top of page

የካቲት 15፣2015 - የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን እንድረዳቸው እርዱኝ አለ



የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን እንድረዳቸው እርዱኝ አለ፡፡


ኮሚሽኑ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን ለመርዳት የ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር የተማፅኖ ጥያቄ ማቅረቡን አናዶሉ ፅፏል፡፡


በአቅራቢያው አገሮች 2 ነጥበ 2 ሚሊዮን ስደተኞች እንደሚኖሩ ዘገባው አስታውሷል፡፡


ኮሚሽኑ ስደተኞቹን ለማኖር የእርዳታ ገንዘቡ በእጅጉ አስፈላጊ ነው ማለቱ ተሰምቷል፡፡


ከደቡብ ሱዳን ስደተኞች 80 በመቶዎቹ በቀጠናው ይገኛሉ ተብሏል፡፡


አገሪቱ ለበርካታ አመታት ግጭት ውስጥ ቆይታለች፡፡


አሁንም ድረስ ወደ ሙሉ መረጋጋት መመለስ እንዳልቻለች ዘገባው አስታውሷል፡፡



የኔነህ ከበደ





ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

bottom of page