top of page

ሚያዝያ  18፣2016 - ኢትዮጵያን አስጠልይን ብለው የመጡ ስደተኞች ቁጥር ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንድ ሚሊዮን በላይ መድረሱ ተሰማ

ኢትዮጵያን አስጠልይን ብለው የመጡ እና የተመዘገቡ ስደተኞች ቁጥር ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንድ ሚሊዮን በላይ መድረሱ ተሰማ፡፡


በኢትዮጵያ ያሉ ስደተኞች እና ስደተኝነት ጠያቂዎች በብዛት አንድ ሚሊዮን 59 ሺህ 232 መድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛው የስደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) ለሸገር በላከው መግለጫ ጠቅሷል፡፡


ባለፈው አንድ ወር ብቻ ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ሪፖርቱ ይነገራል፡፡


በሱዳን ያለውን የእርስ በርስ ጦረነት ሽሽት ኢትዮጵያ የመጡ ስደተኞች ብቻ 52 ሺህ 666 መድረሱን ኮሚሽኑ በሪፖቱ አስረድቷል፡፡


በኢትዮጵያ ከሚገኙ ከ1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞች ውስጥ 80 በመቶው ሴቶች እና ህፃናት መሆናቸው ተነግሯል፡፡


በሀገሪቱ ተጠልለው ለሚገኙ ስደተኞች ምግብ ጨምሮ የተለያዩ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት ላለንበት የፈረንጆቹ አመት 426 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተጠቅሷል፡፡

ይሁን እንጂ እስካሁን ከለጋሾች የተገኘው 55.3 ሚሊዮን ዶላር ወይንም 13 በመቶው ብቻ መሆኑ በሪፖርቱ ሰፍሯል፡፡


ይህም ለስደተኞች የሚሰጥን ድጋፍ በእጅጉ እንደሚጎዳው ተነግሯል፡፡


በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከሚገኙ የውጭ ሀገር ስደተኞች ከፍተኛውን ቁጥር የሚያዙት የሱዳን ስደተኞች ሲሆኑ የደቡብ ሱዳን ፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ፣ እና ኬኒያ ስደተኞች ይከተላሉ፡፡


የየመን፣ የኮንጎ ዲሞክራቲክ እና የሶሪያ ስደተኞችም እንደሚገኙ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram:  @ShegerFMRadio102_1




bottom of page