top of page

መስከረም 2 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች

  • Sep 12, 2025
  • 2 min read

በአሜሪካ ሴቶችን የወሲብ ባሮቹ በማድረግ ሲገለገልባቸው ነበር ከተባለው ጄፍሪ ኤፒስተን ጋር ግንኙነት ነበራቸው የተባሉት በአሜሪካ የብሪታንያው አምባሳደር ፒተር ማንዴልሰን ከሀላፊነታቸው ተባረሩ፡፡


አምባሳደሩ ከሀላፊነት የተባረሩት በቀደመውጊዜ ለኤፒስተን የፃፉት የኢሜይል መልዕክት ከተረጋገጠ በኋላ ነው ተብሏል፡፡


ኤፒስተን ተይዞ በታሰረበት እስር ቤት በአወዛጋቢ ሁኔታ ሕይወቱ ያለፈው ከ6 አመታት በፊት ነው፡፡


የሰውየው ህይወት ቢያልፍም ወንጀሉ ብዙ ዝነኞችን በማነካካቱ አሁንም አነጋጋሪነቱ አልሰከነም፡፡

47ኛው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕም በጄፍሪ ኤፒስተን ጉዳይ አሁንም ስማቸው ተያይዞ እየተነሳ ነው፡፡


ትራምፕ በቀደመው ጊዜ ለግለሰቡ ፅፈውታል የተባለ የልደት ማስታወሻ በኮንግረሱ ይፋ ተደርጓል ቢባልም ዋይት ሐውስ ማስታወሻው በትራምፕ የተፃፈ እንዳልሆነ በማስተባበል መጠመዱ ይነገራል፡፡


ከሀላፊነት የተባረሩት ማንዴልሰን በአሜሪካ የብሪታንያ አምባሳደርነቴ ታላቅ ስኬቴ ነበር ማለታቸውን ቢቢሲ ፅፏል፡፡



በኢንዶኔዥያዋ የቱሪስቶች መዝናኛ ደሴት ባሊ በከባድ የጎርፍ አደጋ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ታወጀ፡፡


በደሴቲቱ የአስቸኳይ ጊዜ የታወጀው በዚያ ከባድ ጎርፍ ያስከተለው አደጋ 14 ሰዎችን ከገደለ በኋላ እንደሆነ አረብ ኒውስ ፅፏል፡፡


በባሊ ከባድ ጎርፍ የደረሰው ባለፈው ሳምንት ሲጥል በሰነበተውዶፍ ዝናብ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡


ዶፍ ዝናብ መጣሉ ቢያቆምም ጎርፍ እና የውሃ ሙላ ሰፊ አካባቢን ማዳረሱ ታውቋል፡፡


በጎርፍ አደጋው ሕይወታቸው ካለፈው ሌላ የደረሱበት የጠፋም እንዳሉ ተጠቅሷልል፡፡


መጠነ ሰፊ የነፍስ አድን ጥረት እየተዳረገ መሆኑ ተሰምቷል፡፡


ባለ ከኢንዶኔዥያ ግዛቶች ሁሉ በውጭ ቱሪስቶች መስህብነቷ የሚደርስባት እንደሌለ መረጃው አስታውሷል፡፡



አሜሪካ በየመን ሁቲዎች ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ጣለችባቸው ተባለ፡፡


ታላቋ አገር በሁቲዎቹ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ የጣለችባቸው ከእስራኤል ጋር ክፉኛ እየተጋጩ መምጣታቸውን ተከትሎ እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡


አዲሱ የአሜሪካ ማዕቀብ 32 የሁቲዎቹን ሹሞች እና 4 መርከቦቻቸውን የተመለከተ ነው ተብሏል፡፡


አሜሪካ በሁቲዎቹ ላይ የጣለችው ማዕቀብ የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያቸውን እንደሚያሰናክልባቸው ተጠቅሷል፡፡


ሁቲዎቹ እስራኤል የጋዛ የጦር ዘመቻዋን ከጀመረች አንስቶ ለፍልስጤማውያን አጋርነታቸውን ለማሳየት ከእስራኤል ጋር ነገር እየተፈላለጉ ነው፡፡


የየመንን ሰሜናዊ ክፍል የሚያስተዳድሩት ሁቲዎቹ የኢራን ሁነኛ የጦር እና የፖለቲካ ሸሪኮች መሆናቸው ይነገራል፡፡



የደቡብ ሱዳኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት ሪያክ ማቻር በብርቱ ብርቱ ወንጀሎች ክስ ተመሰረተባቸው፡፡


ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት ሪያክ ማቻር በወንጀል የተከሰሱት በተለምዶ ዋይት አርሚ የተሰኘው የኑዌር ወጣቶች ታጣቂ ቡድን በአፐር ናይል ግዛት ናሲር ከተማ በሚገኝ የመንግስት የጦር ሰፈር ላይ አድርሶታል በተባለ ጥቃት ምክንያት እንደሆነ TRT አፍሪካ ፅፏል፡፡


በዚያ ጥቃት 250 የመንግስት ወታደሮች መገደላቸው ይነገራል፡፡


ታጣቂ ቡድኑ ከማቻር ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ነው ይባላል፡፡


በዚሁ ምክንያት ማቻር ካለፈው መጋቢት ወር አንስቶ በቁም እስር ሆነው መቆየታቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡


የደቡብ ሱዳን መንግስት ለናሲሩ ጥቃት ከማቻር ራስ አልወርድም እያለ ነው፡፡


ከማቻር ጋርም አባሪ ተባባሪዎቻቸው ናቸው የተባሉ 8 የቀድሞ ሹሞችም ክስ እንደተመሰረተባቸው ተሰምቷል፡፡


የኔነህ ከበደ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Recent Posts

See All
የሐምሌ 23 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ግብፅ በግብፅ የሜዴትራኒያን የባህር ዳርቻ የነበረ የአሜሪካ የጋዝ ማጠራቀሚያ መርከብ በድሮን ተመታ ተባለ፡፡ ሁለት የደህንነት ምንጮች መርከቡ በድሮን እንደተመታ አረጋግጠውልኛል ሲል ሬውተርስ ፅፏል፡፡ መርከቡ በድሮን እንደተመታ በእሳት መያያዙ ታውቋል፡፡ ቃጠሎው ወደ ሌላ መርከብም ተጋብቶ ነበር ተብሏል፡፡ ኋላ ግን

 
 
 
የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ፣አፍሪካዊያን የጋራ መጪ እድላቸውን እንዲቀርፁ ማገዝ ያስፈልጋል ተባለ።

ሐምሌ 23 2018 የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ፣አፍሪካዊያን የጋራ መጪ እድላቸውን እንዲቀርፁ ማገዝ ያስፈልጋል ተባለ። የአፍሪካ ሀገሮች እርስ በእርስ፣በአፍሪካና በሩሲያ እንዲሁም አፍሪካ ከተቀረው ዓለም ጋር ያላትን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማሳደግን ዓለማው ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በተባበሩት መንግስታት የአ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page