወረቀት አሰራር፤ ከፊት ለፊት ተገናኝቶ ከመስራት ያልተላቀቀው የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ዘርፍ የሚሰጠውን አገልግሎት ወደ ዲጅታላይዜሽን አለመቀየሩ ቋሚ ተገልጋይ ደንበኞቹን እያሳጣው ነው ተባለ፡፡


ቴክኖሎጅን ታግዞ አገልግሎት መስጠት የማይችል ከሆነ ዘፉር ችግር ላይ መውደቁ እንደማይቀር የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡


ባለሙያዎቹ ይህንን ያሉት በኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ዘርፍ ዲጅታላይዜሽን እና የደንበኛ ታማኝነት ያላቸው ግንኙነት በሚል በቀረበ ጥናት ላይ ነው፡፡



የኢንሹራንስ ዘርፉ እስካሁን ለደንበኞቹ አገልግሎት ለመስጠትም ሆነ ሌሎች ስራዎቹን የሚከውነው ቴክኖሎጅን ተጠቅሞ ባለመሆኑ መስራት በሚገባው ልክ እንዳይሰራ እና ወደ ኋላ እንዲቀር አድርጎት ቆይቷል ተብሏል፡፡


ነገር ግን ኢትዮጵያ እሰራችነበት ያለው የ2030 ዲጅታላይዜሽን እቅድ ዘርፉን አሁን ካለበት አሰራር ለማስወጣት መንገድ ይጠርግለታል ሲሉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡


በአለም አቀፍ ደረጃ የኢንሹራንስ ዘርፉ ከነበረበት ቅርፅ በከፍተኛ ፍጥነት እየተቀየረ መጥቷል ያሉት ጥናቱን ያቀረቡት የኒያላ ኢንሹራንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ያሬድ ሞላ (ዶ/ር) ዘርፉ ላይ የሚገቡት አዳዲስ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በተሻለ መንገድ አገልግሎቱን በመስጠት ነባሮቹ ከገበያው እየተገፉ የሚወጡበት አጋጣሚ በስፋት እየተስተዋለ ነው ብለዋል፡፡


ለዚህ ደግሞ መፍትሄው ዘርፉን በዲጂታላይዜሽን ማበርታት እና የደንበኞችን ታማኝነት ማቆየት ላይ በርትቶ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ያስረዳሉ፡፡


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ……


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page