top of page


የኮሎምቢያው ፕሬዘዳንት ጉስታቮ ፔትሮ የአሜሪካ ጦር ጥቃት ያሰኛጋል አሉ፡፡
ጥር 1/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ኮሎምቢያ የኮሎምቢያው ፕሬዘዳንት ጉስታቮ ፔትሮ የአሜሪካ ጦር ጥቃት ያሰኛጋል አሉ፡፡ ጉስታቮ ፔትሮ በአሜሪካ የጦር ጣልቃ ገብነት ስጋት ገብቶኛል ያሉት ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት አሜሪካ በቬኔዙዌላ ላይ ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ የአገሪቱን ፕሬዘዳንት ኒኮላስ ማዱሮን አሳግታ ወደ ኒውዮርክ ማስወሰዷ ይታወቃል፡፡ ከዚያ ወዲህ በርካታ አገሮች በአሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ክፉኛ ስጋት እንደገባቸው ይነገራል፡፡ በአሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ ስጋት ገብቶኛል የሚሉት የኮሎምቢያው ፕሬዘዳንት ጉስታቮ ፔትሮ የዋይት ሐውስን አስተዳደር በግላጭ በመንቀር ይታወቃሉ፡፡ ትራምፕ እንደ ቬኔዙዌላ ሁሉ በኮሎምቢያም ላይ ሲዝቱ መቆየታቸው መረጃው አስታውሷል፡፡ #ሶማሊያ የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ሹሞቹ
Jan 92 min read


ጥቅምት 11 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ፈረንሳይ የፈረንሳይ ሹሞች እጅግ ውድ የአገራችንን ቅርሶች ማስጠበቅ ተስኖናል ሲሉ በፀፀት ተናገሩ፡፡ የሹሞቹ አስተያየት የተሰማው በርዕሰ ከተማዋ ፓሪስ ከሚገኘው የሉቨር ቤተ መዘክር ውድ ጌጣ ጌጦች ከተሰረቁ በኋላ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ጌጣ ጌጦቹ የአገሪቱ ቅርሶችም በመሆናቸው በዋጋ እንደማይታመኑ እየተነገረ ነው፡፡ ከተዘረፉት ቅርሶች መካከል የፈረንሳዩ ንጉሰ ነገስት ናፖሊዮን በናፖርት ለባለቤቱ አበርክቶለት የነበረ በአልማዝ የተንቆጠቆጠ ሐብልም ይገኝበታል ተብሏል፡፡ ዘራፊዎቹ ላይ በፍጥነት ካልተደረሰባቸው ቅርሶቹን በማወላለቅ በትንሽ በትንሹ ወደ ውጭ አገራት ሊያሸሿቸው ይችላሉ የሚል ስጋት አሳድሯል፡፡ የፓሪሱ ዘረፋ በመሰል ቤተ መዘክሮች የደህንነት ጥበቃው በእጅጉ እንዲጠናከር የማንቂያ ደወል ሆኗል ተብሏል፡፡ የቤተ መዘክሩ የቅርሶች ዘረፋ በአገሪቱ
Oct 21, 20252 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page








