የነሐሴ 12 የውጪ ሀገር ወሬዎች
- 3 hours ago
- 2 min read
የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ብሪታንያን በብርቱ አስጠነቀቋት፡፡
ፑቲን ብሪታንያ ለዩክሬይን ግዛት ተሻጋሪ ድሮኖችን ከማቀበል ብትቆጠቢ ይሻልሻል ማለታቸው ሬውተርስ ፅፏል፡፡
ቀደም ሲል ታይምስ ጋዜጣ ዩክሬይን በሩሲያ ላይ ግዛት ተሻጋሪ ጥቃት የምታደርሰው በብሪታንያ ስሪት ድሮኖች እንደሆነ መዘገቡ ተጠቅሷል፡፡
ከቅርብ ወራት ወዲህ ዩክሬይን በሩሲያ ላይ ግዛት ተሻጋሪ የድሮን ጥቃቷን እየደጋመች መሆኑ ይነገራል፡፡
ፑቲን እና ሌሎች የሩሲያ ሹሞች ብሪታንያ ዩክሬይንን በተራቀቁ ድሮኖች ማስታጠቋ ውድ ዋጋ ያስከፍላታል ሲሉ መዛታቸው ተሰምቷል፡፡
ሩሲያ ከዩክሬይን ጋር ስትዋጋ ከ4 አመታት በላይ ሆኗታል፡፡
ዩክሬይን ድሮኖችን ለውጊያ ማዋሏ እየጨመረ መምጣቱ ይነገራል፡፡
በሶማሊያ የባህር ዳርቻ አንድ የጭነት መርከብ በታጠቁ የባህር ወንበዴዎች መጠለፉ ተሰማ፡፡
የብሪታንያው የባህር ንግድ ተከታታይ ድርጅት የጭነት መርከቡ በ8 የታጠቁ የባህር ላይ ወንበዴዎች መታገቱን ሰምቻለሁ ማለቱን አናዶሉ ፅፏል፡፡
መርከቡን ያገቱት የባህር ላይ ሽፍቶች እስከ አፍጢማቸው የታጠቁ ናቸው ተብሏል፡፡
የባህር ላይ ንግድ ተከታታይ ድርጅቱ የተጠለፈው መርከብ የየትኛው ኩባንያ እንደሆነ አልጠቀሰም፡፡
የሽፍቶቹም ማንነት ለጊዜው አልታወቀም፡፡
ሀላፊነትም የወሰደ ወገን የለም፡፡
በሶማሊያ የባህር ዳርቻ እና በኤደን ባህረ ሰላጤ በቀደሙት አመታት ገንኖ የነበረው የመርከቦች ጠለፋ ከ6 አመታት ወዲህ የለም ከሚባልበት ደረጃ ደርሶ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡
በካሜሩን ከባድ የኮሌራ ወረርሽኝ እየተዛመተ ነው ተባለ፡፡
በተለይም ሰሜናዊው የአገሪቱ ክፍል የኮሌራ ወረርሽኙ የበረታበት እንደሆነ አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡
ወረርሽኙ መዛመት ከያዘ 1 ወር ማስቆጠሩ ተጠቅሷል፡፡
እስካሁንም ከሺህ በላይ ሰዎች በኮሌራ በሽታ መያዛቸው ተረጋግጧል ተብሏል፡፡
ወረርሽኙ 28 ሰዎችን እንደገደለ ተጠቅሷል፡፡
የጤና ባለሙያዎች የቤት ከቤት የመከላከያ ምክር እየሰጡ መሆኑ ታውቋል፡፡
ደካማ የንፅህና አጠባበቅ እና የንፁህ የመጠጥ ውሃ እጥረት ለወረርሽኙ በዋና ምክንያትነት ቀርቧል፡፡
የየመን ሁቲዎች በበርካታ የሳውዲ አረቢያ መርከቦች ላይ የሚሳየል እና የድሮን ድብደባ ፈፅመናል አሉ፡፡
በሳውዲ መርከቦች ላይ ከባድ ጥቃት መፈፀሙን የተናገሩት የሁቲዎቹ ቃል አቀባይ ያህያ ሳሪ እንደሆኑ ሳኒ ሳፋክ ፅፏል፡፡
ቃል አቀባዩ ጥቃት የተሰነዘረባቸው የሳውዲ የባህር ሀይል መርከቦች በደፈናው በርካታ ናቸው ከማለት ውጭ ብዛታቸውን በአሃዝ ይሄን ያህል ነው አላሉም፡፡
ከፊሉቹ ተመትተው ሲሰጥሙ ፤ ሌሎቹ ደግሞ በቃጠሎ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ያህያ ሳሪ ተናግረዋል፡፡
በመርከቦቹ ላይ በሁቲዎቹ ጥቃት የተፈፀመባቸው ማሪብ በተሰኘው የወደብ ከተማ ነው ተብሏል፡፡
በዚያ የጦር መሳሪያ ማከማቻ መጋዘን እንደሚገኝ ይነገራል፡፡
ሁቲዎቹ በርካታ መርከቦቿን አስምጠናል ስለማለታቸው ሳውዲ ማረጋገጫም ይሁን ማስተባበያ አልሰጠችም፡፡
የየመኑ ጦርነት ከ4 አመታት ፋታ በኋላ እያገረሸ ነው፡፡
ሳውዲ አለም አቀፍ እውቅና ያለው የየመን መንግስት ደጋፊ ነች፡፡
ሁቲዎቹ ርዕሰ ከተማዋ ሰንዓን ጨምሮ ሰሜናዊውን ክፍል ሲያስተዳድሩ ከ12 አመታት በላይ ሆኗቸዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ አዲስ ከባድ ዛቻ ሰነዘሩባት፡፡
ትራምፕ ኢራን ለምህረት ልመና ነጭ ጨርቅ ካላውለበለበች ወዮውላት ማለታቸውን አልጀዚራ ፅፏል፡፡
ኢራን እጅ ከመስጠት ሌላ ምንም ዓይነት አማራጭ እንደሌላት ትራምፕ ተናግረዋል፡፡
ትራምፕ በኢራን ላይ የዛቱባት ሁለቱ አገሮች ቀደም ሲል ደርሰውት በነበረው የጦርነት ማስቆሚያ የመግባቢያ ስምምነት መሰረት የተደረሰው የተኩስ አቁም ጊዜው ማብቃቱን ተከትሎ ነው፡፡
የተኩስ አቁሙ ጊዜው ያበቃው እምብዛም ተከባሪ ባልነበረበት አጋጣሚ ነው፡፡
የኢራን ሹሞች ስምምነቱን በመጣስ አሜሪካን በተጠያቂነት ከስሰዋታል፡፡
የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ኢስማየል ባጋይ የመጣውን እንዳመጣጡ ለመመከት ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡
አብዮታዊ ዘብ የተሰኘው የኢራን የጦር ክፍል ከፍተኛ አዛዥ የሆኑት ብርጋዲየር ጄኔራል ያዶላህ ጃቫኒ መከላከላችን ወደ ሙሉ ማጥቃት ይሸጋገራል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ከእንግዲህ የመግባቢያ ስምምነቱ ዋጋ ቢስ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የኔነህ ከበደ
_edited.jpg)



speedstars is unique in that it makes players focus on their footwork instead of merely the speed shown on the screen. Even if an athlete is fast, their advantage may be lost if their running steps aren't synchronized.