top of page

ተማሪዎች በወርቅ ማዕድን ስራ ላይ መሰማራት ለትምህርት ማቋረጥ አንዱ ምክንያት መሆኑን የቤንሻንጉሉ ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ ተናገረ፡፡ 

  • sheger1021fm
  • 2 hours ago
  • 2 min read

ጥር  21/2018

 

ተማሪዎች በወርቅ ማዕድን ስራ ላይ መሰማራት ለትምህርት ማቋረጥ አንዱ ምክንያት መሆኑን የቤንሻንጉሉ ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ ተናገረ፡፡

 

ችግሩን ለመቅረፍ ከፀጥታ አካላትና ከወረዳዎች ጋር በመነጋገር እየሰራ መሆኑን አስረድቷል፡፡

 

የቤንሻንጉሉ ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ዘነበ በዚህ አመት 315 ሺህ ተማሪዎች ለመመዝገብ ታቅዶ 305 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎችን መዝግበናል ብለዋል፡፡

 

በክልሉ በየዓመቱ ለተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት አለመምጣትና ከትምህርት ገበታ መቅረት ዋንኛ ምክንያት የማእድን ስራ ተጠቃሽ ነው ብለዋል፡፡

አሁን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከወረዳዎች ጋር በመነጋገር የወርቅን ቁፋሮ ስራ በሚሰራባቸው አካባቢዎች ለትምህርት የደረሰ ልጅ በትምህርት ቀን ስራ እንዳይሰራ ከፀጥታ አካላት ጋር ወረዳዎች ህግ አውጥተው ክትትል እያደረጉ ነው፡፡

 

ተማሪው ችግር ካለበት በእረፍት ቀናት ብቻ እንዴት ይደረግ የሚለው እየታየ ነው ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡

 

በክልሉ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ የተማሪ መፅሀፍ እጥረት አለመኖሩን የነገሩን አቶ ምትኩ ዘነበ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ባሉ ክፍሎች በአንዳንድ የትምህርት ዓይነቶች ላይ የመፅሀፍት እጥረት መኖሩን ያስረዳሉ፡፡

 

የክልሉ መንግስት ችግሩን በማየት በጀት መድቦ ህትመት እንዲደረግ አዟል በቅርቡ ችግሩ ሊፈታ ይችላል ሲሉም አክለዋል፡፡

 

እንደ እንግሊዘኛ ፣ አካባቢ ሳይንስና በክልሉ ውስጥ በሚሰጡ 5 የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች የሚያስተምሩ የመምህራን እጥረት መኖሩን የቤንሻንጉሉ ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ዘነበ ጠቅሰዋል፡፡

 

መምህራን ለማፍራት በክልሉ ውስጥ በሚገኘው አንድ የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋም ነው፡፡

 

በዘርፉ መሰማራት የሚፈልጉ ልጆችን መልምለን ክፍተት በታየባቸው የትምህርት ዓይነቶች እጩ መምህራንን እያሰለጠንን ነው ብለዋል፡፡

 

በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማምጣትና የተማሪዎች ማቋረጥን ለመቀነስ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከወረዳዎች ጋር አብሮ እየሰራ ነው ብለዋል አቶ ምትኩ ዘነበ፡፡

 

የመፅሀፍት እጥረቱ በቅርቡ ይፈታል የሚል እምነት አለኝ የመምህራን እጥረቱ ግን በአንድ ጀንበር መፍታት ስለማይቻል ሰልጣኞች እስከሚመረቁ መጠበቅ ያስፈልጋል ሲሉም መክረዋል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

 

በረከት አካሉ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

YouTube : https://shorturl.at/18TS1                   

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page