top of page

የአለማችን የሙቀት መጠን በእጅጉ እየጨመረ እንደሚመጣ የሳይንስ ሊቃውንት አስጠነቀቁ፡፡

  • 3 hours ago
  • 2 min read

ግንቦት 26/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች



የአለማችን የሙቀት መጠን በእጅጉ እየጨመረ እንደሚመጣ የሳይንስ ሊቃውንት አስጠነቀቁ፡፡


ከፍተኛ የሙቀት መጠን በብዙ የአለማችን ክፍሎች እንደሚመዘገብ አለም አቀፉ የአየር ሁኔታ ተከታታይ መስሪያ ቤት ማስጠንቀቁን ቢቢሲ ፅፏል፡፡

ኤል ኒኖ የተሰኘው የአየር ለውጥ ክስተት የከፍተኛ ሙቀት ጭማሪው ምክንያት መሆኑ ታውቋል፡፡


ከወዲሁም የሙቀት መጠን ጭማሪው መከሰቱን መረጃው አስታውሷል፡፡


ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ደግሞ የሙቀት መጠን ጭማሪው እየተጠናከረ ይመጣል ተብላል፡፡


የሙቀት መጠን ጭማሪው ደረጃ ሊቃውንቱን ከወዲሁ በእጅጉ እያሳሰበ መሆኑ ተሰምቷል፡፡


የአየር ለውጡን ተፅዕኖ ለመገደብ ሲወተወት ቢቆይም ችግሩ ከእርምጃው እየገዘፈ መምጣቱ ይነገራል፡፡



የአሜሪካ ጦር በኢራን ኬሽም ደሴት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈፅሜያለሁ አለ፡፡


የጦሩ ማዕከላዊ ወታደራዊ ዕዝ በኢራን ኬሽም ደሴት ፈፀምኩት ያለውን ድብደባ ራስን የመከላከል እርምጃ ሲል እንደጠራው አልጀዚራ ፅፏል፡፡


እንደተባለው ከሆነ የአሜሪካ ጦር ወደ እርምጃው የገባው የኢራን አብዮታዊ ዘብ የአሜሪካ አጋሮች ወደሆኑት ኩዌት እና ባሕሬን የድሮን እና የሚሳየል ጥቃቶችን ከሰነዘረ በኋላ ነው፡፡


ሁለቱ አገሮች ከአሜሪካ ታላላቅ የጦር ሰፈሮች መገኛዎች መካከል እንደሆኑ ይታወቃል፡፡


የአሜሪካ ጦር የኢራንን የጥቃት ውጥን አክሽፌባታለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡


በሰውም ሆነ በጦር ተቋሞቼ ላይ የደረሰ አንዳችም ጉዳት የለም ብሏል፡፡


በአፀፋ እርምጃው በኬሽም ደሴት የሚገኝን የኢራን የምድር መቆጣጠሪያ ጣቢያን መትቻለሁ ማለቱ ተጠቅሷል፡፡


ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ የኢራኑ የተኩስ አቁም መጣስ መደጋገሙን መረጃው አስታውሷል፡፡



በኬንያ በቅርቡ የአንድ የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ ሆን ብለው ቃጠሎ አስነስተዋል የተባሉ 9 ሴት ተማሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡


ወንጀሉ የተፈፀመው ከርዕሰ ከተማዋ ናይሮቢ በስተሰሜን ምዕራብ በ120 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንደሆነ አፍሪካ ኒውስ አስታውሷል፡፡


በቃጠሎው የ16 ሴት ተማሪዎች ህይወት አልፏል፡፡


79 ተማሪዎች ደግሞ የተለያየ ደረጃ አካላዊ ጉዳይ ገጥሟቸዋል፡፡


ሆን ብለው ቃጠሎውን ቀስቅሰዋል የተባሉት ተማሪዎች በፖሊስ ተይዘው ይገኛሉ ተብሏል፡፡


ወንጀሉን ፈፅመዋል ከተባሉት መካከል 6ቱ ድርጊቱን መፈማቸው የሚያሳይ የደህንነት መጠባበቂያ CCTV ምስል መገኘቱን መረጃው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page