ሐምሌ 21 2017 - መምህራን በእንግሊዘኛ ትምህርት ፈተና ያመጡት ውጤት ደካማ ሆኖ መመዝገቡን ተነገረ
- sheger1021fm
- Jul 28
- 1 min read
ለመጀመሪያ ጊዜ ትምህርት ሚኒስቴር በሰጠው የ2ኛ ደረጃ የመምህራን አቅም ማሻሻያ ስልጠና የተሳተፉ መምህራን በእንግሊዘኛ ትምህርት ፈተና ያመጡት ውጤት ደካማ ሆኖ መመዝገቡን ተነገረ፡፡
ባለፈው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የ2ኛ ደረጃ መምህራን ወደ ዩኒቨርሲቲ ገብተው የአቅም ማሻሻያ ስልጠና በሚያስተምሩት የትምህርት ዓይነት መውሰዳቸው ይታወሳል፡፡
43,000 የሚሆኑ መምህራን ስልጠናውን ዩኒቨርስቲ ውስጥ ገብተው ከወሰዱ በኋላ ፈተና ተሰጥቷቸው ነበር፡፡
ፈተናውን ከወሰዱ #መምህራን መካከል 61.4 ከመቶ የሚሆኑት ብቻ ማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸው ይታወሳል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 የክረምት የመምህራን አቅም ማሻሻያ ስልጠናን በተመለከተ አጠቃላይ ትንተና መስራቱን ተናግሯል፡፡
በዚህ የውጤት ትንተና መሰረት መምህራን 70 ከመቶ የሚወስዱት ፈተና ቀጥታ ከትምህርት ሚንስቴር የሚዘጋጀው ሲሆን ቀሪው 30 በመቶ ደግሞ በዩኒቨርስቲ መምህራን አማካኝነት የሚሞላ ነው፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ሙሉቀን ንጋቱ የዩኒቨርስቲ መምህራን የሚሞሉት 30 ከመቶ ውጤት ተትቶ ሙሉ ለሙሉ በማዕከል በተሰጠው ፈተና ብቻ ውጤቱ ቢሰራ አሁን የተገኘው ውጤት በ17 ከመቶ ያንስ ነበር ሲሉ ተናግረዋል፡፡
መምህራኖቹ የተፈተኑን በየትምህርት ቤቶቻቸው ለተማሪዎቻቸው የሚፈትኑት ፈተና ነበር ያሉት ዶክተር ሙሉቀን አሁን የተገኘው ውጤቱ ከዚህ ቀደም ትምህርት ሚኒስቴር ለመምህራን ሰጥቶ ካገኘው ውጤቶች የተሻለ ቢሆንም ግን ገና ብዙ መስራት እንዳለብን ያሳያል ብለዋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው የተፈጥሮ ሳይንስ የ2ኛ ደረጃ የመምህራን የአቅም ማሻሻያ ስልጠና በአብዛኛው የትምህርት ዓይነቶች ጥሩ ውጤት ቢመጡን እንግሊዘኛ ትምህርት ላይ የተገኘው ውጤት ግን አሳሳቢ ነው ሲሉ ዶክተር ሙሉቀን ንጋቱ ጠቅሰዋል፡፡
ፈተናውን ከወሰዱ መምህራን መካከል አብዛኛዎቹ መምህራን 70 ከመቶ የተቀመጠውን የመቁረጫ ነጥብ ማምጣት ተስኗቸዋል ሲሉም አስረድተዋል፡፡
ሙሉበ ዘገባውን ያድምጡ……
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
Comments