ጉዳት ከመድረሱ በፊት መቆጣጠር የተቻለውና ጉዳት መድረሱ በኦዲት የተረጋገጠ በአጠቃላይ 560 ቢሊየን 606 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የወንጀል ምርመራ መዝገቦች ተደራጅተው ምርመራ ተጣርቶባቸዋል ሲል የፌደራል ፖሊስ ተናገረ።
- 3 hours ago
- 2 min read
ነሐሴ 12 2018
ጉዳት ከመድረሱ በፊት መቆጣጠር የተቻለውና ጉዳት መድረሱ በኦዲት የተረጋገጠ በአጠቃላይ 560 ቢሊየን 606 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የወንጀል ምርመራ መዝገቦች ተደራጅተው ምርመራ ተጣርቶባቸዋል ሲል የፌደራል ፖሊስ ተናገረ።

ከ2012 ጀምሮ በተከታታይ ለ6 አመታት በተካሄዱ የፋይናንስ፣ የሙስና፣ የታክስና ጉምሩክ፣ የኮንትሮባንድ፣ የባንክ ማጭበርበር ፣ ሕገ-ወጥ የሐዋላና የመሬት ወረራ ወንጀሎች ምርመራ ከፍተኛ የሀገር ሀብት ከጉዳት አትርፈናል ብሏል ተቋሙ፡፡
ተደራጅተው በተፈጸሙና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ አደጋ በደቀኑ ወንጀሎች ላይ በተደረገ የተቀናጀ ምርመራ፣ በአጠቃላይ 560 ቢሊዮን 606 ሚሊዮን 987 ሺህ 502 ብር የሚገመት የወንጀል ምርመራ መዝገብ ተደራጅቶ መጣራቱን ጠቅሷል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከ2012 እስከ 2018 ዓ.ም ከቀረቡ 20 ሺህ 142 ጥቆማዎች ውስጥ 19 ሺህ 835 (98 በመቶ) መዝገቦች ተጠናቀው ለዐቃቤ ሕግ ተልከዋል፣ ነባር ውዝፍ መዝገቦችም ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቀዋል ብሏል።
በዚህ ሂደት 39 ሺህ 567 ተጠርጣሪዎች ተይዘው 15 ሺህ 756 ተከሳሾችና 30 ሺህ 982 ምስክሮች ፍርድ ቤት ቀርበዋል ሲል የፌዴራል ፖሊስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ተናግሯል፡፡
በፎረንሲክ ምርመራ ዘርፍም ከ2012 እስከ 2018 ዓ.ም 1 ሚሊየን 975 ሺህ 740 የአሻራ፣ 3 ሺህ 250 የጦር መሣሪያና ልዩ ልዩ ፈለግ፣ 5 ሺህ 2 የሰነድ ፣ 4 ሺህ 191 የዲጂታል ፎረንሲክ፣ 14 ሺህ 721 የኬሚስትሪና ቶክሲኮሎጂ፣ 1 ሺህ 165 የባዮሎጂ (DNA) እና 2 ሺህ 362 የቃጠሎና ፍንዳታ ምርመራዎች ተጣርተው በአጠቃላይ 2 ሚሊየን 6 ሺህ 431 ጉዳዮች ተመርምረው ምላሽ ተሰጥቷቸዋል ሲል ፖሊስ ባወጣው መግለጫ አስረድቷል።
ይህ ውጤት ሊመዘገብ የቻለው ተቋሙ የክትትልና የምርመራ ስልቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ፣ በፎረንሲክ ላቦራቶሪዎች እና " በመረጃና ማስረጃ መር የወንጀል ምርመራ መርህ" በመገንባቱ እንዲሁም ከፍትህ ሚኒስቴር ፣ ከፀጥታ ተቋማት እና ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ባደረገው ጠንካራ ቅንጅት መሆኑ ተጠቅሷል።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል አድራጊዎች ስልት መራቀቅን፣ የሳይበርና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች መጨመርን እንዲሁም የነበሩበትን የሰብዓዊ መብትና የጥራት ችግሮች ለመቅረፍ ባካሄደው ተቋማዊ ሪፎርም በወንጀል ምርመራና ፎረንሲክ ዘርፍ ከፍተኛ ስኬት ማስመዝገቡንም አስረድቷል።
ተቋሙ ከባህላዊ የምርመራ ዘዴ ወደ "መረጃና ማስረጃ መር የወንጀል ምርመራ መርህ" በመሸጋገር በርካታ አዳዲስ አሰራሮችንና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በስራ ላይ አውያለሁ ብሏል፡፡
ፖሊስ የምርመራ ክፍሎቹን በሲሲቲቪ ካሜራ በማደራጀት የሰብዓዊ መብት አያያዙን ማሻሻሉን አስረድቷል፡፡
በተጠርጣሪዎች ላይ የሚደረጉ የቃል መጠይቆችና የምርመራ ሂደቶች በድምፅና በምስል ቀርጸው መያዝ በሚችሉ የሲሲቲቪ ካሜራዎች በተገጠሙላቸው ክፍሎች ውስጥ ማካሄድ መጀመሩንም ጠቁሟል።
ይህም የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ለመከላከል አስችሏል፣ አመራሮችም እያንዳንዱን የምርመራ ሂደት በቅርበት የሚከታተሉበት ሥርዓት ተዘርግቷል ብሏል።
በፌዴራል ፖሊስ የተከናወነውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ እና የፍትሃዊ ምርመራ ሂደት ማሻሻያ የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ፣ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀልና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ተወካዮች በአካል በተደጋጋሚ በመጎብኘት ማረጋገጣቸው ጠቅሷል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ.....
ንጋቱ ሙሉ
_edited.jpg)


The sense of player control over every step is what really sets space waves apart, not only its speed, geometric hurdles, or visual vision.