የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የምሰጠው የአየር ትንበያ ትክክለኛነት እስከ 90 በመቶ እየደረሰ ነው አለ።
- 5 minutes ago
- 1 min read
ግንቦት 21/2018
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የምሰጠው የአየር ትንበያ ትክክለኛነት እስከ 90 በመቶ እየደረሰ ነው አለ።
እንደ ውሃና ኢነርጂ እንዲሁም ግብርና ሚኒስቴር ያሉ ተቋማትም ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ መልኩ የትንበያ መረጃውን መሰረት አድርገው ስራዎችን እየሰሩ እንደሚገኙ ነግረናል።
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በተለያዩ ወቅቶች የሚኖረውን የአየር ሁኔታ አዝማሚያ በተመለከተ ትንበያዎችን እና ቅድመ ማስጠንቀቂያዎችን ይሰጣል።
ኢንስቲትዩቱ እነዚህን ትንበያዎችን እና ማስጠንቀቂያዎች የሚሰጠው በተለያዩ አካባቢዎች ካሉት የአየር ሁኔታ መመዝገበያ ጣቢያዎች፤ከሚያሰባስበው መረጃ እንደሆነ የኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሳምነው ተሾመ ተናግረዋል።
መረጃዎቹን በመጠቀም የሚሰጠው ትንበያ ትክክለኛነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷልም ብለዋል።

ለአብነትም በዘንድሮው የበልግ ወቅት የሚኖረውን የአየር ሁኔታ በተመለከተ የሰጠው ትንበያ ከሞላ ጎደል እንደተባለው ሆኖ መገኘቱን ጠቅሰዋል።
ኢንስቲትዩቱ የረጅም ጊዜ እና የአጭር ጊዜ ትንበያዎችን እንደሚሰጥ የተናገሩት ዶክተር አሣምነው የአጭር ጊዜ ትንበያዎች ትክክለኛነት የበለጠ እንደሆነ አክለዋል።
የረጅም ጊዜ ትንበያዎች ትክክለኛነት በአንጻራዊነት አነስ ያለ እንደሚሆን ተናግረዋል።
ኢንስቲትዩ ከትንበያ ባሻገር የሚኖረው የአየር ሁኔታ በግብርና ፤ በጤና ፤ በአካባቢ ጥበቃና በውሃ ላይ የሚኖረውን ፤ አዎንታዊ እና አሉታዊ ተጽዕኖ ተከትሎ ሊወሰዱ የሚገባዎችን ጉዳዮች በተመለከተም ምክረ ሃሳብ ይሰጣል።
ኢንስቲትዩቱ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ያሉትን ማዕከላት በማጠናከር እንዲሁም ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ፤
ይበልጥ ትክክለኛ እና ታማኝ የሆኑ መረጃዎችን ለማቅረብ ወደፊትም ይሰራል ሲሉ ዶክተር ዶ/ር አሳምነው ተናግረዋል።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ.......
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments