top of page


በዩጋንዳ የፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ የምርጫ ዋነኛ ተፎካካሪ የነበረው ሮበርት ካያጉላኒ ለፖሊስ እጅ እንዲሰጥ ከትናንት አንስቶ የ48 ሰዓታት ጊዜ ተሰጠው፡፡
ጥር 14/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ዩጋንዳ በዩጋንዳ የፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ የምርጫ ዋነኛ ተፎካካሪ የነበረው ሮበርት ካያጉላኒ ለፖሊስ እጅ እንዲሰጥ ከትናንት አንስቶ የ48 ሰዓታት ጊዜ ተሰጠው፡፡ ካያጉላኒ ማስጠንቀቂያው የተሰጠው የአገሪቱ የጦር ሰራዊት አዛዥ በሆኑት የፕሬዘዳንቱ ልጅ ጄኔራል ምዑዚ ኬኔሩጋባ እንደሆነ አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ ሮበርት ካያጉላኒ አወዛጋቢውን ምርጫ ተከትሎ ራሱን መሸሸጉ እየተናገረ ነው፡፡ የቀድሞው አቀንቃኝ እና በመድረክ ስሙ ቦቢ ዋይን የተሰኘው ሮበርት ካያጉላኒ ፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ አሸናፊ የተደረጉበት ምርጫ ታላቅ ማጭበርበር የተፈፀመበት ነው ብሏል፡፡ ካያጉላኒ የምርጫው ውጤት እንዲሰረዝ ለማድረግ ወደ ፍርድ ቤት በመሄድ አልሟገትም ማለቱ ተሰምቷል፡፡ አማራጭ ሰላማዊ የትግል መንገዶችን
Jan 222 min read


ከሳምንት በፊት ከናይጄርያ ኬቢ ግዛት አዳሪ ትምህርት ቤት ታግተው የተወሰዱ ሴት ተማሪዎች በሙሉ ተለቀቁ፡፡
ህዳር 17 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ናይጄርያ ከሳምንት በፊት ከናይጄርያ ኬቢ ግዛት አዳሪ ትምህርት ቤት ታግተው የተወሰዱ ሴት ተማሪዎች በሙሉ ተለቀቁ፡፡ በጊዜው 25 ሴት ተማሪዎች ታግተው እንደነበር ቢቢሲ አስታውሷል፡፡ አንዷ አስቀድሞ ከአጋቾቿ ማምለጧ ሲነገር ሰንብቷል፡፡ ታጋቾቹን ሴት ተማሪዎች ለማስለቀቅ የናይጀሪያ የፀጥታ ሀይሎች በፕሬዘዳንት ቦላ ቲኑቡ ትዕዛዝ በቅንጅት አሰሳ ላይ ተሰማርተው ነበር፡፡ ሴት ተማሪዎቹ ከእገታ ተለቀዋል ቢባልም በምን ዓይነት ሁኔታ እንደተለቀቁ የተብራራ ነገር የለም፡፡ ባለፈው ሳምንት አርብ ደግሞ ከኒጀር ግዛት የካቶሊክ ትምህርት ቤት ከ250 በላይ ተማሪዎች ታግተው መወሰዳቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡ ከኒጀር ግዛት ታግተው የተወሰዱት ተማሪዎች ግን እንዳልተለቀቁ ተጠቅሷል፡፡ #ብራዚል
Nov 26, 20252 min read


ህዳር 15 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ናይጄርያ ከናይጄርያዋ ኒጀር ግዛት የአንድ የካቶሊክ ትምህርት ቤት ከታገቱት ከ300 በላይ ተማሪዎች መካከል ሃምሳው ከአጋቶቻቸው ማምለጣቸው ተሰምቷል፡፡ ጉዳዩን የሚከታተለው ቡድን 50ው ተማሪዎች ከአጋቾቻቸው ማምለጣቸውን አረጋግጫለሁ ማለቱን ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ይሁንና በምን ሁኔታ እና ከየት እንዳመለጡ አላብራራም፡፡ አምላጮቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል ማለቱ ተሰምቷል፡፡ የናይጀሪያ የፀጥታ ሀይሎች ታጋቾቹን ለማስለቀቅ በተቀናጀ አሰሳ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያም በኬቢ ግዛት ከሚገኝ አንድ አዳሪ ትምህርት ቤት 20 ተማሪዎች ታግተው መወሰዳቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡ እገታውን በመስጋት ብዙዎቹ የናይጀሪያ ግዛቶች ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ማድረጋቸው በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ #ሳውዲ_አረቢያ ሳውዲ አረቢያ በ1
Nov 24, 20252 min read


ጥቅምት 8፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች
#ጊኒ_ቢሳዎ የጊኒ ቢሳዎ ርዕሰ ከተማ ኤሌክትሪክ በመቋረጡ በድቅድቅ ጨለማ መዋጧ ተሰማ፡፡ ቢሳዎ በጨለማ የተዋጠችው የአገልግሎት ዋጋዬ አልተከፈለኝም ያለ የቱርክ ኩባንያ አገልግሎት በማቋረጡ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡...
Oct 19, 20232 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page

